TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሀዉልቶች ነገር⬇️

እዉነት እንነጋገር!

ከወዲያ እና ከወዲህ ተመሳሳይ ድምፅ! ሀሳብ የሌለበት ንትርክ! አሁን ክርክሮች ስለሀዉልቶች ሆኗል። ግማሹ የአኖሌ ሀዉልት እንዲፈርስ ይጠይቃል። ሌላዉ ደግሞ በምኒልክ ሀዉልት ላይ አተኩሯል። ይህ ጫወታ የማን እንደሆነ ይታወቃል። የእሳትና ጭድ ፖሊሲ አካል ይመስላል። ሀዉልት ሟቾችን ይመለከታል። ጠላት ሆን ብሎ ትኩረታችንን ወደ ሟቾች ይስባል። በመሀሉ የኗሪዎች ጉዳይ ተዘንግቷል። ስለሞቱት እያለቀስን የአሁኑን እና የወደፊቱን ትዉልድ በጅምላ እንዳንገድል ያሰጋል። በ21ኛ ክፍለ ዘመን በዝህ ደረጃ መታለላችን ምን ይባላል? ሌላ ጋ መማሪያ የሆነ ታሪክ እኛ ጋ ለምን የግጭት መነሻ ይሆናል? ሰዉ እንዴት በገዛ እጁ በተከለዉ ሀዉልት ሰለባ ይሆናል?

እዉነት እላለሁ፦

ሰዉ ከሀዉልት ይበልጣል!
ልብ ያለዉ ልብ ይበል!
ሠላም!

#ታዬ_ደንዳዓ #TayeDendea (የኦሮሚያ ፍትህ ቢሮ ሀላፊ )
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#TayeDendea

የሰላም ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ታዬ ደንደአ ከስልጣን መነሳታቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ እንደደረሳቸው ተሰምቷል።

ለሚኒስትር ዴኤታው የተፃፈው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፊርማ ያረፈበት ደብዳቤ ፦

" ከመስከረም 28 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የሠላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነዉ ላበረከቱት አስተዋጽኦ እያመስገንኩ ከታህሳስ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከኃላፊነት የተነሱ መሆኑን አስታዉቃለሁ። " ይላል።

ደብዳቤው ከራሳቸው አቶ ታዬ ገፅ የተገኘ ነው።

ይህ ተከትሎ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ታዬ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ተችተው ፅፈዋል።

አቶ ታዬ ፤ " ለክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ " ብለው ባሰራጩት ፅሁፍ " የተናገሩትንና የፃፉትን የመደመር እሳቤ አምኜ ተከተልኩዎት። አሁን ግን በተናገሩት የማይኖሩ ብቻ ሳይሆን በሰዉ ደም የሚጫወቱ አረመኔ መሆንዎን ተረድቻለሁ። " ብለዋል።

" እዉነት መስሎኝ በሀገር ህልውና ስም ሲያካሄዱ የነበረዉንና ኢትዮጵያውያንን ከማገዳደል አልፎ ሀገሪቷን ያደቀቃትን ከንቱ ጦርነት ሳዳምቅልዎ በነበረበት ወቅት ሲያወድሱኝ ነበር። " ያሉት አቶ ታዬ " ዛሬ ነገሩ ገብቶኝ የወንድማማቾች መገዳደል ይቆም ዘንድ ለሰላም በመወገኔ ከስልጣን አነሱኝ። " ብለዋል።

" ለወንበርና ለመኪና በመገዛት ኦሮሞን በኦሮሞ ለማጥፋትና ኦሮሞን ከወንድሞቹ ጋር ለማጣላት የሚጫወቱትን ቁማር እያየሁ ዝም ባለማለቴ እጅግ ደስተኛ ነኝ። " ያሉት አቶ ታዬ " ስለነበረን አጭር ቆይታ አመሰግናለሁ። እስካለሁ ድረስ ለሰላምና ለህዝቦች ወንድማማችነት የማደርገዉ ትግል ይቀጥላል " ሲሉ ፅፈዋል።

ምንም እንኳን አቶ ታዬ ከስልጣን መነሳታቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ አያይዘው ብስጭታቸውን ቢገልጹም ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

አቶ ታዬ ደንደአ በተለያየ ጊዜ እሳቸው ያሉበትን መንግሥት በመተቸት ይታወቃሉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#TayeDendea

አቶ ታዬ ደንደአ ትላንት በይፋዊ ፌስቡክ ገፃቸው ከስልጣን መነሳታቸውን የሚገልፅ የስንብት ደብዳቤ አያይዘው ከለጠፉ እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ጠንካራ ቃላትን ተጠቅመው ትችት ከሰነዘሩ በኃላ #በሕግ_ሊያስጠይቃቸው የሚችል ጉዳይ ይኖር እንደሆነ ተጠይቀው ነበር።

አቶ ታዬ ፤ " በሕግ መጠየቅ ምን ችግር አለው ፣ ነገር ግን ሕግ የታለና በሕግ ይጠይቁኛል። ከጠየቁኝ ደግሞ ዝግጁ ነኝ " የሚል ምላሽ ነው የሰጡት።

በሕግ ሊጠየቁ የሚችልበት እድልም እንደሌለ ተናግረው ነበር።

ዛሬ የፀጥታ እና የደህንነት የጋራ ግብረኃይል አቶ ታዬን ደንደአን በሕግ ቁጥጥር ስር ያዋላቸው ሲሆን መኖሪያ ቤታቸው ላይም ብርበራ አድርጓል።

ግብረ ኃይሉ አቶ ታዬ ደንደአን ፦

- በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በንፁሃን ዜጎች ላይ ሲፈፀሙ በነበሩ የሽብር ተግባራት በተለይም ደግሞ #ከእገታ ጋር በተያያዘ እጃቸው እንዳለበት አሳውቋል።

(አቶ ታዬ ደንደአ በ #ሰላም_ሚኒስቴር ውስጥ ሆነው በተለያዩ ጊዜ በሚፈፀሙ የእግታ ጉዳዮች እጃቸው እንዳለበት የታወቀው መቼ ነው ? ከዚህ ቀደም ታውቆ ከሆነ ለምን እስከዛሬ ዝም ተባሉ ለሚለው ጉዳይ የተብራራ ነገር የለም)

- የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ሰላምን ለማስፈን ከመስራት ይልቅ ከፀረሠላም ኃይሎች ጋር ተሳስረው ለጥፋት ተልዕኮ በህቡዕ ሲሰሩ ነበር ብሏቸዋል።

- መንግስት እና የፓርቲ መዋቅሩን በሴራ ለመናድ በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ ነበር ብሏቸዋል።

- መንግሥት በሽብርተኝነት ከፈረጀው ከኦነግ ሸኔ አመራሮች እና በሽብር ወንጀል ከሚጠረጠሩ ፅንፈኛ ኃይሎች ጋር ትስስር ፈጥረው መንግስትን በአመፅ፣ በሽብርና በትጥቅ ለመጣል ሲያሴሩ ተደርሶባቸዋል ብሏል።

አቶ ታዬ ደንደአ ከሰሞኑን ለመገናኛ ብዙሃን እና በራሳቸው የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው የተለያዩ አስተያየቶችን ሲሰጡ የነበረ ሲሆን ትላንት ታሕሳስ 1 በኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተፃፈ ደብዳቤ ከስልጣን እንዲነሱ ተደርገዋል።

አቶ ታዬ ከስልጣን ለመነሳታቸው ምክንያቱ ጦርነት ተቃውመው ስለእርቅ ስለተናገሩ እንጂ ሌላ ምክንያት እንደሌለ ተናግረዋል። " በጦርነቱ ጊዜ ጦርነቱን ስደግፍ ሲያበረታቱኝ ነበር ሕዝቡ ይታረቅ ስንል ነው ያመማቸው " ያሉት አቶ ታዬ ሰላምን በመደገፌ ነው ከስልጣን የተነሳሁት ብለዋል።

ግብረ ኃይሉ ግን አቶ ታዬ ስልጣን ላይ ቁጭ ብለው እራሳቸው ያሉበትን #መንግስት እና #ፓርቲ ለመናድ መንግስትንም በሽብር ትጥቅ ለመጣል ከፀረሠላም ኃይሎች ጋር ሲሰሩ እንደደረሰባቸው አመልክቷል።

ልክ በቁጥጥር ስር እንደሚውሉ ሲያውቁ ደግሞ #ታጋይ ለመምሰል በየማህበራዊ ትስስር ገፆች ፀረ-ሰላም ፅሁፎችን እና ንግግሮችን ሲያስተላልፉ ነበር ብሏል።

@tikvahethiopia