TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የዕለቱ መልዕክት፦

"ጨለማ ጨለማን አያጠፋም፤ ብርሃን እንጂ! ጥላቻ ጥላቻን አያጠፋም፤ #ፍቅር እንጂ!"

"Darkness cannot drive out darkness; only light can do that. #Hate cannot drive out hate; only #love can do that."

ሰላም እደሩ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዕለቱ መልዕክት፦

ከጭፍን ጥላቻ መላቀቅ ይቻላል!

አብዛኞቹ ሰዎች ጭፍን ጥላቻን በመሠረተ ሐሳብ ደረጃ የሚያወግዙ ቢሆኑም ከጭፍን ጥላቻ መዳፍ የሚላቀቁ ግን ጥቂቶች ናቸው። እንዲያውም ሥር የሰደደ ጭፍን ጥላቻ ያላቸው ብዙ ሰዎች ጥላቻ እንደሌላቸው ሊናገሩ ይችላሉ። ሌሎች ደግሞ ሰዎች ጭፍን ጥላቻቸውን ይፋ እስካላወጡ ድረስ ምንም ጉዳት የለውም ይላሉ።

ይሁን እንጂ ጭፍን ጥላቻ ሰዎችን የሚጎዳና የሚከፋፍል መጥፎ ነገር ነው። ጭፍን ጥላቻ የድንቁርና ልጅ ነው ቢባል የልጅ ልጁ ደግሞ ጠላትነት ነው። ቻርልስ ካለብ ኮልተን የተባሉት ደራሲ (1780-1832) “አንዳንድ ሰዎችን ስለማናውቃቸው #እንጠላቸዋለን። ስለምንጠላቸውም #ልናውቃቸው አንችልም” ብለዋል። ጭፍን ጥላቻን ሰዎች መማር እንደሚችሉ ሁሉ ማስወገድም ይችላሉ።

Via #JW

#ፍቅር #ሰላም #አንድነት #ተስፋ #ኢትዮጵያ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ድሬዳዋ

የድሬዳዋን የፍቅር ፣የሰላምና የአንድነት መገለጫ እሴቶች ለመመለስ ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ የከተማዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አህመድ መሐመድ ጥሪ አቀረቡ፡፡ “አንድ ዕድል ለሰላም” በሚል መሪ ሃሳብ የዛፍ ጥላ ሥር የእርቅ ሰላም ውይይት በድሬደዋ ተካሄዷል። በውይይቱ ተሳተፉት ምክትል ከንቲባው እንደተናገሩት ድሬዳዋ ሁሉም የሀገሪቱ ህዝቦች በፍቅርና በአንድነት የሚኖርባት የፍቅር አርአያ ናት፡፡ ይህ ለሀገር አርአያ የሆነውን #ፍቅር ከጊዜ ወደ ጊዜ ለመሸርሸር የሚደረገው ጥረት ቦታ እንደሌለው ገልጸዋል፡፡ የድሬዳዋ አርአያዊ አንድነትን ለመጠበቅና በትውልድ ውስጥ የትላንቱን ታላቅ የህብረት ስብዕና ለመመለስ ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ አመልክተዋል፡፡

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA💪ክብር ይገባችኃል!

ስንተባባር በአንድነት ስንቆም ምንም ነገር አያቅተንም!! 6710 የልብ ህሙማን ህፃናትን አለንላችሁ እንበላቸው!!

#TIKVAH_ETHIOPIA_FAMILY

Screenshot ወደዚህ ግሩፕ👇

https://t.iss.one/joinchat/FCD9AhWFZJX_rX95-4rWNQ

#አንድነት #ተስፋ #መተሳሰብ #ፍቅር #ቲክቫህ
❤️ከ3000 በላይ አባል❤️

6710 ላይ የህፃናት የልብ ህክምናን ለማገዝ በተከፈተው ግሩፕ ላይ እስካሁን ከ3 ሺህ የሚበልጡ የቤተሰባችን አባላት ተቀላቅለውናል!! በሺዎች የሚቆጠር ገንዘበ እንደ አቅማችን አስተዋፆ እያደረግን እንገኛለን!! ሀገር ወዳድነት መገለጫው ይህ ነው!!

Screenshot ወደዚህ ግሩፕ👇

https://t.iss.one/joinchat/FCD9AhWFZJX_rX95-4rWNQ

እኔ ካለኝ ላይ አካፍያለሁ?? እናተስ??

ለአንድ መልዕክት የሚቆርጠው 1 ብር ብቻ ነው!!


በትንሹ 3 መልዕክት ይላኩ!

#አንድነት #ተስፋ #መተሳሰብ #ፍቅር #ቲክቫህ
TIKVAH-ETH 2011 ዓ/ም- የፎቶ ማጠቃለያ⬆️

•ሀረማያ
•ወሎ
•ደብረብርሃን
•ወልዲያ
•መቐለ
•ዋቸሞ
•መቐለ
•ወላይታሶዶ
•ሀዋሳ
•አርባምንጭ
•ጅማ

#ተስፋ #ፍቅር #ሰላም #TIKVAH

#STOP_HATE_SPEECH

በጎዞው ላይ ያልተሳተፋችሁ ደግሞ በያላችሁበት ሆናችሁ ዓላማውን በሀሳብ ስትደግፉ ነበር። ተመስግናችኃል!!

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

🔖በበጎ አድራጎቱ ስራም በአቅማችሁ ለቻላችሁት ሁሉ ፤ድጋፍ ለሚፈልጉ ወገኖችም ድጋፍ ያደረጋችሁበት አመት ነበር።

🔖የየአካባቢያችሁን እውነተኛ ክስተቶችም በማካፈል ፍፁም የተሳካ አመት ነበር። በተለይ ሀሰተኛ መረጃዎችን በመከላከል ትልቅ ስራ ሰርታችኃል።

🔖መልካምነት ጎልቶ እንዲታይ በየአካባቢው መልካም ስራዎችን ሰርታችሁ ያለፋችሁበት ዓመት ነበር።

🔖የቤተሰቡ አባላት ለሀገሪቱ ችግር ከመሆን ይልቅ የመፍትሄ አካል ለመሆን በሁሉም አቅጣጫ የሰራችሁበት ነበር።
.
.
.
ብዙ ብዙ ሌሎች ስራዎች!

በአጠቃላይ ጥሩ የሚባል አመት ነበር። ሁላችሁም የዚህ ቤተሰብ አባላት እንኳን አደረሳችሁ። አዲሱ አመት ደግሞ ትልልቅ ስራዎችን የምንሰራበት ነው። ተዘጋጁ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በደንብ ተመልከቱ⬆️

እኛ እንዲህ ነን፤ ተያይዞ፣ ተቻችሎ፣ ተዋዶ መኖር ካልቻልን ተያይዞ መጥፋት ነው የሚሆነው፤ አንዱን ጠጠር ብታነሱት ሁሉም ይፈርሳል፤ ለሁሉም መኖር የአንዱ መኖር ወሳኝ ነው።

#እንዋደድ #እንከባበር #እንፋቀር #ሰላም #ፍቅር #ተስፋ

ሀሳቡ ከማህበራዊ ሚዲያ ተወሰደ!


🚪መስከረም 2 ቀን 2012 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ #በጳጉሜ_ወር ለሀገር ሰላም እና አንድነት በመላው ዓለም በምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፀሎት እና ምህላ ወስኗል። ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ፣ ጌዴኦ አማሮና ቡርጂ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ፥ ቋሚ ሲኖዶሱ 5ቱን የጳጉሜ ቀናት በፀሎትና ምህላ እንዲታሰብ መወሰኑን ገልፀዋል።…
"...ቋሚ ሲኖዶስ በወሰነው መሰረት ህዝበ ክርስቲያኑ #በአንድነት እና #በፍቅር ሊፀልይ ይገባል" - ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር)

የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ፅ/ቤት የውጭ ጉዳይ መምሪያ የበላይ ኃላፊና የድሬዳዋና ጅቡቲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶክተር) ፥ ቋሚ ሲኖዶስ በወሰነው ውሳኔ መሰረት ከጳጉሜ 1 እስከ 5 ድረስ ባሉት ቀናት በአንድነት እና በፍቅር መፀለይ እንደሚገባ ገልፀዋል።

"ምዕመናኑ በአምስቱ ዕለታት #ስለሀገር ሰላም፣ #ፍቅር እና #አንድነት፣ በፀሎት እና በምዕላ በትጋት ጊዜውን እንዲያሳልፍ ጥብቅ መመሪያ የተላለፈ መሆኑን በቋሚ ሲኖዶስ በኩል ለየአብያተክርስቲያናቱ እና ገዳማቱ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ላሉ ሁሉ እነዚህን ዕለታት በፀሎት እና በምዕላ እንዲያሳልፍ ተወስኗል" ሲሉ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶክተር) ለEOTC ቴሌቪዥን ጣቢያ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
ድሬ❤️

"ተዋዶ ያለበት እስላም ክርስቲያኑ
ከቶ አይዘነጋም ድሬ ላይ መሆኑ! "

በድሬዳዋ ሁሌም ቢሆን የነዋሪዎቿ #ፍቅር#አንድነት እና #አብሮነት ብሎም አሁናዊ የከተማዋ ሰላም ለሌሎች ምሳሌና ማሳያ ነው መባሉ በምክንያት ነው።

በጥምቀት ከተራ በዓል የእስልምና እምነት ተከታይ የሆኑ ወንድምና እህቶች በቀፊራ ፣ በለገሀሬ ፣ ኮኔል ፣ በድልድይ መጋላ እና በሌሎችም አካባቢዎች ለህዝበ ምእመኑ ውሀ፣ ኩኪሲችና ጣፍጭ ምግቦችን በማቅረብ እንኳን አደረሳችሁ ሲሉ ወንድማዊና ቤተሰባዊ ፍቅራቸውን ገልፀዋል።

ፎቶ ፦ ድሬ ፖሊስ ሚዲያ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ስምምነት

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ያጋጠመውን ፈተና ለመፍታት የተደረሰው ስምምነት ዝርዝር ፦

1. በኦሮሚያ ክልል በኦሮምኛ ቋንቋ ትምህርት፤ ቅዳሴ እና ሌሎችም አገልግሎቶች እንዲሰጡ የተጀመረው ሥራ የሕዝቡን ጥያቄ በሚመልስ መልኩ እንዲጠናከር። ለዚህም ከዚህ በፊት ከተደረገው በተጨማሪ አስፈላጊው በጀትና የሰው ኃይል እንዲመደብ።

2. በኦሮሚያና በሌሎች አካባቢዎች የተዳከሙ አብያተ ክርስቲያናት ቋንቋውን በሚያውቁ አገልጋዮችና በአገልግሎት እንዲጠናከሩ አስፈላጊው ዕቅድ ተዘጋጅቶ ከበፊቱ በበለጠ ተገቢው በጀትና የሰው ኃይል እንዲመደብ።

3. በኦሮሚያ እና በሌሎች አካባቢዎች የሚያገለግሉ ቋንቋውን የሚያውቁ አገልጋዮችን የሚያሠለጥኑ ተጨማሪ ኮሌጆች እና ማሠልጠኛዎች እንዲከፈቱ፣ የተከፈቱትም እንዲጠናከሩ እንዲደረግ።

4. ለኦሮሚያ አህጉረ ስብከት በቂ የሆነ የኦሮምኛ ቋንቋን የሚያውቁና በቋንቋው የሚያገለግሉ ኤጲስቆጶሳት በቀጣይ የግንቦት ርክበ ካህናት ተወስኖ እንዲሾሙ፡፡

5. ሦስቱ ሊቃነ ጳጳሳት ብጹዕ አቡነ ሳዊሮስ፣ ብጹዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ እና ብጹዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ወደ ቀደመ ሀገረ ስብክታቸውና የክነት ማዕረጋቸው እንዲመለሱ።

6. በሦስቱ አባቶች የተሾሙት አባቶች ቀድሞ ወደነበሩበት የክነት ማዕረግ ይመለሳሉ፡፡ ከእነርሱ ውስጥ በቤተ ክርስቲያን ሕግና ሥርዓት ተመዝነው የሚያሟሉት እንደገና በቅዱስ ሲኖዶስ እንዲሾሙ ይደረጋል።

7. በአስተዳደራዊ ጉዳዮች፣ በፋይናንስ ፣ በምደባ፣ በቅጥር የሚታዩ ክፍተቶችን በጥናት የወንጌል አገልግሎትን በሚያጠናክር መልኩ እናሻሽላለን።

8. የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት የበለጠ ለማጠናከርና ለትውልድ አርአያ የሚሆን ቤተ ክህነት እንዲኖረን ለማድረግ አሠራራችንን በጥናት አሻሽለን ቤተ ክርስቲያንን ለትውልድ እናሻግራለን፡፡

9. ጥላቻን የሚያባብሱ ጉዳዮችን ከማድረግ መቆጠብ ይገባል። ሚዲያዎች፣ አክቲቪስቶች፣ መምህራን እና አባቶች ፍቅርን ከሚያጠፋ፣ ጥላቻን ከሚያበዛና መለያየትን ከሚያሰፋ ነገር ሁሉ እንዲቆጠቡ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን። ይሄንን ተግባር ሆን ብለው የሚያደርጉትንም እናወግዛለን።

10. የገጠመን ፈተና ይበልጥ ውስጣችንን ለመፈተሽ፤ አንድነታችንን ለማጠናከር፤ ወንጌልን የበለጠ ለመስበክና የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ለማስፋፋት ለበጎ እንጠቀምበታለን።

በመጨረሻም #ፍቅር#ይቅርታ እና #አንድነት እንዲመጣ የደከማችሁትን ሁሉ በቤተ ክርስቲያን ስም እናመስግናለን። ዋጋችሁንም እግዚአብሔር እንዲከፍላችሁ እንጸልያለን።

@tikvahethiopia