TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በታጣቂዎች #ታግተው የነበሩት የ " ሰዴን ሶዶ " የወረዳ አመራር ተገድለው ተገኙ።

በኦሮሚያ ክልል፤ ደ/ምዕራብ ሸዋ ዞን፤ የሰዴን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ ከመኖሪያ ቤታቸው ታፍነው ከተወሰዱ ከሁለት ቀን በኃላ ተገድለው መገኘታቸው ተሰምቷል።

የሰዴን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ በቀለ ቃቻ ፤ ባለፈው ቅዳሜ ዕለት ከመኖሪያ ቤታቸው ታፍነው ከተሰወዱ በኋላ ማክሰኞ ተገድለው አስክሬናቸው መገኘቱን የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ በሰጠው ቃል ገልጿል።

ወረዳው ለግድያው በክልሉ የሚንቀሳቀሰውን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን ተጠያቂ አድርጓል ፤ እስካሁን ከታጣቂ ቡድኑ ዘንድ የተሰጠ አስተያየት የለም።

አቶ በቀለ ፤ ከታገቱ በኃላ ያገቷቸው ታጣቂዎች እንዲለቀቁ ' 10 ሚሊየን ብር ' መጠየቃቸውን ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ለጉዳዩ ቅርብ ከሆኑ ሰዎች መስማቱን ገልጿል።

የወረዳው የኮሙዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት ጉዳዩ ተጨማሪ ምርመራ የሚጠይቅ ቢሆንም ታጣቂዎቹ ለተወሰኑ ሰዎች በወረዳው አስተዳዳሪ ስልክ ደውለው እስከ 10 ሚሊዮን ብር መጠየቃቸውን አመልክቷል።

በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ወረዳ ውስጥ ግለሰቦችን በታጣቂዎች እያታገቱ ከ200 ሺህ ብር አንስቶ እስከ 500 ሺህ ብር ድረስ እንደሚጠየቅባቸው ፤ ከዚህ ባለፈ ማሰቃየት እና ግድያ እንደሚፈፀም ከወረዳው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በታጣቂዎች #ታግተው የነበሩት የ " ሰዴን ሶዶ " የወረዳ አመራር ተገድለው ተገኙ። በኦሮሚያ ክልል፤ ደ/ምዕራብ ሸዋ ዞን፤ የሰዴን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ ከመኖሪያ ቤታቸው ታፍነው ከተወሰዱ ከሁለት ቀን በኃላ ተገድለው መገኘታቸው ተሰምቷል። የሰዴን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ በቀለ ቃቻ ፤ ባለፈው ቅዳሜ ዕለት ከመኖሪያ ቤታቸው ታፍነው ከተሰወዱ በኋላ ማክሰኞ ተገድለው አስክሬናቸው መገኘቱን የደቡብ ምዕራብ…
በታጣቂዎች #ታግተው የነበሩት የሰዴን ሶዶ የወረዳ አመራር ተገድለው ተገኙ።

በኦሮሚያ ክልል ፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ፤ የሰዴን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ ከቤታቸው ታፍነው ከተወሰዱ ከሁለት ቀን በኃላ ተገድለው መገኘታቸው ተሰምቷል።

የሰዴን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ ቅዳሜ ዕለት ከመኖሪያ ቤታቸው ታፍነው ከተሰወዱ በኋላ ማክሰኞ ተገድለው መገኘታቸውን የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሃይሉ አብዶ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ተናግረዋል።

አቶ ኃይሉ ፤ " አቶ በቀለ ቃቻ በአዳማ ከተማ ስብሰባ ላይ ነበሩ። ባለፈው ቅዳሜ ወደ ቤተሰብ ተመለሱ ፤ በዕለቱ ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ላይ ከቤታቸው ባልታወቁ ሃይሎች ታፍነው ተወስደዋል "  ሲሉ ተናግረዋል።

ቅዳሜ ምሽት ከመኖሪያ ቤታቸው ታፍነው የተወሰዱት የወረዳው አስተዳዳሪ ላለፉት ሁለት ቀናት የት እንዳሉ ሳይታወቅ ቆይቶ ባለፈው ማክሰኞ ከቀኑ 8 ሰአት ላይ ተገድለው ተገኝተዋል ሲሉ ገልጸዋል።

የአቶ በቀለ አስክሬን በቶሌ ወረዳ፣ ኢሉ ወረዳ እና በበቾ ወረዳ መካከል በፀጥታ ኃይሎች አሰሳ መገኘቱ ተመላክቷል።

አቶ በቀለ ፤ የወረዳው አስተዳዳሪ በመሆን ለሁለት አመታት ማገልገላቸው ፤ ከዚያ በፊት በትውልድ አካባቢያቸው በዳዎ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ በመሆን ማገልገላቸውን አቶ ኃይሉ ገልጸዋል።

አቶ ኃይሉ ፤ ለ ' ግድያው ተጠያቂው ' በክልሉ ውስጥ የሚንቀሳቀሰው መንግሥት " ኦነግ - ሸኔ " የሚለው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ሃይል መሆኑን ጠቅሰዋል።

" አዎ፣ እንደ ህዝብ ጥቆማ እንደዛ የሚባል ነገር አለ። በተግባር ከወረዳችን ከተለያዩ ቦታዎች ሰዎች እየታገቱ ነው። የሚያግተው ይኸው አካል ነው። አንዳንድ ጠቆማዎችም አሉ፣ ታግተው የተለቀቁ ሰዎችም አሉ " ብለዋል።

መንግሥት 'ኦነግ ሸኔ' የሚለው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት  ስለ ውንጀላው እስካሁን የሰጠው አስተያየት የለም።

በመንግስት ባለስልጣናት እና በተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ላይ የሚፈፀሙ ግድያዎችን በተመለከት ግን ታጣቂ ቡድኑ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ሲያስተባብል ነበር።

" 10 ሚሊዮን ብር ተጠይቋል "

የሰዴን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ ቅዳሜ ዕለት ከቤታቸው ከታገቱ ከአንድ ቀን በኋላ ታጣቂዎቹ አቶ በቀለ ቃቻ እንዲለቀቁ ' 10 ሚሊየን ብር ' መጠየቃቸውን ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ለጉዳዩ ቅርብ ከሆኑ ሰዎች መስማቱን ገልጿል።

የወረዳው የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ኃይሉ ፤ ጉዳዩ ተጨማሪ ምርመራ የሚጠይቅ ቢሆንም ታጣቂዎቹ ለተወሰኑ ሰዎች በወረዳው አስተዳዳሪ ስልክ ደውለው እስከ 10 ሚሊዮን ብር መጠየቃቸውን መረጃዎች ጠቁመዋል ሲሉ ተናግረዋል።

ታጣቂዎቹ ለወረዳው አስተዳዳሪ አቶ በቀለ ቀደም ብለው የሰጡት ማስጠንቀቂያ / ዛቻ አለ ? ወይንም በግላቸው ደውለውላቸው የጠየቁት ገንዘብ አለ ? ተብለው የተጠየቁት አቶ ኃይሉ የአስተዳዳሪው ስልክ በታጣቂዎቹ እጅ ስለገባ ይሄን ለማወቅ አስቸጋሪ መሆኑን ተናግረዋል።

" ዛቻ ወይም ማስጠቀቂያ እየተነዛበት እንደሆነ ሪፖርት ቀርቦ የሚያውቅ አይመስለኝም " ሲሉ አክለዋል።

ታጣቂዎቹ የወረዳውን አስተዳዳሪ ከእገታ ለማስለቀቅ የጠየቁት ገንዘብ ተሰጥቷቸው እንደሆነ ግልፅ  የሆነ ነገር ባይኖርም የተገደሉት " የጠየቁት ገንዘብ ስላልተሰጠ " ነው የሚል ግምት ግን አለ።

አቶ ኃይሉ ግን " ከዚህ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም ነገር ግን በቀጣይ ምርመራ ይታወቃል " ሲሉ ተናግረዋል።

በሁለት ቀናት ውስጥ የጸጥታ ሃይሎች አስተዳደሪውን ለማስለቀቅ ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸው ተገልጿል።

የተገደሉት አስተዳዳሪ ከ30ዎቹ - 40ዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ባለትዳር እና የልጆች አባት ነበሩ።

" ለአንድ ግለሰብ 200 ሺህ፣ 300 ሺህ እና 500ሺ እየተጠየቀ ነው "

የወረዳው ኮሚኒኬሽን ፅህፈት ቤት ኃላፊው አቶ ኃይሉ ፤ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ነን የሚሉ የታጠቁ ሃይሎች (መንግሥት ኦነግ - ሸኔ የሚላቸው) በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ወረዳ ውስጥ ግለሰቦችን እያገቱ ብዙ ገንዘብ እየጠየቁ በማሰቃየትና በመግደል ላይ ናቸው ሲሉ ተናግረዋል።

" ፖለቲካ የማያውቁ እና ማንም ነገር ውስጥ የማይገቡ ገበሬዎችን በየቀኑ እያፈኑ ፤ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እየተጠየቀ ነው። " ያሉት አቶ ኃይሉ " ገንዘብ የሌለው ግለሰብ ሁለት መቶ ሺህ ፣ ሶስት መቶ ሺህ፣ አምስት መቶ ሺህ ብር ዘመዶቹ እየሰበሰቡ መስጠት የተለመደ ሆኗል " ሲሉ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ፤ ልጆቻቸውን የማገትና በአሰቃቂ ሁኔታ የመግደል ሁኔታ መጨመሩንም አስረድተዋል።

የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኃይሉ  አብዶ ፤ " መፍትሄው እርስ በእርስ ከመገዳደል ፤ አንድ ቋንቋ  እየተናገርን ከመጨራረስ ይልቅ በውይይት መፍታት ነው " ብለዋል።

መረጃውን ከ " ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ " ነው ያገኘነው።

@tikvahethiopia