TIKVAH-ETHIOPIA
ማዳበሪያ . . . " ከተማ ምትኖሩ ሰዎች የጤፍ ዋጋ እና አስፔዛ ሲጨምር ብቻ ሳይሆን የገበሬዎች ማዳበሪያ ሲጨምርም / ሲጠፋ መንግስትን ትኩረት እንዲያደርግ ልትጠይቁ ይገባል " - አብራራው (በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል - አብራራው) " ሰላም ለእናንተ ይሁን !! አንድ አሳሳቢ ሀገራዊ ጉዳይ አለ ፤ ነገር ግን ማንም ትኩረት ሰጥቶት ሲሰራ አላየውም ፤ እናም የሚመለከተው አካል ተመልክቶ መፍትሄ…
የማዳበሪያ ነገር . . .
መንግሥት ፤ የ " አፈር ማዳበሪያ " ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ለምርት ዘመኑ የሚያስፈልገውን ማዳበሪያ ለማቅረብ እየሰራ መሆኑን ቢገልፅም አሁንም በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ገበሬዎች በወቅቱ እየደረሳቸው እንዳልሆነ እየገለፁ ይገኛሉ።
የግብርና ሚኒስቴር ፤ ለምርት ዘመኑ የሚያሰፈልገውን የአፈር ማዳበሪያ ለማቅረብ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።
በ2015/16 ምርት ዘመን የሚውል 12.8 ሚሊዮን የአፈር ማዳበሪያ ግዥ ተፈጽሞም ወደ ሀገር ውስጥ የማጓኀጓዝ ስራ እየተሰራ ይገኛል ብሏል።
እንደ ግብርና ሚኒስቴር እና ኢትሎባድ መረጃ መሰረት ፦
- በቀን በአማካኝ 8 ሺህ ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ከጅቡቲ ወደብ ወደ ሀገር ውስጥ እየገባነው።
- በ13 ግዙፍ መርከቦች ተጓጉዞ ጅቡቲ ከደረሰ አጠቃላይ መጠን ከ677 ሺህ 678 ሜትሪክ ቶን (90 %) በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ገብቷል።
- እስከ ሰኔ 10/2015 ዓ.ም ድረስ ከ7.4 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ የደረሰ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ደግሞ 6.6 ሚሊዮን ኩንታል ሙሉ በሙሉ ሀገር ውስጥ ገብቶ እየተጓጓዘ ነው፡፡
- በመጪው 10 ቀናት በአራት / 4 መረከቦች 220 ሺህ ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ጅቡቲ ወደብ እንደሚደርስ ይጠበቃል። ሶስት መረከቦች መጫኛ ወደብ ላይ በመጫን ላይ ናቸው።
ግብርና ሚኒስቴር ፤ እስካሁን የማጓጓዝ ስራው በመኪና እና በባቡር በፍጥነት እየተከናወነ መሆኑን አዳማ ካለው ባቡሩ ጣቢያ እንደደረሰም ወደ ፦
- ኦሮሚያ፣
- አማራ
- ሲዳማ ክልሎች እየተጓጓዘ መሆኑን አመልክቷል።
" በክልሎች ያሉ የተለያዩ የህብረት ስራ ማህበራት የማጓጓዝ ስራውን በትኩረት እየሰሩ ነው " የሚለው የግብርና ሚኒስቴር " በቀጣይም ለምርት ዘመኑ የሚያስፈልገውን የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶናአርብቶ ለማቅረብ በትኩረት ይሰራል " ብሏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን አሁንም በክልል ያሉ አርሶ አደሮች " ማደበሪያ #በወቅቱ እየደረሰን አይደለም " በሚል ከፍተኛ ምሬት ላይ ናቸው።
ለአብነት በአማራ ክልል ያሉ አርሶ አደሮች በማዳበሪያ ችግር የተነሳ የእርሻ ጊዜያቸው እያለፈ መሆኑን አሁንም እየገለፁ ናቸው።
ጥያቄያቸውን በተደጋጋሚ ጊዜ በ "ሰላማዊ ሰልፍ" ቢገልጡም አሁንም ድረስ ችግራቸውን የሚፈታ እንዳልተገኘ በምሬት ተናግረዋል።
አርሶ አደሮቹ " የማደበሪያ ችግራችን አልተፈታም " በማለት በባሕር ዳር ላይ ለሦስተኛ ጊዜ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል።
አርሶ አደሮች የመጀመሪያው ዙር የማሽላ እና የበቆሎ የዘር ወቅት በማዳበሪያ እጥረት የተነሳ መዝራት እንዳልቻሉ እና ጊዜው እንዳለፈባቸው እየገለፁ የሚገኙ ሲሆን የቀጣይ የዘር ወቅት እንዳያልፍባቸው ድምፃቸውን ቢያሰሙም ምላሽ አላገኙም።
" ማሽላም አልዘራሁ፤ ዳጉሳም ተጎልጉሎ የማሽላውን ለዳጉሳ ጎለጎልሁ ። [ማዳበሪያ] የሚገዛልኝም አጣሁ ። ማሽላ በግንቦት ነበር የምንዘራ፤ ዝናቡ ሰጥቶ ነበር አመለጠኛ ። ገበያ ላይማ እየተሸሸገ የሚሸጥማ አለ ። ዐሥር ሺህ ዘጠን ሺህ አሉት ። ያንም እኔ አልሆንልኝ አለ፤ አጣሁት፤ አላገኘሁትም ። ጤፍ እና ዳጉሳ ዛሬ ወቅቱ ። ማሽላማ አለፈ ። " ሲሉ አንድ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ቃላቸውን የሰጡ አርሶ አደር ተናግረዋል።
የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የግብርና መምሪያ ፤ አጠቃላይ የማዳበሪያ እጥረት መኖሩን አልሸሸገም። ሆኖም የቀረበው ማዳበሪያ በተቀመጠው ስሌት መሰረት የድርሻቸውን ይወስዳሉ ብሏል።
መምሪያው ፤ " ክልሉ 43,280 አጸደቀልን። መጥቶ ኅብረት ሥራ ማኅበር የደረሰው ግን 16,343 ነው ፤ የሚታረሰው መሬት 15,000 በላይ ነው ፤ ይኼ ደግሞ በቆሎ አምራች ነው ። አንድ ኼክታር ሁለት ይፈልጋል ዳፕ ብቻ ። 16,000 ብቻ መጥቶ 43,000 ቢቀርብ ነው የተወሰነ ፍልጎቶችን ሊያረካ የሚችለው ። እና እጥረቱ በጣም ሰፊ ነው ። ያለው ግን በኮታቸው መሠረት፤ በድልድላቸው መሠረት እየተሰራጨ ነው። " ብሏል።
በአማራ ክልል እስካሁን ከ5 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ማዳበሪያ እንደተገዛ በክልሉ ግብርና ቢሮ በኩል ቢነገርም፤ አብዛኛው አርሶ አደር ግን እስካሁን በእጁ የገባ ነገር እንደሌለ ይናገራል።
ማዳበሪያው " በሕገወጥ መንገድ በከፍተኛ ዋጋ እየተሸጠ የግለሰቦች መጠቀሚያ ሆኗል " ሲሉም አርሶ አደሮቹ ምሬት እያሰሙ ናቸው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ ከአማራ ክልል፣ ከኦሮሚያ ክልል ቤተሰቦቹ አሁንም የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት ችግር ስለመኖሩ መልዕክቶችን እየተቀበለ ይገኛል።
" ምንም አይነት " የማዳበሪያ አቅርቦት የሌለባቸው አካባቢዎች መኖራቸውን በማመልከት ህዝቡን አርሶ የሚያበላው ገበሬ የከፋ ችግር ላይ ሳይወድቅ የሚመለከተው ሁሉ ችግሩን እንዲፈታ ጥሪ አቅርበዋል።
ከዚህ ቀደም (ከበርካታ ሳምንታት በፊት) እጅግ በርካታ የቤተሰብ አባላቶቻችን " ትኩረት ለገበሬው " በሚል የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት ችግር በፍጥነት እንዲፈታ ጥሪ አቅርበው ነበር።
በተለይም መንግሥት ፤ በማዳበሪያ ሽያጭ ላይ የተሰማሩ ህገወጥ አካላትን፣ በህገወጥ ስራ ውስጥ ያሉ የራሱን አካላት እንዲፈትሽ ብለው ነበር።
(ለትውስታ ከምዕራብ ጎጃም ከተላኩ መልዕክቶች አንዱ) ፦
" የጤፍ ዋጋ ፣ የኑሮ ውድነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እጅግ እየጨመረ ይገኛል።
በገበሬው ዘንድ እንደምክንያት የሚጠቀሰው ደግሞ መንግስት እያቀረበ ያለው የአፈር ማዳበሪያ በቀበሌ ኃላፊዎች አመቻችነት ቀጥታ በነጋዴው እጅ እንዲገባ እና ትክክለኛ ዋጋው በኩንታል 3500 ብር የተተመነ ቢሆንም በነጋዴው እጅ 9000 ብር መደረጉ ነው።
ገበሬው የሚፈልገውን የማዳበሪያ መጠን አለማግኘቱ የጤፍ ዋጋ እንዲሁም የኑሮ ውድነት ከዚህ ዓመት ይልቅ በሚቀጥለው መባባስ የማይቀር አመላካች ነው።
ስለሆነም የሚመለከተው አካል ትኩረት ቢሰጠው መልካም ነው። "
@tikvahethiopia @tikvah_eth_BOT

#Update #የመሬት_ሊዝ_ጨረታ " በ7 ክ/ከተሞች የመሬት ሊዝ ጨረታ አሸናፊዎች ከአፍታ ቆይታ በኃላ ይለያሉ " - የአ/አ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ላለፉት አምስት ዓመታት ተቋርጦ የነበረውን የመሬት ሊዝ ጨረታ ዛሬ አስጀምሯል። ይህንንም ተከትሎ ቢሮው በሁሉም ክፍለ ከተሞች 14 ነጥብ 13 ሄክታር መሬት በሊዝ ለማጫረት ማዘጋጀቱን…
Addis lissan .pdf
1.2 MB
#AddisAbaba
የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የ1ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ አሸናፊዎችን ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል።
ቢሮው በከተማዋ ላለፉት አምስት ዓመታት ቆሞ የነበረውን መሬትን በሊዝ ጨረታ የማስተላለፍ ተግባር ዳግም መጀመሩ አስታውሷል።
ከግንቦት 24/2015 ዓ/ም ጀምሮ ለስድስት ተከታታይ ቀናት በይፋ ተከፍቶ አሸናፊዎቹ የተለየውን የ1ኛው ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ አሸናፊዎችን ስም ዝርዝር ይፋ መደረጉን አሳውቋል።
በዚህ ጨረታ ዝቅተኛ ዋጋ የተመዘገበው በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሲሆን፣ ይህም በካሬ ሜትር 20 ሺህ ብር ነው፡፡
ከፍተኛው በአራዳ ክፍለ ከተማ ሲሆን በካሬ ሜትር 414 ሺህ ብር እነደሆነ ተገልጿል።
ለ21 ሺህ 636 ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የተሸጠ ሲሆን ከእነዚህ ወስጥ 11 ሺህ 437 ሰነዶች ተሞልተው ሳጥን ውስጥ ገብተዋል።
ሙሉ የጨረታውን አሸናፊዎች ስም ዝርዝር ከላይ በተያያዘው PDF ፋይል ይመልከቱ።
Credit : Addis Media Network / Addis Lisan
@tikvahethiopia

ጉዞዎን በካርዶ!
በሚጠቀሙት የትራንስፓርት አገልግሎት ላይ የብርሃንን ኤም-ፓሶችን ይጠይቁ ፣ ባንካችን ላጠቃቀም ቀላል እና ምቹ የሆኑ ኤም-ፖሶችን አቅርቦሎታል
በብርሃን ካርዶ ይጠቀሙ ጥሬ ገንዘብ አልያዝኩም ከሚል ሀሳብ እና ጭንቀት ይረፉ!
#ብርሃን_ባንክ
እንደ ስማችን ብርሃን ነው ስራችን

#MY_MUSIC_SHOP
🎹 All kind of musical Instruments & Accessories.
🎧 All kinds of Studio Recording Equipments!
🎸BOX GUITAR, 🎸LEAD GUITAR, 🎸BASS GUITAR, 🎹STAGE KEYBORDS, 🎤 MICROPHONES, 🎧HEADPHONES
Join 👉 https://t.iss.one/dagmusical
☆ Contact. ☎️ +251939854210
🏠 Megenagna Zefmesh Grand Mall 3rd floor #325.

በጊዜያዊነት ታግደዋል !
" ብራስ ዩዝ አካዳሚ " እና " ቅዱስ ሚካኤል ትምህርት ቤቶች ከክፍያ ጭማሪ ጋር በተያያዘ በጊዜያዊነት ታገዱ።
የአዲስ አበባ ትምህርት እና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ሁለት ትምህርት ቤቶችን በጊዜያዊነት አግዷል።
የታገዱት " ብራስ ዩዝ አካዳሚ " እና ቅዱስ ሚካኤል ትምህርት ቤቶች ናቸው።
ለምን ታገዱ ?
ብራስ ዩዝ አካዳሚ ፦
ት/ቤቱ ከክፍያ ጭማሪ ጋር በተያያዘ ከወላጆች ጋር ስምምነት ሊደርስ አልቻለም ተብሏል።
ት/ቤቱ ያቀረበው 40 % እና ወላጆች ለቅድመ መደበኛ 25 % ለመጀመሪያ ደረጃ 30 % ያቀረቡ ሲሆን በዚሁ ጉዳይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
ባለስልጣን መስሪያ ቤ/ት የሁለቱንም ወገን ምክንያት ታሳቢ በማድረግ በ30% ለማስማማት መሞከሩን በዚህም ወላጆች ቢስማሙ ት/ቤተ ግን የማደራደሪያ ሃሳቡን አልተቀበለም።
ከወላጆች ጋር በ2016 ዓ/ም የትምህርት አገልግሎት ክፍያ ላይ የጋራ ስምምነት ላይ ሳይደረስ ለ2016 ዓ/ም የተማሪ ምዝገባ ማከናወን የማይቻል በመሆኑ ተቋሙ በጊዜያዊነት መታገዱን ባለስልጣን መ/ቤቱ አሳውቋል።
ቅዱስ ሚካኤል ትምህርት ቤቶች ፦
ይህም ት/ቤቱ በተመሳሳይ ከክፍያ ጭማሪ ጋር በተያያዘ ከወላጆች ጋር ስምምነት ሊደርስ አልቻለም ተብሏል።
ት/ቤቱ ያቀረበው 80 % ጭማሪ ሲሆን እና ወላጆች 50 % እንዲቀራረቡ ሰፊ ውይይት ለማድረግ ቢሞከርም ማስማማት አልተቻለም።
ባለስልጣን መስሪያ ቤ/ት የሁለቱንም ወገን ምክንያት ታሳቢ በማድረግ በ60% ለማስማማት መሞከሩን በዚህም ወላጆች እና ተወካዮቻቸው ቢስማሙ ት/ቤቱ ግን የማደራደሪያ ሃሳቡን አልተቀበለም።

ምንጭ፦ የአዲስ አበባ ትምህርት እና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን

የመውጫ ፈተና !
ከ168 ሺ በላይ የ2015 ዓ.ም ዕጩ ተመራቂዎች በቀጣይ ወር የሚሰጠውን ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ይወስዳሉ።
የመውጫ ፈተናው ከሐምሌ 03 እስከ 08/2015 ዓ.ም በኦንላይን በ208 የትምህርት መስኮች ይሰጣል።
መንግሥት ከዚህ ቀደም ፈተናው ለ240 ሺህ በላይ ዕጩ ተመራቂዎች ይሰጣል ብሎ የነበረ ቢሆንም፤ ፈተናውን ለመውሰድ 168,345 ተማሪዎች ብቻ #መስፈርት ማሟላታቸው ተገልጿል።
ከ44 የመንግሥት እና ከ161 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተውጣጡ ዕጩ ተመራቂዎች ፈተናውን በ82 የመፈተኛ ማዕከላት ውስጥ ይወስዳሉ።
ከሐምሌ 09/2015 ዓ.ም ጀምሮ ውጤት ይገለጻል ተብሏል።
በሌላ በኩል ፤ የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎችን የተመለከተ መረጃ ለትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የላኩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተፈታኝ ተማሪዎቻቸውን የመግቢያ ስም እና የይለፍ ቃል መውሰድ እንደሚችሉ ተገልጿል።
ባለሥልጣን መ/ቤቱ ከትምህርት ሚኒስቴር የመጣለትን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተፈታኝ ተማሪዎች የመግቢያ ስም እና የይለፍ ቃል እንዲወስዱ ለተቋማቱ ጥሪ አድርጓል፡፡
More : @tikvahuniversity

ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይከተሉ!
=====================
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ስምና አርማ በመጠቀም በሚከፈቱ ሀሰተኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች የተለያዩ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት የሌብነት ተግባር የሚፈፅሙ አጭበርባሪዎች አሉ፡፡
በመሆኑም የባንኩን ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገፆች ብቻ በመከተል ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ ያግኙ፤ ከአጭበርባሪዎች ይጠበቁ!
የባንኩ ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች፡
• Facebook፡- https://www.facebook.com/combanketh
• YouTube፡- https://www.youtube.com/commercialbankofethiopia
• LinkedIn፡- https://www.linkedin.com/company/commercialbankofethiopia
• Twitter፡- https://twitter.com/combankethiopia
• Telegram፡- https://t.iss.one/combankethofficial
• Instagram፡- https://www.instagram.com/commercialbankofethiopia/
• tiktok:- https://www.tiktok.com/@commercialbankofethiopia
=====================
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ስምና አርማ በመጠቀም በሚከፈቱ ሀሰተኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች የተለያዩ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት የሌብነት ተግባር የሚፈፅሙ አጭበርባሪዎች አሉ፡፡
በመሆኑም የባንኩን ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገፆች ብቻ በመከተል ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ ያግኙ፤ ከአጭበርባሪዎች ይጠበቁ!
የባንኩ ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች፡
• Facebook፡- https://www.facebook.com/combanketh
• YouTube፡- https://www.youtube.com/commercialbankofethiopia
• LinkedIn፡- https://www.linkedin.com/company/commercialbankofethiopia
• Twitter፡- https://twitter.com/combankethiopia
• Telegram፡- https://t.iss.one/combankethofficial
• Instagram፡- https://www.instagram.com/commercialbankofethiopia/
• tiktok:- https://www.tiktok.com/@commercialbankofethiopia
#MY_MUSIC_SHOP
🎹 All kind of musical Instruments & Accessories.
🎧 All kinds of Studio Recording Equipments!
🎸BOX GUITAR, 🎸LEAD GUITAR, 🎸BASS GUITAR, 🎹STAGE KEYBORDS, 🎤 MICROPHONES, 🎧HEADPHONES
Join 👉 https://t.iss.one/dagmusical
☆ Contact. ☎️ +251939854210
🏠 Megenagna Zefmesh Grand Mall 3rd floor #325.
🎹 All kind of musical Instruments & Accessories.
🎧 All kinds of Studio Recording Equipments!
🎸BOX GUITAR, 🎸LEAD GUITAR, 🎸BASS GUITAR, 🎹STAGE KEYBORDS, 🎤 MICROPHONES, 🎧HEADPHONES
Join 👉 https://t.iss.one/dagmusical
☆ Contact. ☎️ +251939854210
🏠 Megenagna Zefmesh Grand Mall 3rd floor #325.
ለሃጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን ድጋፍ ተደረገ።
ኦሮሚያ ባንክ ለ " ሃጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን " ስራ ስኬት አንድ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን አሳውቋል።
ድጋፉን የሃጫሉ ሁንዴሳ ባለቤትና የፋውንዴሽኑ የቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ ፋንቱ ደምሶ ከኦሮሚያ ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተፈሪ መኮንን እጅ ተቀብለዋል።
ባንኩ ፤ ለሃጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን የተደረገው ድጋፍ የባንኩ የማህበራዊ ሃላፊነት ስራ አንዱ አካል መሆኑን ገልጿል።
ኦሮሚያ ባንክ ባለፈው አመትም ለፋውንዴሽኑ ተመሳሳይ ድጋፍ ማድርጉን አስታውሷል።

" . . . ግድያው መከላከያን በካደ አንድ ግለሰብ የተፈጸመ እንጂ በሠራዊቱ ደረጃ የተፈጸመ አይደለም " - የሶማሌ ክልል መንግስት ኮሚኒኬሽን
ከትላንት በስቲያ በሶማሌ ክልል፣ ቀብሪደኀር ከተማ አንድ የመከላከያ ሠራዊትን ከድቶ ከካምፕ ያመለጠ ነው የተባለ አባል ድንገት ተኩስ በመክፈት አራት ሰዎችን ገድሎ ሶስት ሰዎችን ማቁሰሉ ተሰምቷል።
የክልሉ ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ለቪኦኤ ሬድዮ በሠጠው ቃል ፤ ድርጊቱን የፈጸመው ወታደር ከካምፕ #አምልጦ የጠፋና ለሦስት ቀናት ክትትል ሲደረግበት የቆየ እንደሆነ ገልጾ አስቀድሞ ተኩሶ የመታውም ተከታትለው የደረሱበትን የቀብሪ ደኀር ነዋሪ እና የከተማዋን አመራር አባል ነው ሲል ገልጿል።
ግድያውን የፈጸመው ወታደር ተጨማሪ ጉዳት ከማድረሱ በፊት በመከላከያ ሠራዊት አባላት ርምጃ እንደተወሰደበት ተገልጿል።
የሶማሌ ክልል መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ግድያውን የፈጸመው ወታደር ከ3 ቀናት በፊት ከመከላከያ ካምፕ ያመለጠና ክትትል እየተደረገበት የነበረ የመከላከያ ሠራዊት አባል መሆኑን ገልጾ " ግድያው መከላከያን በካደ አንድ ግለሰብ የተፈጸመ እንጂ በሠራዊቱ ደረጃ የተፈጸመ አይደለም " ብሏል።
በሌላ በኩል የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) ባወጣው መግለጫ ፤ ከቀብሪድሃር ከተገደሉት አራት ሰዎች ሶስቱ ፓርቲው አባላት እንደነበሩ አንዱ ሰው ደግሞ የብልፅግና ፓርቲ አመራር እንደነበር ገልጿል።
የፌዴራል እና የክልሉ መንግሥት እንዲሁም የጦር ሰራዊቱ ድርጊቱን በፍጥነት አጣርተው እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቋል።
ባለፉት ስድስት ወራት በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ወቅት አካባቢውን ለቆ የነበረው መከላከያ ሠራዊት ወደ ሶማሌ ክልል ከተመለሰ በኋላ ይህን መሰል ጥቃት በልዩ ልዩ ከተሞች እየተሰማ ነው ሲል ኦብነግ በመግለጫው አመልክቷል።
ኦብነግ፤ የሠራዊቱ ካምፖች ከከተሞች እንዲርቁና የመከላከያ አባላት ትጥቅ ይዘው ወደ ከተማ ከመግባት እንዲከለከሉ ጠይቋል።
የሶማሌ ክልል ሕዝብ በዘመነ " ኢሕአዴግ " በርካታ ጅምላ ጭፍጨፋዎች እንደተፈጸሙበት ያስታወሰው ኦብነግ ዛሬም የመከላከያ ሠራዊቱን እንደ ጠላቱ እንዲያይ ከሚያደርጉ አካሔዶች መቆጠብ ተገቢ ነው ሲል አስጠንቋል።
ተመሳሳይ ጥቃቶች ዳግም እንዳይፈጸሙ ርምጃዎች መወሰድ አለባቸውም ብሏል።
ትላንት የመከላከያ ሠራዊት አመራሮችና የሶማሌ ክልል አመራሮች የቀብሪደኀር ከተማ ነዋሪዎችን ሰብስበው ስለ ጉዳዩ እንዳወያዩዋቸው የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታውቀዋል።
መረጃው የቪኦኤ ሬድዮ አማርኛ አገልግሎት ነው።
ፎቶ፦ ኦብነግ

የ3 ዓመት ህፃን ልጅ #አግቶ ቤተሰቦቹ 500 ሺህ ብር እንዲያመጡ ሲጠይቅ የነበረው አጋች በቁጥጥር ስር ዋለ።
በአማራ ክልል፤ ማዕከላዊ ጎንደር ዞን የቆላድባ ከተማ ነዋሪ የሆነው አቶ ደጀን አረጋ የ3 ዓመት ልጅ ህፃን አማኑኤል ወንድማገኝን ከደብረ ማርቆስ ከተማ 06 ቀበሌ በማገት ወደ ጠገዴ ወረዳ እርጎየ ቀበሌ ጫካ ውስጥ ይዞ ይገባል።
ህፃኑን በጫካው ውስጥ ለ7 ቀን ያክል ይዞ ቤተሰቦቹን 500 ሺህ ብር እንዲከፍሉ ሲጠይቅ ከቆየ በኃላ ፖሊስ ባደረገው ኦፕሬሽን ህፃኑን ከአጓቾች እጅ ማስለቀቅ ችሏል።
ፖሊስ ህፃኑ ታግቶ የነበረበትን ጫካ በመክበብ እና የተኩስ ልውውጥ በማድረግ ለጊዜው ዋናው አጋች ቢያመልጥም የጉዳዩ ተባባሪ እንደሆነ የተነገረው ጣማለው አስፋ የተባለ ግለሰብ ህፃኑን እንደያዘ በቁጥጥር ስር ማዋል ችሏል።
ዋናው አጋች አቶ ደጀን አረጋን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተደረገው እንቅስቃሴም ግለሰቡን ሰኔ 14 በቁጥጥር ማዋል ተችሏል።
የሶሮቃ ንዑስ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት ታግቶ የነበረውን ህፃን ለቤተሰቡ ካስረከበ በኃላ የማህበረሰቡ እሴትና ባህል መገለጫ ያልሆነ አፀያፊ ተግባር በዋና ተዋናይነት ፈፅሟል በሚል የተጠረጠረውን ደጀን አረጋን በቁጥጥር ስር ለማዋል የተባባሪ አጋች ጣማለው አስፋ ቤተሰቦች ጉዳዩን በዋናነት እንዲከታተሉና ጥቆማ እንዲሰጡ ማድረጉን ገልጿል።
ሌሎች ልዩ ልዩ ዘዴዎችንም በመጠቀም ባደረገው ክትትል ሰኔ 14/2015 ዓ.ም ከአካባቢው ሚሊሻና ማህበረሰብ ጋር በመተባበር ጠገዴ ወረዳ እርጎየ ቀበሌ ልዩ ስሙ " እምባ ጓዳድ " ከተባለ ቦታ ደጀን አረጋን በቁጥጥር ስር ማዋል ችሏል።
የሶሮቃ ንዑስ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤትም ጉዳዩን እያጣራ መሆኑን ያሳወቀ ሲሆን ተጠርጣሪውን በህግ ቁጥጥር ስር ለማዋል ሲባል የአካባቢው ማህበረሰብና መላው የፀጥታ መዋቅር ላደረገው ትበብር ምስጋና አቅርቧል።
በዚህና መሰል የወንጀል ተግባራት ላይ በሚሰማሩ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ በቀጣይም በተጠናከረ መንገድ ርብርብ እንደሚደረግ አሳውቋል።
መረጃው የጠገዴ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ነው።

#RosewoodFurniture
በዘመናዊ ማሽነሪ እና በ3D ዲዛይን የታገዘ፣ ለኣጠቃቀም ምቹ እና ወቅቱን የጠበቁ ዘመናዊ የፈርኒቸር ስራዎች !
ስራዎቻችንን ለማየት ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.iss.one/R0seWood
https://t.iss.one/R0seWood
https://t.iss.one/R0seWood
👉🏼 ስልክ : 📲 0905848586
👉🏼 ኣድራሻ : 📍4 ኪሎ አምባሳደር ሞል 2ኛ ፎቅ
📍ሩፋኤል ቤተክርስቲያን ከፍ ብሎ
ሮዝዉድ ፈርኒቸር 🙌

በታጣቂዎች #ታግተው የነበሩት የ " ሰዴን ሶዶ " የወረዳ አመራር ተገድለው ተገኙ።
በኦሮሚያ ክልል፤ ደ/ምዕራብ ሸዋ ዞን፤ የሰዴን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ ከመኖሪያ ቤታቸው ታፍነው ከተወሰዱ ከሁለት ቀን በኃላ ተገድለው መገኘታቸው ተሰምቷል።
የሰዴን ሶዶ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ በቀለ ቃቻ ፤ ባለፈው ቅዳሜ ዕለት ከመኖሪያ ቤታቸው ታፍነው ከተሰወዱ በኋላ ማክሰኞ ተገድለው አስክሬናቸው መገኘቱን የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ በሰጠው ቃል ገልጿል።
ወረዳው ለግድያው በክልሉ የሚንቀሳቀሰውን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን ተጠያቂ አድርጓል ፤ እስካሁን ከታጣቂ ቡድኑ ዘንድ የተሰጠ አስተያየት የለም።
አቶ በቀለ ፤ ከታገቱ በኃላ ያገቷቸው ታጣቂዎች እንዲለቀቁ ' 10 ሚሊየን ብር ' መጠየቃቸውን ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ለጉዳዩ ቅርብ ከሆኑ ሰዎች መስማቱን ገልጿል።
የወረዳው የኮሙዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት ጉዳዩ ተጨማሪ ምርመራ የሚጠይቅ ቢሆንም ታጣቂዎቹ ለተወሰኑ ሰዎች በወረዳው አስተዳዳሪ ስልክ ደውለው እስከ 10 ሚሊዮን ብር መጠየቃቸውን አመልክቷል።
በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ወረዳ ውስጥ ግለሰቦችን በታጣቂዎች እያታገቱ ከ200 ሺህ ብር አንስቶ እስከ 500 ሺህ ብር ድረስ እንደሚጠየቅባቸው ፤ ከዚህ ባለፈ ማሰቃየት እና ግድያ እንደሚፈፀም ከወረዳው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።