TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የመውጫ ፈተና !

ከ168 ሺ በላይ የ2015 ዓ.ም ዕጩ ተመራቂዎች በቀጣይ ወር የሚሰጠውን ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ይወስዳሉ።

የመውጫ ፈተናው ከሐምሌ 03 እስከ 08/2015 ዓ.ም በኦንላይን በ208 የትምህርት መስኮች ይሰጣል።

መንግሥት ከዚህ ቀደም ፈተናው ለ240 ሺህ በላይ ዕጩ ተመራቂዎች ይሰጣል ብሎ የነበረ ቢሆንም፤ ፈተናውን ለመውሰድ 168,345 ተማሪዎች ብቻ #መስፈርት ማሟላታቸው ተገልጿል።

ከ44 የመንግሥት እና ከ161 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተውጣጡ ዕጩ ተመራቂዎች ፈተናውን በ82 የመፈተኛ ማዕከላት ውስጥ ይወስዳሉ።

ከሐምሌ 09/2015 ዓ.ም ጀምሮ ውጤት ይገለጻል ተብሏል።

በሌላ በኩል ፤ የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎችን የተመለከተ መረጃ ለትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን የላኩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተፈታኝ ተማሪዎቻቸውን የመግቢያ ስም እና የይለፍ ቃል መውሰድ እንደሚችሉ ተገልጿል።

ባለሥልጣን መ/ቤቱ ከትምህርት ሚኒስቴር የመጣለትን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተፈታኝ ተማሪዎች የመግቢያ ስም እና የይለፍ ቃል እንዲወስዱ ለተቋማቱ ጥሪ አድርጓል፡፡

More : @tikvahuniversity