TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ እና በክልሎች መካከል #ግጭት በቀሰቀሱ እና #ወንጀል በፈጸሙ ግለሰቦችና ቡድኖች ላይ የተደራጀ ምርመራ ማድረጉን ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ተናግሯል፡፡ አቃቤ ሕግ ብርሃኑ ጸጋየ ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት እንዳሉት እነዚህ አካላት በቅርቡም ክስ ይመሰረትባቸዋል፡፡ ክሱ ከጀርባ ገንዘብ ድጋፍ ያደረጉ እና ያስተባበሩ አካላትንም ያካትታል፡፡ ምርመራው የተካሄደው በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን እና ቡራዩ፣ በደቡብ ክልል ጊዴኦ ዞን፣ በሶማሌ ክልል በጅግጅጋ የተለያዩ ዞኖች፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በሃዋሳ እና አዲስ አበባ ከተሞች በተፈጸሙ ወነጀሎች ላይ ነው፡፡

በተያያዘ ዜና...

እስካሁን ይሙቱ ይኑሩ የማይታወቁ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች እንዳሉ ዐቃቤ ሕጉ አስታውቀው የብሄራዊ ዕርቅ ኮሚሽን ደብዛቸው ስለጠፉ ሰዎች መፍትሄ ያመጣ ይሆናል ሲሉ ተስፋቸውን ገልጸዋል፡፡

Via~wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

በጅግጅጋና አካባቢው #ብሔርን መሰረት አድርጎ በተፈጸመው #ወንጀል ዙሪያ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳደር በተጨማሪ ሌሎች #በቁጥጥር ስር የሚውሉ አካለትም መኖራቸው ታውቋል።

ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ እና የፌዴራል ፖሊስ ከሀምሌ 28 እሰከ 30 በሶማሌ ክልል በጅግጅግናና ሌሎች ዞኖች ላይ ብሔርን መሰረት አድርጎ በተፈጸመው ወንጀል ዙሪያ በጋራ ሲያደርጉት የቆዩትን የምርመራ ስራ አጠናቀዋል።

ከተቋሙ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው፤ ከሀምሌ 28 እስከ 30 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት በጅግጅጋና ሌሎች ዞኖች ላይ ብሄርን መሰረት አድርጎ በተፈጸመው ከባድ የወንጀል ድርጊቶች ዙሪያ የድርጊቱ ተሳታፊ የነበሩ በርካታ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በዚሁ የምርመራ ውጤት መሰረት ተጨማሪ ትልልቅ ወንጀሎች እንደተገኙ የታወቀ ሲሆን፤ ይህንን ተከትሎም በቁጥጥር ስር የሚውሉ ተጨማሪ ግለሰቦች መኖራቸውም ታውቋል።

የምርመራው ውጤት በመጠናቀቁም በቁጥጥር ስር ያሉትን የክልሉን የቀድሞ ርዕሰ መስተዳደር ጨምሮ ሌሎች አካላት ላይ ክስ መመስረቱ እንደሚቀጥል ተጠቁሟል።

የምርመራ ሂደትንና ውጤቱን በተመለከተም አርብ (ጥር 17 ቀን 2011 ዓ.ም) በጠቅላይ ቃቤ ህግ ለጋዜጠኞች #መግለጫ ተሰምቷል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአገር መከላከያ ሰራዊት‼️

የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላት የመለያ ደንብ ልብስ የቀለምና የዲዛይን ለውጥ ሊደረግበት መሆኑን የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ሜጀር ጀኔራል #አብዱራህማን_እስማኤል ገለጹ።

የመከላከያ ሰራዊቱን የመለያ ደንብ ልብስ በመልበስ በሰራዊቱ ስም #ወንጀል የሚፈፅሙ አካላትን #ለመቆጣጠር ያስችላልም ተብሏል።

የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ሜጀር ጀነራል አብዱራህማን እስማኤል ለኢዜአ እንዳሉት፤ የመከላከያ ሰራዊቱን የመለያ ደንብ ልብስ ጥራትና ደረጃውን በጠበቀ የቀለምና ዲዛይን ለውጥ ሊደረግበት ነው።

ፋውንዴሽኑ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 179/2002 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ለሰራዊቱ አልባሳትና ሌሎች ወታደራዊ ግብዓቶችን በማምረት ወይም ገዝቶ ያቀርባል ብለዋል።

የመከላከያ ሰራዊት አባላት የሚወዱት፣ በጥራት፣ በቀለምና በዲዛይን የተሻለ የመለያ ልብስ እንዲሆን ከተለያዩ አገሮች ተመክሮ መወሰዱን ገልጸዋል።

የመከላከያ ጥናትና ምርምር ማዕከል ሃላፊ ብርጋዴር ጀኔራል #ተሾመ_ገመቹ በበኩላቸው የመከላከያ ሰራዊቱን አልባሳት መልበስ የሚችለው የሰራዊቱ አባል ብቻ ቢሆንም ተገቢ ቁጥጥር ባለመደረጉ የማይመለከታቸው ግለሰቦች ለብሰውት ተስተውሏል።

አዳዲስ አልባሳት በሚቀርቡበት ወቅት አሮጌዎቹ በአግባቡ ሳይወገዱ በመቅረታቸው ልብሱ በማይመለከታቸው አካላት እጅ ገብቶ የሰራዊቱን ስምና ክብር የሚያጎድፉ የተለያዩ ወንጀሎች እየተፈጸሙበት መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም በቀጣይ በሰራዊቱ አልባሳት ላይ የሚደረገው የቀለም ለውጥ እንዲሁም አዲስ አልባሳት ሲሰጥ ችግሩን ለመፍታት የሚያስቸሉ እርምጃዎች እንደሚወሰዱ ነው ያመለከቱት።

የመከላከያ ሰራዊቱን የመለያ ደንብ ልብስ በመልበስ ወንጀል የሚፈጽሙ አካላት ካሉ በወንጀል እንደሚጠየቁ ተናግረዋል።

ኅብረተሰቡም የመከላከያ ሰራዊቱን የመለያ ደንብ ልብስ መልበስ የሚችለው ሰራዊቱ ብቻ መሆኑን ተረድቶ የማይገባውን ልብስ ባለመልበስ ወንጀል እንዳይፈጸም ሊተባበር እንደሚገባ አሳስበዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ...

"ኢትዮጵያ ውስጥ #ወንጀል ሰርቶ መንግስት ወንጀለኛ መሆኑ መንግስት ካወጀ በኋላ ያልታሰረ ግለሰብ የለም፡፡ ልዩነቱ በመንግስት ቀለብ እያቀረበለት እስር በመንግስት እስር ቤት መሆኑና እራሱን ማሰሩ ነው፡፡ በእኔ እምነት ሁሉም ታስሯል፡፡ እንደውም በመንግስት እስር ቤት የታሰሩ ግለሰቦች ቤተሰባቸው እየተጠየቃቸው ስፖርት እየሰሩ ነው ያሉት፡፡ እራሳቸውን ያሰሩ ግን ይሄንም ዕድል አላገኙም፡፡ የጊዜ ነገር እንጂ ወንጀል ሰርቶ ተሸሽጎ የሚቀር የለም፡፡"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በክልሉ #ወንጀል ሰርተው የተደበቁ አሉ፡፡ ይሄንን ያስተባበረ ያቀናበረ ተልዕኮ የሰጠ እጁን ያስገባ አካል ካለ ተጣርቶ #ለህግ ይቀርባል፡፡" የሀረሪ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲ በድሪ ለአዲስ ዘመን የተናገሩት!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ማስጠንቀቂያ

የድምፅ መስጫ ቁሳቁስ ታሽጎ የሚሄድበትን ሳጥን ፦
- መክፈት
- ማንቀሳቀስ
- መቁረጥ
- ውስጡን ማየት ከፍተኛ የሆነ #ወንጀል ነው።

ምርጫ ቦርድ ለሁሉም ምርጫ አስፈፃሚዎች፣ ወረዳ ላይ ያሉ ዝቅተኛ እርከን ላይ የሚሰሩ የመንግስት አካላት (ይከፈት እንየው የሚሉ) በሙሉ ከፍተኛ #ማስጠንቀቂያ ሠጥቷል።

በማንኛውም ሁኔታ በምርጫ ክልሎች ላይ ችግር ተፈጥሮ ከተገኘ ወደድጋሚ ምርጫ እንደሚሄድ መታወቅ አለበት ብሏል ቦርዱ ፤ አክሎም የድጋሚ ምርጫ ለሀገር ሃብት ጠቃሚ ስላልሆነ፣ ቦርዱም ብዙ ገንዘብ ስለሚያባክን ከድምፅ መስጫ ቁሳቁስ ጋር በተገናኘ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስቧል።

#TikvahEthiopia #TikvahFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NationalExam የ12ኛ ክፍል " የተፈጥሮ ሳይንስ " ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ማዕከላት መግባት ጀምረዋል። ተማሪዎች ነገ ተጠቃለው የሚገቡ ሲሆን ጥቅምት 07/2015 ዓ.ም ገለጻ (ኦሬንቴሽን) ይሰጣቸዋል። ከጥቅምት 08 እስከ 11 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ፈተናቸውን ይወስዳሉ። ከዚሁ ከሁለተኛ ዙር ፈተና ጋር በተያያዘ የባለፉት ክፍተቶች መታረም ያለባቸው ሲሆን፤ ትምህርት ሚኒስቴር  ሴት ተፈታኝ…
#ማስታወሻ

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፤ " የፈተና ስርቆት እና ኩረጃ ከፍተኛ የደንብ ጥሰትና #ወንጀል " መሆኑን የሚገልፅ ሲሆን እንዲህ ያለው ድርጊት በህግ እንደሚያስጠይቅ ያስገነዝባል።

የማህበረሰብ የጋራ ሀብት በሆነው ፈተና ላይ ሚፈጸም ማንኛውንም አይነት ወንጀል በጋራ መከላከል ይገባል ይላል አገልግሎቱ።

የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የብሔራዊ ፈተና ከማክሰኞ ጥቅምት 8 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ እስከ አርብ ጥቅምት 11 ቀን 2015 ዓ/ም ድረስ ይሰጣል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ምዕራባውያን እንግዳ የሆነ ባህል (የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት) እንድንፈቅድ #ማዕቀብ በመጣል ጫና ያሳድራሉ " - ፕሬዜዳንት ሙሴቬኒ የኡጋንዳ ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ምዕራባውያን አገራት የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን መብቶች በአፍሪካ አገራት ላይ በኃይል ለመጫን እየጣሩ ነው ሲሉ ወቅሰዋል። ሙሴቬኒ ይህን ያሉት አገራቸው የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በተመለከተ አዲስ ሕግ እያረቀቀች ባለችበት ወቅት ነው።…
#Update

የኡጋንዳ ፓርላማ በአገሪቱ ውስጥ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ #ወንጀል እንዲሆን የሚያደርገውን ረቂቅ ሕግ አጸደቀ።

ሕጉ ምን ይዟል ?

- ማንኛውንም ራሱን በተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት አፍቃሪነት የመደበ፣ ወይም የጾታ ለውጥ ያስደረገ እንዲሁም በእንግሊዝኛ ምሕጻራቸው ኤል-ጂ-ቢ-ቲ-ኪው ዝርዝር ውስጥ የሚካተት የጾታ ዝንባሌ ያለው ዜጋን ሁሉ ወንጀለኛ ያደርጋል።

- በጸደቀው አዲሱ ሕግ መሠረት የተመሳሳይ ጾታ ዝንባሌ ያለው ዜጋ #የረጅም_ጊዜ_እስር ይጠብቀዋል።

- የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን በጉያው ያቀፈ ፣ በቤተሰብ ደረጃ #ያስጠለለ ፣ ወዳጃቸው የሆነ ወይም አብሯቸው ያለ ሰው “እከሌ እና እከሌ” ብሎ ለሕግ አካላት ማንነታቸውን የማጋለጥ ግዴታን በሌሎች ላይ ይጥላል።

- በዚህ ሕግ ልጆችን ለዚሁ ለተመሳሳይ ጸታ ያጨ ወይም ያስተላለፈ #የእድሜ_ይፍታህ ፍርድ ይጸናበታል።

- " በተመሳሳይ ጸታ መብት " ዙርያ የሚሠሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ግንኙነቱን የሚያበረታታ ማንኛውንም የሕትመት ውጤት ማተም አልያም በሌሎች የመገናኛ ብዙኃን ማሠራጨት አይችሉም። ይህን ካደረጉ በሕግ ተጠያቂ ይሆናሉ።

በምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኡጋንዳ የተመሳሳይ ጾታ ቀድሞም ሕገ ወጥ ተደርጎ ነው የቆየው።

ይህ ሕግ ከሕገ ወጥነቱ አልፎ ነገሩን ወንጀልና በተራዘመ እስር የሚያስቀጣ ያደርገዋል።

በዚህ ወር መጀመርያ ለፓርላማ የቀረበው ይህ ሕግ በከፍተኛ ድምጽ ነው ትናንት ማክሰኞ የጸደቀው።

ከዚህ በኋላ ሕጉን የመሻር ብቸኛ ሥልጣን ያላቸው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ሲሆኑ ሕጉ ላይ በፈረሙ ቅጽበት ተፈጻሚነቱ ይረጋገጣል።

ከቀናት በፊት የኡጋንዳ ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ #ምዕራባውያን አገራት የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን መብቶች #በአፍሪካ አገራት ላይ በኃይል ለመጫን እየጣሩ ነው ማለታቸው ይታወሳል።

ፕሬዝዳንቱ በአገሪቱ ፓርላማ ቀርበው ንግግር ሲያደርጉ " እንግዳ የሆነ ባህል / ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት እንድንፈቅድ ምዕራባዊያኑ ማዕቀብ በመጣል ጫና ያሳድራሉ " ብለዋል።

" ምዕራባውያን የራሳቸውን አሠራር በሌሎች ላይ ለመጫን የሚያባክኑትን ጊዜ ማቆም አለባቸው " ሲሉ አሳስበው ነበር።

#BBC

@tikvahethiopia
የገቢዎች ሚኒስቴር ግብር ከፋዮች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳሰበ።

ሚኒስቴሩ ፤ ማንነታቸው በውል ያልታወቁ ግለሰቦች እና ቡድኖች የተለያዩ የማደናገሪያ እና የማጭበሪያ መንገዶችን እንዲሁም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ስም እና ሀሰተኛ ማንነት በመጠቀም ግብር ከፋዮችን #እያጭበረበሩ ይገኛሉ ብሏል።

ይህ የማጭበርበር ተግባር እየተሰራ ያለው የግብር ከፋዩን የስልክ አድራሻ በመጠቀም እንደሆነም ገቢዎች ሚኒስቴር ገልጿል።

የማጭበርበር ተግባሩ የሚፈፀመው እንዴት ነው ?

የግብር ከፋዮችን አድራሻ በመጠቀም ፦

1.  ለታማኝ ግብር ከፋይ የሚሰጠውን ሽልማት እንድትሸለሙ እናስመርጣችኋለን፣

2. የኦዲት ውሳኔ #እናስቀንስላችኋለን

3.  ድርጅታችሁ #ወንጀል_መስራቱ ስለተደረሰበት በህግ እንዳትጠየቁ እናደርጋለን የሚሉና የመሳሰሉ #የማስፈራራት እና #የማግባባት ሙከራዎች እና ዘዴዎችን በመጠቀም ነው።

ገቢዎች ሚኒስቴር ይህ ድርጊት እየተፈፀመ መሆኑ በክትትል ለማወቅ እንደቻለ ገልጾ ግብር ከፋዮች የነዚህ መሰል የማጭበርበር ሙከራዎች ሰለባ እንዳይሆኑ አስጠንቅቋል።

ማንኛውም ግብር ከፋይ ይህ መሰል ሁኔታዎች ሲያጋጥሙትም በአቅራቢያው ለሚገኝ የግብር ሰብሳቢ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በአፋጣኝ ጥቆማ እንዲሰጥ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አፅድቀውታል ፤ ፈርመውበታል ! ዩጋንዳ የ " ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት " ን ወንጀል የሚያደርገውን ሕግ አፀደቀች። ዛሬ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ያፀደቁት / ፊርማቸውን ያኖሩበት የረቂቅ አዋጅ ሕግ ተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት የሚፈጽሙ ሰዎችን ሁሉ በዕድሜ ልክ እስራት የሚያስቀጣ ነው። በአንዳንድ ሁኔታዎች ዳግሞ #የሞት ቅጣትን የሚያስከትል ነዉ። ረቂቅ ሕጉ ባለፈው መጋቢት ወር ላይ በአገሪቱ…
#Update

አሜሪካ ዩጋንዳ ላይ እርምጃ ልትወስድ እንደምትችል አስጠነቀቀች።

የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ፤ ኡጋንዳ ትላንት ያፀደቀችውን የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን #ወንጀል የሚያደርገውን ህግ " አሳፋሪ እና ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት " በማለት ተቃወሙ።

ባይደን ፤ " ይህ አሳፋሪ ድርጊት / ሕጉ መፅደቁን / በዩጋንዳ ውስጥ ያለው አስደንጋጭ የሰብአዊ መብት ረገጣ እና ሙስና የቅርብ ጊዜ እድገት አመላካች ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

ፕሬዜዳንት ባይደን ፤ የአሜሪካ ብሄራዊ ደኅንነት ም/ ቤት የዩጋንዳው ሕግ አሜሪካ ከአገሪቱ ጋር ባሏት ግንኙነቶች ላይ ምን አንድምታ እንዳለው አጥንቶ እንዲያቀርብ አዘዋል ተብሏል።

ከህጉ ጋር በተያያዘ ፤ አሜሪካ ለኡጋንዳ የምትሰጠውን እርዳታና ኢንቨስትመንት ልታቆም እንደምትችል ባይደን አስጠንቅቀዋል።

የሕጉን ተፅኖ ከግምት በማስገባትም የዩጋንዳ የአጎዋ (AGOA) ተጠቃሚነት እንደሚገመገም አሳውቀዋል።

ፕሬዜዳንቱ በከባድ የሰብአዊ መብት ረገጣ ወይም ሙስና ውስጥ በተሳተፈ ማንኛውም ሰው ላይ #ማዕቀብ እና ወደ አሜሪካ የመግባት #እገዳን ጨምሮ ተጨማሪ እርምጃዎችን እያጤኑ ስለመሆኑ ተናግረዋል።

ከባይደን በተጨማሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንቶኒ ብሊንከን ፤ ህጉን ተቃውመዋል ፤ መስሪያ ቤታቸውም የአሜሪካ ዜጎች ወደ ዩጋንዳ በሚያደርጉት ጉዞ ላይ መመሪያ እንዲያወጣ አዘዋል።

የባይደን አስተዳደር የዩጋንዳ ፓርላማ አፈ ጉባኤ " አኒታ አሞንግ " አሁን ያላቸውን የአሜሪካ መግቢያ ቪዛ መሰረዙ ሮይተርስ ፣ እንዲሁም ዘ ኢስት አፍሪካን ዘግበዋል።

ከዚህ ቀደም የዩጋንዳ ፕሬዜዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ፤ #ምዕራባውያን አገራት የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን መብቶች #በአፍሪካ አገራት ላይ #በኃይል ለመጫን እየጣሩ ነው ሲሉ ተናግረው ነበር።

ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ  " እንግዳ የሆነ ባህል / ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት እንድንፈቅድ ምዕራባዊያኑ #ማዕቀብ በመጣል ጫና ያሳድራሉ " ሲሉ ነበር የገለፁት።

ምንም እንኳን ምዕራባውያን ሀገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት (ተመድን ጨምሮ) ፕሬዜዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ በዩጋንዳ ምድር የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን ወንጀል በሚያደርገው ረቂቅ ሕግ ላይ ፊርማቸውን እንዳያኖሩና እንዳያፀድቁ ማስጠንቀቂያዎችን ቢሰጡም ፕሬዜዳንቱ ትላንት መጠነኛ ማሻሻያ የተደረገበትን ሕግ በፊርማቸው በማኖር #አቅፅድቀውታል

@tikvahethiopia