TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኡጋንዳ ፓርላማ በአገሪቱ ውስጥ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ #ወንጀል እንዲሆን የሚያደርገውን ረቂቅ ሕግ አጸደቀ። ሕጉ ምን ይዟል ? - ማንኛውንም ራሱን በተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት አፍቃሪነት የመደበ፣ ወይም የጾታ ለውጥ ያስደረገ እንዲሁም በእንግሊዝኛ ምሕጻራቸው ኤል-ጂ-ቢ-ቲ-ኪው ዝርዝር ውስጥ የሚካተት የጾታ ዝንባሌ ያለው ዜጋን ሁሉ ወንጀለኛ ያደርጋል። - በጸደቀው…
#ኡጋንዳ

ምዕራባውያኑ በተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ጉዳይ የኡጋንዳ ፓርላማ ያሳለፈውን ውሳኔ #እየተቃወሙ ናቸው።

የኡጋንዳ ፓርላማ ትላንት ከተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ጋር በተገናኘ አዲስ ህግ አውጥቷል።

ይኸው ህግ በኡጋንዳ ምንድር ማንም ሰው የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ነኝ በሚል ማንነቱን ቢገልፅ ህይወቱን ሙሉ / ለበርካታ አመታ እስር ቤት ውስጥ እንዲያሳልፍ የሚያደርግ ነው።

በአንዳንድ ሁኔታዎች ደግሞ #ሞትም ያስፈርዳል።

ይህ ህግ ትላንት ማክሰኞ በፓርላማ በከፍተኛ ድምፅ ነው የፀደቀው።

ይህንን ተከትሎ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና ምዕራባውያኑ ውሳኔውን መቃወም ጀምረዋል።

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የሆነው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ህጉን " #አፋኝ " ሲል ነው የተቃወመው። ተቋሙ ህጉን " አደንጋጭ ህግ " ሲልም ገልጾ " መድሎ እና ጥላቻን ያበረታታል ስለሆነም ሀገሪቱ እንደገና ህጉን ትፈትሽ " ሲል ጥሪ አቅርቧል።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር #አንቶኒ_ብሊንከን እንዲሁም የዩናይትድ ኪንግደም የአፍሪካ ሚኒስትር #አንድሪው_ሚቼል አዲሱን ህግ ስለማውገዛቸው ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

አዲሱ ህግ የኡጋንዳ ፕሬዜዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ በፈረሙ ቅፅበት ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።

ከቀናት በፊት ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ #ምዕራባውያን አገራት የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን መብቶች #በአፍሪካ አገራት ላይ በኃይል ለመጫን እየጣሩ ነው ሲሉ ተናግረው ነበር።

ፕሬዝዳንቱ በአገሪቱ ፓርላማ ቀርበው ንግግር ሲያደርጉ " እንግዳ የሆነ ባህል / ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት እንድንፈቅድ ምዕራባዊያኑ #ማዕቀብ በመጣል ጫና ያሳድራሉ " ብለዋል።

" ምዕራባውያን የራሳቸውን አሠራር በሌሎች ላይ ለመጫን የሚያባክኑትን ጊዜ ማቆም አለባቸው "  ሲሉም ፕሬዜዳንት ሙሴቬኒ አሳስበው ነበር።

@tikvahethiopia