TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አጫጭር መረጃዎች፦

- የእንግሊዙ ዘውድ ወራሽ የሆኑት ልዑል ቻርልስ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውንና መጠነኛ ምልክት እንደታየባቸው ከቤተ መንግሥቱ የወጣው መረጃ ያስረዳል። ባለቤታቸውም ምርመራ የተደረገላቸው ቢሆንም ከቫይረሱ ነፃ ሆነው ተገኝተዋል።

- በስፔን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከቻይና መብለጡ ተነግሯል። የስፔን ጤና ጥበቃ ሚንስቴር ባወጣው አሃዝ መሠረት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 3434 ደርሷል።

- በሩዋንዳ መንግሥት የተጣለውን የእንቅስቃሴ ገደብ ጥሶ በመውጣት አሳ ለማስገር የሄደው ግለሰብ በአዞ መበላቱ ተሰማ።

- በሁቤይ ግዛት ውሃን የሚገኘው ኤርፖርት ከ APRIL 8 ጀምሮ ዳግም አገልግሎት መስጠት ይጀምራል። ለጊዜው አለም አቀፍ በረራዎችን እንዲሁም ከውሃን ወደ/ከ ቤጂንግ የሚደረጉ በረራዎችን አያስተናግድም።

- ሞስኮ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት ተጨማሪ እርምጃ ወስዳለች የከተማይቱ ከንቲባ ፦ ማንኛውም አይነት ህዝባዊ ዝግጅት ሞስኮ ውስጥ እንዳይደረግ አግደዋል።

#BBC #REUTERS #XInhua
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia