TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በብሄር ግጭት 890 ሰዎች ተገደሉ‼️

የተባበሩት መንግሥታት ባወጣው መረጃ መሰረት፤ በምዕራብ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ #በብሔር_ግጭት ሳቢያ ቢያንስ 890 ሰዎች ተገድለዋል።

#ባኑኑ እና #ባቴንዴ በተባሉ ማኅበረሰቦች መካከል ግጭት የተከተሰተው ዩምቢ በሚባለው አካባቢ በሚገኙ አራት መንደሮች ውስጥ ነው።

የተባበሩት መንግሥታት እንዳለው፤ አብዛኞቹ የአካባቢው ነዋሪዎች ከቤት ንብረታቸው #ተፈናቅለዋል። ዩምቢ አካባቢ ባለው ግጭት ሳቢያ ለዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሀገራዊ ምርጫ ድምጽ የሚሰጡት መጋቢት ላይ ይሆናል።

የተባበሩት መንግሥታት እንዳለው፤ 465 ቤቶችና ህንጻዎች ተቃጥለዋል፤ ፈራርሰዋልም። ከነዚህ መካከል ሁለት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ የጤና ተቋም፣ ገበያ እና የሀገሪቱ ገለልተኛ የምርጫ ኮሚሽን ቢሮ ይገኙበታል።

ከተፈናቀሉት ሰዎች 16,000 የሚሆኑት የኮንጎ ወንዝን ተሻግረው በኮንጎ ብራዛቪል ተጠልለዋል።

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽነር ሚሼል ባቼት፤ "ይህ አስደንጋጭ ግጭት ተመርምሮ ጥፋተኞቹ ለፍርድ መቅረብ አለባቸው" ብለዋል። ኮሚሽኑ ምርመራ መጀመሩም ተመልክቷል።

ዩምቢ ለወትሮው ሰላማዊ ግዛት ነበር። በማኅበረሰቦቹ መካከል ግጭት የተቀሰቀሰው፤ የባኑኑ ማኅበረሰብ አባላት ባህላዊ መሪያቸውን በባቴንዴ መሬት ለመቅበር በመሞከራቸው ነበር።

የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምርጫን ፌሊክስ ቲስኬዲ ማሸነፋቸው ቢነገርም ሌላው ተቀናቃኝ ማርቲን ፋያሉ "አሸናፊው እኔ ነኝ" ማለታቸው ይታወሳል።

ማርቲን ፋያሉ እንደሚሉት ከሆነ፤ ፌሊክስ ቲስኬዲ ምርጫውን ያሸነፉት ከቀድሞው ፕሬዘዳንት #ጆሴፍ_ካቢላ ጋር #ተመሳጥረው ነው። ሕዝቡ የሰጠው ድምጽ ዳግመኛ ይቆጠር ሲሉም ለፍርድ ቤት አቤቱታ አሰምተዋል።

የአፍሪካ ኅብረት የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን ጉዳይ በተመለከተ ከቀናት በፊት በአዲስ አበባ መክሯል።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia