TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
‹‹በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ከ80 ሺህ በላይ ዜጎች #ተፈናቅለዋል፡፡›› የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት
.
.
የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዛሬ በሠጠው መግለጫ ተፈናቃዮችን ለመርዳት ክልሉ 35 ሚሊየን ብር በመመደብ ድጋፍ ሲደረግ ቢቆይም አሁን ላይ ያለውን ችግር ሙሉ በሙሉ ለመቋቋም ከክልሉ መንግሥት አቅም በላይ እንደሆነ ገልጻል፡፡

ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠሩ ችግሮች ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸው #ተፈናቅለዋል፡፡ በአማራ ክልልም ከክልሉ ውስጥና በሌሎች ክልሎች የሚኖሩ ከ80 ሺህ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸውን የክልሉ መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ አድርጓል፡፡

የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ.ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ አሰማኸኝ አስረስ እንዳሉት ከክልሉ ውጭ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ከኦሮሚያና ከሶማሌ ክልሎች እንዲሁም በክልሉ ውስጥ ደግሞ በተለይም በማዕከላዊ እና በምዕራብ ጎንደር አካባቢዎች ዜጎች በስፋት ተፈናቅለዋል፡፡

የመፈናቀል አደጋው ከተከሰተበት በተለይም ከሕዳር ወር ጀምሮ የክልሉ እና የፌዴራል መንግሥት በጋራ ተፈናቃዮችን በጊዜያዊና በዘላቂነት ለማቋቋም 35 ሚሊየን ብር በመመደብ ድጋፍ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ያስታወሱት አቶ አሰማኸኝ ‹‹አሁን ላይ ያለውን ችግር ሙሉ በሙሉ ለመቋቋም ከክልሉ መንግሥት አቅም በላይ ሆኗል›› ብለዋል፡፡

ተፈናቃዮቹ ለሰፋ ማኅበራዊ፣ ምጣኔ ሀብታዊ እና ሥነ ልቦናዊ ችግሮች በመጋለጣቸው ዘላቂ ድጋፍ እና እንክብካቤ እንደሚያስፈልጋቸው ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል፡፡ ይህንንም ለማድረግ የክልሉ መንግሥት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የሚመራ ግብረ ኃይል አቋቁሞ ድጋፍ የማሰባሰብ ሥራ መጀመሩን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፤ ‹‹ድጋፉ በተደራጀ እና በአንድ አግባብ እንዲሆን ይፈለጋል›› ሲሉም አሳበዋል፡፡

የሚደረገው ድጋፍ በገንዘብ፣ በዓይነት እና በዕውቀት ሊሆን እንደሚችል ያስረዱት አቶ አሰማኸኝ ከዚህ ቀደም ድጋፍ ያደረጉ አካላትን በማመስገን በተከፈተው የሒሳብ ቁጥር ሕዝቡ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

#የገንዘብ_ድጋፍ ማድረግ ለሚፈልጉ አካላት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የአደጋ መከላከል ፕሮግራሞችና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ማስተባበሪያ ኮሚሽን የባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000258250811 እንዲሁም በዓይነት ድጋፍ ለማድረግ ለሚፈልጉ አካላት በስልክ ቁጥሮች 0582180196፣ 0582181096፣ 0582181151፣ 0918701136፣ 0918340128 ወይም 0953600333 በመደወል መረጃ ማግኘት እንደሚቻል አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia