TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#USA

ዛሬ የሀገራችን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የ49 አገራት መሪዎች እንዲሁም አፍሪካ ህብረት የሚሳተፉበት ሁለተኛው የአሜሪካ- አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ይጀመራል።

ለዚሁ ጉባኤ ዶ/ር ዐቢይን ጨምሮ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች አሜሪካ ላይ ተሰባስበዋል።

ለሦስት ቀናት የሚካሄደው ይኸው የመሪዎች ጉባኤ ዓለማችንን እየፈተኗት ያሉ ተግዳሮቶች ፦
- የአየር ንብረት ቀውስ፣
- መልካም አስተዳደር፣
- የምግብ ዋስትና እና የዓለም ጤናን የሚጨምር ሲሆን፣ እንዲሁም የአሜሪካ-አፍሪካ የንግድ እና የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማጠናከር ላይ ያተኩራል።

አሜሪካ ጉባዔው አፍሪካ ቁልፍ የጂኦፖለቲካል ተጫዋች እንደሆነች ዕውቅና በመስጠት ላይ የተመሠረተ መሆኑን ገልጻለች።

በአሜሪካ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ፕሬዝዳንት ባይደን በቡድን 20 ውስጥ የአፍሪካ ኅብረት ቋሚ ቦታ እንዲያገኝ ድጋፍ እንደሚሰጡ ይጠበቃል።

በተጫማሪም የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ ከአፍሪካ አገራት መካከል " ቋሚ አባል እንዲያካትት " ድጋፍ መስጠትን ጨምሮ ማሻሻያ እንዲያደርግ ፕሬዝዳንት ባይደን ቁርጠኛ እንደሆኑ ተነግሯል።

በሌላ በኩል ፤ አሜሪካ ለአፍሪካውያን አገራት ከቀረጥ ነፃ ንግድ ተጠቃሚነት ዕድል (#አጎዋ) ጋር በተያያዘ ከተጠቃሚ አገራቱ ንግድ ሚኒስትሮች ጋር የሚካሄደው ጉባኤ ዛሬ ለማካሄድ ቀጠሮ መያዙን ቢቢሲ ዘግቧል።

#DrAbiyAhmed -  " አፍሪካ ፡ የዓለም አቀፍ ንቅናቄ አጣዳፊነት " በሚል መሪ ሀሳብ አሜሪካን አካዳሚ ኦፍ አቺቭመንትና ግሎባል ሆፕ ኮአሊሽን የተሰኙት ተቋማት በዋሽንግተን ዲሲ በጋራ ባዘጋጁት ልዩ ዝግጅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአረንጓዴ ዐሻራ ንቅናቄን አስመልክቶ ላሳዩት አመራር ‘የአፍሪካ የላቀ አመራር’ ሽልማት አበርክቶላቸዋል።

@tikvahethiopia