TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#መውሊድ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ቅዳሜ የሚከበረውን 1 ሺህ 494 ኛውን የመውሊድ በዓል አስመልክቶ ለመላው ሙስሊሞች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል። የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እንድሪስ በዓሉን በማስመልከት መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም በኢትዮጵያ በዚህ ዓመት የሙስሊሙችን አንድነት ለማጠናከር የጀመርነው እንቅስቃሴ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል።

More👇
https://telegra.ph/ETH-11-08-2

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#መውሊድ

የ1497ኛው የመውሊድ በዓል እየተከበረ ይገኛል።

በታላቁ አንዋር መስጂድ ያለው የበዓል የአከባበር ሁኔታ ከላይ በፎቶ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#መውሊድ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ነገ ረቡዕ የሚከበረውን የታላቁ ነቢይ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) 1498ኛ ዓመት የልደትን አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።

ምክር ቤቱ በዚህ መግለጫው ፤ " እኛ ሙስሊሞች ይህን ታላቅ በዓል ሲያከብር አላህ (ሱ.ወ.) ለመልእክተኛው (ሶ.ዐ.ወ) መርጦ ያላበሳቸውን መልካም ስነ-ምግባራት በመላበስና ለሌሎችም አርኣያ በመሆን፣ ሱናቸውን (ፈለጋቸውን) ሕያው በማድረግ መርኅ ሊሆን ይገባል " ብሏል።

" ከምንም ነገር በላይ ከታላቁ ነቢይ (ሶ.ዐ.ወ) አስተምህሮና ከሕይወት ፈለጋቸው አኳያ ራሳችንን ከመፈተሽ ባሻገር ፦
- የተቸገሩትን በመርዳት፣
- የታመሙትን በመጎብኘት፣
- ቅስማቸው የተሰበረ የኅብረተሰብ ክፍሎችን አለንላችሁ በማለትና በመደገፍ፣
- የሕግ ታራሚዎችን በመጠየቅ፤
- በመሃከላችን የተፈጠሩ ልዩነቶች እና አለመግባባቶችን ለአላህ ብለን በመተው፣ ዐውፍ በመባባል፣ ፍቅራችንንና እንድነታችንን በማደስና ብሎም ከመልእክተኛው (ሶ.ዐ.ወ) በወረስነው ባህርይ መሠረት ከእምነቱ ውጭ ላሉ ወገኖች ጭምር ረሱላችን (ሶ.ዐ.ወ) ለዑመታቸው የነበራቸውን ፍቅር፣ ርኅራኄ እና እዝነትን በመግለጽ ጭምር ሊኾን ይግገባል " ሲል ገልጿል።

በተጨማሪም ዕለቱን ልዩ ልዩ የግልና የቡድን ዒባዳዎችን በመፈፀም፣ ለሰው ልጆች በአጠቃላይ፣ በተለይም ሀገራችን ኢትዮጵያ ሰላሟ እንዲሟላ፣ አስተማማኝ ደኅንነት እንዲሰፍንባት፣ የተሟላ ፀጋ ይለግሳት ዘንድ ፈጣሪያችንን አላህ (ሱ.ወ.) በመማጸን እስላማዊ አደብን በጠበቀ መልኩ እንድናሳልፈው አደራ ለማለት እንወዳለን ብሏል ምክር ቤቱ።

እነዚህን ማድረግ በሚገባበት በዚህ ጊዜ ፣ በተቃራኒው ሌሎች ሰዎችን በማንጓጠጥ፣ በመወረፍና በመዝለፍ ላይ መዘውተር፣ የነቢዩን (ሶ.ዐ.ወ.) አስተምህሮ በሚቃረን ተግባር ላይ መሰለፍ ስለሚኾን፣ ከዚህ ዓይነቱ ባህርይ እጅግ መጠንቀቅና መራቅ ያስፈልጋል ሲል አሳስቧል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#መውሊድ : 1499ኛው የታላቁ ነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓል በነገው ዕለት #እሁድ እንደሚከበር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት አሳውቋል።

@tikvahethiopia