TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ግጭቱ በቁጥጥር ስር ውሏል...

በድሬዳዋ ከተማ #በግል ጸብ ተጀምሮ ባለፉት ጥቂት ቀናት መልኩን ቀይሮ የነበረው ግጭት «በቁጥጥር ስር መዋሉን» የድሬዳዋ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽነር ኮማንደር ዓለሙ መግራ ዛሬ ለዶይቸ ቬለ በስልክ ተናግረዋል። «እዛ አካባቢ ያለው የቀበሌ መስተዳደር ከኅብረተሰቡ ጋር ውይይት አካሂዶ፤ (ነገሩ የግለሰብ ግጭት ነው) ግጭቱ አሁን በቁጥጥር ስር ውሏል» ብለዋል ኮሚሽነሩ። የድሬዳዋ ነዋሪዎችም በሠርግ ላይ ተቀስቅሶ ላለፉት ሦስት ቀናት ወደ ቡድን ግጭት ያመራው ጠብ መብረዱን አረጋግጠዋል። ኾኖም እዛው ችግሩ የነበረበት አካባቢ በሚገኝው ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ብሔር ነክ ግጭት ተከስቶ ዛሬ አንዳንድ ተማሪዎች ወደ ክልላችን እንመለሳለን ማለታቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ዩኒቨርሲቲው ችግሩን ለመፍታት ከተማሪዎች ጋር ውይይት ለማድረግ ጥረት እያደረገ ይገኛል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በምርጫ 2013 ይወዳደራሉ።

እንደ ሀሩን ሚዲያ /Harun Media/ ዘገባ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በመጭው ምርጫ #በግል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) ይወዳደራሉ።

ለዚህም ምዝገባ የሚያስፈልገውን የ2,500 ሰው ድጋፍ በማሰባሰብ በእጩነት መመዝገባቸው ታውቋል።

በሌላ በኩል፦

ኡስታዝ አቡበክር አህመድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) እንደሚወዳደሩ ሀሩን ሚዲያ /Harun Media/ የዘገበ ሲሆን በዘገባው ላይ ኡስታዝ አቡበክር በግል ይሁን በፓርቲ በምርጫው እንደሚወዳደሩ የተገለፀ ነገር የለም።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በምርጫ 2013 ይወዳደራሉ። እንደ ሀሩን ሚዲያ /Harun Media/ ዘገባ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በመጭው ምርጫ #በግል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) ይወዳደራሉ። ለዚህም ምዝገባ የሚያስፈልገውን የ2,500 ሰው ድጋፍ በማሰባሰብ በእጩነት መመዝገባቸው ታውቋል። በሌላ በኩል፦ ኡስታዝ አቡበክር አህመድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) እንደሚወዳደሩ ሀሩን ሚዲያ…
ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ በምርጫ 2013 ይወዳደራሉ።

የህግ ምሩቅ የሆኑት ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ በምርጫ 2013 #በግል ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት (ፓርላማ) እንደሚወዳደሩ ሃሩን ሚዲያ /Harun Media/ ማረጋገጡን አሳውቋል።

ቀደም ብሎ በወጣው መረጃ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል እና ኡስታዝ አቡበክር አህመድ በዘንድሮው ምርጫ 2013 ላይ ለ ፓርላማ እንደሚወዳደሩ መገለፁ ይታወቃል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" የሬሜዲያል ተማሪዎች ምደባ በቀጣይ ይካሄዳል " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትላንት ይፋ በተደረገው የማካካሻ ትምህርት / ሬሜዲያል መቁረጫ ነጥብ መሰረት ወደ መንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ገብተው ለሚማሩ ተማሪዎች በቀጣይ የዩኒቨርሲቲ ምደባ እንደሚካሄድ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

የመቁረጫ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ከተደረገላቸው በኃላ ለ4 ወራት የማካካሻ ትምህርት የሚወስዱ ሲሆን ይህንን ተከታትለው በተቋማቸው እና በማዕከል የሚሰጣቸውን ፈተና ማለፍ ሲችሉ በቀጣይ መደበኛ ተማሪ ሆነው ወደ ፌሽማን ይቀላቀላሉ።

ትምህርት ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው የመቁረጫ ነጥብ በሁሉም አማራጮች ማለትም #በግል እና #በመንግስት ተቋማት የሬሜዲያል ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል፤ ይህም ማለት 210 ከ700፣ 180 ከ600 እና 150 ከ500 ማስመዝገብ አለባቸው።

በመንግስት ተቋማት (ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) በዩኒቨርሲቲ ተመድበው የሬሜዲያል ፕሮግራም የሚከታተሉ በ #ተፈጥሮ_ሳይንስ የመደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች መቁረጫው 255 ከ700 ነው። የሴት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች መቁረጫው ደግሞ 234 ከ700 ነው።

በዩኒቨርሲቲ ተመድበው ለሚማሩ የማህበራዊ ሳይንስ መደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥቡ 218 ከ600 ሲሆን ፤ የሴት ተማሪዎች መቁረጫው 200 ከ600 ነው።

እንደ ትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ከሆነ ዘንድሮ 164,242 የሬሜዲያል ተማሪዎች በግል እና በመንግሥት ተቋማት ገብተው ይማራሉ።

#ማስታወሻ ፦ የሬሜዲያል መቁረጫ ነጥብ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።

በሌላ በኩል ፤ በ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈትነው የማለፊያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ምደባ ከትላንት ጀምሮ ይፋ የተደረገ ሲሆን የምደባ መመልከቻው ፦በድረገፅ https://result.ethernet.edu.et/
የቴሌግራም ቦት @moestudentbot መሆኑን ለማስታወስ እንወዳለን።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ፤ የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ #በግል_ከፍለው የአዉሮፕላን አብራሪነት ስልጠና ለሚፈልጉ ጥሪ አቀረበ።

ዩኒቨርሲቲው ፤ ለአዉሮፕላን አብራሪነት ስልጠና ለአጭር ጊዜ የሚቆይ የ10% ቅናሽ ማድረጉንም አሳውቋል።

" በግል ከፍለው የአውሮፕላን አብራሪ ለመሆን ለሚማሩ ስልጠናውን ለመስጠት ተዘጋጅቻለሁ " ያለው የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩንቨርስቲ አመልካቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው ብሏል።

1ኛ. የትምህርት ደረጃ ፦ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሰርተፍኬት የወሰዱ፣ እንዲሁም ፦
* በሂሳብ፣
* በእንግሊዘኛ
* በፊዚክስ ዉጤት አመርቂ አፈጻጸም ያስመዘገቡ

2ኛ. ዕድሜ ፦ 18 እና ከዚያ በላይ

3ኛ. እንግሊዘኛ ፦ ደረጃ 4

4ኛ. ቁመት፦ 1ሜ 62 ሴ.ሜ እና ከዚያ በላይ

5ኛ. የጤና ሁኔታ፦ ደረጃ 1 የጤና ሰርተፊኬት

የስልጠናው ርዝማኔ 1 አመት ከ 3 ወር ነው ተብሏል።

" የተደረገው ቅናሽ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ነው " ያለው ዩኒቨርሲቲው ፤ " የምዝገባ ሂደቱን ለማወቅ እና ለበለጠ መረጃ በኢሜል አድራሻ ፦ [email protected] / [email protected] ያነጋግሩን " ብሏል።

ስልክ በመደወል መረጃ ለመቀበል የምትፈልጉም +251-115174600/8598 ነው ተብሏል።

ከዚህ ባለፈ የዩኒቨርሲቲውን ድረገፅ መመልከት ይቻላል ፦ ethiopianaviationuniversity.azurewebsites.net/admission/applyonline

@tikvahethiopia