TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
አሜሪካ በኢትዮጵያ የምታደርገው የምግብ እርዳታ እንዲቋረጥ ወሰነች። የአሜሪካ መንግሥት የዓለም አቀፍ ልማት ተራድኦ ድርጅት (USAID) በኢትዮጵያ የሚያቀርበው የምግብ እርዳታ " ለተረጂዎች ሳይደረስ ሌላ ጥቅም ውሏል " በሚል እንዲቋረጥ መወሰኑን አስታውቋል። USAID እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው " ለኢትዮጵያ ሕዝብ መቅረብ የነበረበት የምግብ እርዳታ በከፍተኛ መጠን እና በተቀናጀ ሁኔታ ከታቀደለት አላማ…
የዓለም ምግብ ፕሮግራም የምግብ ርዳታ ስርጭት አቆመ።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) የኢትዮጵያ የርዳታ ምግብ ሥርጭቱን ማቆሙን አስታውቋል።

የተባበሩት መንግሥታት የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) ለኢትዮጵያ ተጎጂዎች ሲያሠራጭ የቆየውን የምግብ ርዳታ፣ " #ስርቆት_በመንሰራፋቱ " ምክንያት ለጊዜው ማቆሙን ዛሬ ገልጿል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ የርዳታ ምግብ የማቆም ውሳኔውን ይፋ ያደረገው፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ተመሳሳይ ርምጃ መውሰዷን፣ በዩኤስኤአይዲ በኩል ካሳወቀች ከአንድ ቀን በኋላ መሆኑን ቪኦኤ ዘግቧል።

@tikvahethiopia