TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#iPhone #Apple

የአፕል የገበያ ድርሻ ባለፉት ሁለት ቀናት ብቻ በ200 ቢሊዮን ዶላር ቀነሰ።

ከሰሞኑን የቻይና መንግሥት የአፕል ምርት የሆነውን #አይፎንን ማገዱ በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ተዘግቧል።

እገዳው ምናልባት ከደህንነት ጋር ሊያይዝ ይችላል ተብሏል።

ይህን እገዳ ተከትሎ የአፕል የገበያ ድርሻ ለ2 ተከታታይ ቀናት ቅናሽ ማሳየቱ ተነግሯል።

የድርጅቱ የድርሻ ገበያ ከ6 በመቶ በላይ የቀነሰ ሲሆን ይህም ማለት በ200 ቢሊዮን ዶላር ባለፉት ሁለት ቀናት ቀንሷል።

ቻይና የአፕል ምርቶች ሦስተኛዋ ትልቁ ገበያ ስትሆን ከዓመታዊ ገቢው 18% የሚገኘውም ከቻይና ገበያ ነው።

ግዙፉ የአፕል ምርቶች አምራች የሆነው ፎክስኮን በርካታ የአፕል ምርቶችን የሚሠራው በቻይና ነው።

ዋል ስትሪት ጆርናል እንደዘገበው የማዕከላዊ ቻይና መንግሥት ሠራተኞች አይፎን ለሥራ እንዳይጠቀሙና መ/ቤት ይዘውም እንዳይሄዱ ታግደዋል።

ብሉምበርግ እንደዘገበው ዕገዳው በመንግሥት የሚተዳደሩ ተቋሞችን እንዲሁም መንግሥት የሚደግፋቸውን ተቋሞችም ይጨምራል።

ስለዘገባዎቹ ከቻይና መንግሥት የተሰጠ ምላሽ የለም።

ይህ በቻይና መንግሥት ይፋ የተደረገው ዕገዳ የተጣለው አይፎን 15 ከመውጣቱ ከ5 ቀናት በፊት ነው።

አፕል የዓለም ትልቁ የስቶክ ገበያ ያለው ሲሆን፣ ገበያው ወደ 2.8 ትሪሊዮን ዶላር ይደርሳል።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia