TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#COVID19

በስፔን ባለፉት 24 ሰዓት 268 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል ፤ ከመጋቢት 11 በኃላ የተመዘገበ #ዝቅተኛው የሟቾች ቁጥር ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SPAIN

(በቢቢሲ እና ሲጂቲኤን)

በስፔን ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የ164 ሰዎች ሞት ሪፖርት ተደርጓል ፤ ይህ የሟቾች ቁጥር ከመጋቢት 9/2012 ዓ/ም በኃላ የተመዘገበ #ዝቅተኛው ቁጥር ነው።

በአሁን ሰዓት በአጠቃላይ 217,446 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ 25,264 ሰዎች ደግሞ ሞተዋል።

በሌላ በኩል በስፔን ከነገ ጀምሮ በሕዝብ ትራንስፖርት ውስጥ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ (ማስክ) ማድረግ ግድ መሆኑን አስታውቃለች። አገሪቷ በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ የጣለቻቸውን ጥብቅ ገደቦች ቀስ በቀስ እያላላች ነው፡፡

በስፔን የሚገኙ አዋቂዎች ከሰባት ሳምንታት በኋላ እሁድ ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከቤት በመውጣት አካላዊ እንቅስቃሴ አድርገዋል፡፡ ከ14 ዓመት በታች ላሉ ህጻናት በቤት ውስጥ የመቀመጥ ገደቡ የላላው ከሳምንት በፊት ነበር፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ፦

- በፈረንሳይ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የ135 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል (ከ6 ሳምንታት በኃላ የተመዘገበ #ዝቅተኛው የሟቾች ቁጥር ነው)

- በአሜሪካ ሟቾች ቁጥር ከ68,000 በላይ ሆኗል፤ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ከ1.1 ሚልዮን መብለጣቸው ተገልጿል።

- በደቡብ አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 6,783 ደርሰዋል፤ በአንድ ቀን 447 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። የሟቾች ቁጥርም በስምንት ጨምሮ 131 ደርሷል።

- በግብፅ ባለፉት 24 ሰዓት 272 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል፤ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 6,465 ደርሰዋል። በሌላ በኩል 14 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 429 ደርሷል።

- በሩዋንዳ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 259 ደርሰዋል። እስካሁን ሞት አልተመዘገበም።

- በAfricaCDC መረጃ መሰረት እስካሁን በአፍሪካ ደረጃ 1,761 ሰዎች ሞተዋል፤ 43,060 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ተይዘዋል ፤ 14,343 አገግመዋል።

- በዓለም አቀፍ ደረጃ የሟቾች ቁጥር ከ247,335 ደርሷል፤ 1,137,349 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል፤ 3,546,758 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
አጫጭር መረጃዎች ፦

- የሮም 'ቻምፒኖ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ' ሊከፈት እንደሆነ ተገልጿል።

- በጣልያን የሟቾች ቁጥር ከትላንትናው ጨምሯል፤ ባለፉት 24 ሰዓት የ195 ሰዎች ሞት ሪፖርት ተደርጓል። 1,221 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

- በአሜሪካ የሟቾች ቁጥር ከ69,000 በላይ ሆኗል።

- በኳታር 640 ሰዎች በአንድ ቀን በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 16,191 ደርሷል።

- በጃፓን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እስከ ግንቦት 23 ተራዝሟል።

- በዩናይትድ ኪንግደም ባለፉት24 ሰዓት የ288 ሰዎች ሞት ሪፖርት ተደርጓል (ከየካቲት ወር መጨረሻ በኃላ የተመዘገበ #ዝቅተኛው ቁጥር ነው) አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 28,734 ደርሷል።

- በቱርክ የሟቾች ቁጥር 3,461 ደርሷል፤ ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ የ64 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል።

- በፈረንሳይ የሟቾች ቁጥር ከትላንት ጨምሯል፤ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 306 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።

- በዓለም አቀፍ ደረጃ የሟቾች ቁጥር 250,099 ደርሷል፤ 1,170,448 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል፤ 3,610,189 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ፦

- በስፔን ባለፉት 24 ሰዓት የ108 ሰዎች ሞት ሪፖርት ተደርጓል ፤ ከመጋቢት 8 በኃላ የተመዘገበ #ዝቅተኛው የሟቾች ቁጥር ነው።

- በጣልያን ባለፉት 24 ሰዓት 875 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል (ከ69 ቀናት በኃላ ሪፖርት የተደረገ #ዝቅተኛው ኬዝ ነው) ፤ በተጨማሪ ትላንት 153 ሰዎች ሞተዋል።

- ዛሬ በኔፓል የመጀመሪያው ሞት ተመዝግባል።

- በዩናይትድ ኪንግደም በ24 ሰዓት 3,451 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 468 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።

- በህንድ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ከቻይና በልጧል፤ በሀገሪቱ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 90,343 ደርሰዋል።

- በኳታር ተጨማሪ 1,547 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 30,972 ደርሷል።

- የጀርመን ቡንደስሊጋ ከ2 ወር በኃላ ዛሬ ዳግም ጀምሯል።

- በአሜሪካ የሟቾች ቁጥር ወደ 89,000 እየተጠጋ ነው። የCDC ዳይሬክተር እስከ ግንቦት 24 ደረስ በወረርሽኙ የሚሞቱ ሰዎች 100,000 ሊደርሱ እንደሚችሉ ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በስፔን የሟቾች ቁጥር ከ100 በታች ሆኖ ተመዘገበ!

ባለፉት 24 ሰዓት በስፔን 87 ሰዎች ህይወት ማለፉ ሪፖርት ተደርጓል። በሀገሪቱ የእንቅስቃሴ #ገደብ ከተጣለበት ቀን ጀምሮ የተመዘገበ #ዝቅተኛው የሟቾች ቁጥር ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ፦

- በሶሪያ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 58 ደርሰዋል፤ በዛሬው ዕለት 7 ተጨማሪ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሪፖርት ተደርጓል።

- በጣልያን ባለፉት 24 ሰዓት የ145 ሰዎች ህይወት ማለፉ ሪፖርት ተደርጓል። ይህ የሟቾች ቁጥር ከየካቲት 30/2012 ዓ/ም በኃላ የተመዘገበ #ዝቅተኛው የሟቾች ቁጥር ነው።

- በደቡብ ኮሪያ 13 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ ሰባቱ (7) ከውጭ የገቡ ናቸው፤ አምስቱ (5) ከምሽት መዝናኛ ቤቱ ጋር ግንኙነት ያላቸው ኬዞች ናቸው።

- በዩናትድ ኪንግደም ባለፉት 24 ሰዓት የ170 ሰዎች ሞት ሪፖርት ተደርጓል ፤ ከመጋቢት 15 በኃላ የተመዘገበ #ዝቅተኛው የሟቾች ቁጥር ነው።

- ኳታር ውስጥ በአንድ ቀን 1,632 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሪፖርት ተደርጓል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 32,604 ደርሷል።

- በግብፅ ባለፉት 24 ሰዓት 510 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ18 ሰዎች ህይወት አልፏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጣልያን የሟቾች ቁጥር ከ100 በታች ሆኖ ተመዘገበ!

ባለፉት 24 ሰዓት በጣልያን የዘጠና ዘጠኝ (99) ሰዎች ህይወት ማለፉ ሪፖርት ተደርጓል ፤ ከየካቲት 30/2012 ዓ/ም በኃላ የተመዘገበ #ዝቅተኛው የሟቾች ቁጥር ነው።

በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት 451 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ ይህ ደግሞ ከየካቲት 23/2012 ዓ/ም በኃላ የተመዘገበ #ዝቅተኛው ኬዝ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በስፔን ለሁለተኛ ቀን የሟቾች ቁጥር ከ100 በታች ሆኖ ተመዝግቧል!

በስፔን ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ሃምሳ ዘጠኝ (59) ሰዎች ህይወታቸው አልፏል ፤ ከመጋቢት 7/2012 ዓ/ም በኃላ የተመዘገበ #ዝቅተኛው የሟቾች ቁጥር ነው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
TIKVAH-ETHIOPIA
ፈረንሳይ iPhone 12ን አገደች። ፈረንሳይ iPhone / አይፎን 12 ከልክ በላይ ጨረራ ያመነጫል በሚል የስልኩ ሽያጭ እንዲታገድ አዘዘች። ትናንት መስከረም 1/2016 ዓ.ም. የሬዲዮ ሞገዶችን የሚቆጣጠረው አካል አይፎን 12 ከሚፈቀደው የኤሌክትሮማግኔቲክ ራዲዬሽን በላይ እያመነጨ ነው ብሏል። ተቋሙ ስልክ አምራቹ አፕል ችግሩን በሚያደርጋቸው ማሻሻያዎች በአስቸኳይ የማይቀርፍ ከሆነ በመላው አገሪቷ…
#ቴክኖሎጂ #iPhone

ፈረንሳይ " አይፎን 12 " ን ከልክ በላይ ጨረራ ያመነጫል በሚል የስልኩ ሽያጭ እንዲታገድ ማዘዟን ተከትሎ የአውሮፓ ሀገራት ጉዳዩን እየተከታተሉ ነው ተብሏል።

ፈረንሳይ አይፎን 12ን ያገደችው ከሚፈቀደው የኤሌክትሮማግኔቲክ ራዲዬሽን በላይ እያመነጨ ነው በማለት ሲሆን ይህን እገዳ ተከትሎ ፦
- ቤልጂየም፣
- ኔዘርላንድስ
- ጀርመን ጉዳዩን በልዩ ሁኔታ እየተከታተሉት ነው ተብሏል።

የጀርመን ባለሥልጣናት ሁኔታው ወደ አውሮፓ አቀፍ እርምጃዎች ሊመራ ይችላል ብለዋል።

የቤልጂየም መንግስት እ.ኤ.አ. በ2020 ለመጀመሪያ ጊዜ የተለቀቀው አይፎን 12 #የጤና_ጠንቅ መሆኑን እንዲገመግም ለተቆጣጣሪ አካል መመሪያ መስጠቱ ተነግሯል።

የቤልጂየም የዲጂታላይዜሽን ሚኒስትር ማቲዩ ሚሼል ፤ " ዜጎቻችን በሙሉ ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ከማንኛውም አደጋ የተጠበቁ እንዲሆኑ ማድረግ የእኔ ኃላፊነት ነው። ጤና መቼም ቢሆን ችላ ሊባል የማይገባ ጉዳይ ነው። " ብለዋል።

ሁሉም የአፕል ሞዴሎችን እንዲመረምር ተቆጣጣሪውን አካል እንደተጠየቀ አመልክተዋል። ሌሎችም ብራንዶች ላይ ተመሳሳይ ስራ ይሰራል ብለዋል።

የኔዘርላንድ ዲጂታል መሠረተ ልማት ኤጀንሲ ፤ በፈረንሣይ ምርመራ ላይ በመመርኮዝ ከልክ በላይ የጨረር መጠን እንደሚያመነጭ ጥርጥር የለውም ያለ ሲሆን አፕልን እንደሚያነጋግር አሳውቋል።

ነገር ግን “ ምንም አጣዳፊ የደህንነት ስጋት የለም ” ብሏል።

የጀርመኑ BNetzA ኔትወርክ ኤጀንሲ ፤ የፈረንሣይ ምርመራ በሁሉም የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ላይ የሚተገበሩ እርምጃዎችን ሊያስወስድ የሚችል ነው ብሏል።

አፕል የፈረንሳዩን እገዳ ከሰማ በኃላ ለቢቢሲ በሰጠው ቃል ፤ አይፎን 12 የጨረራ መጠኑ በሰዎች ላይ ጉዳት እንደማያስከትል በመላው ዓለም ባሉ ተቆጣጣሪዎች እውቅና ያለው ምርት ነው ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

በሌላ መረጃ ፤ አፕል አዲሱን " አይፎን 15 "  ከነገ ጀምሮ ማዘዝ እንደሚቻል አሳውቋል።

አዲሱ ምርት እንደየአይነቱ በተለያየ የገንዘብ መጠን ለገበያ ቀርቧል።

አይፎን 15 በስንት ዶላር ነው ለገበያ የቀረበው ?

👉 አይፎን 15 ከ$799 እስከ $1,099 (በኢትዮጵያ ብር በባንክ ቢሰላ ከ44,952 ብር እስከ 61,830 ብር ይሆናል)

👉 አይፎን 15 ፕላስ ከ$899 እስከ $1,199 (በኢትዮጵያ ብር በባንክ ቢሰላ ከ50,578 ብር እስከ 67,456 ብር ይሆናል)

👉 አይፎን 15 ፕሮ ከ$999 እስከ $1499 (በኢትዮጵያ ብር በባንክ ቢሰላ ከ56,204 ብር እስከ 84,335 ብር ይሆናል)

👉 አይፎን 15 ፕሮ ማክስ ከ$1,199 እስከ $1,599 (በኢትዮጵያ ብር በባንክ ቢሰላ ከ67,456 ብር እስከ 89,961 ብር ይሆናል)

ገንዘቡ #ዝቅተኛው እና #ከፍተኛውን ጣሪያ የሚያሳይ ሲሆን እንደ ስልኩ GB እና አይነት ይለያያል።

@tikvahethiopia