TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#DrLiaTadesse በኢትዮጵያ ተጨማሪ 15 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል! ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3,707 ላቦራቶሪ ምርመራ 15 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 287 ደርሷል። ቫይረሱ የተገኘባቸው ሁሉም ወንድ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ እድሜያቸው ከ17 እስከ 38 ዓመት የሆኑ ናቸው። ቫይረሱ የተገኘባቸው 8…
#DrLiaTadesse

ዛሬ በፌደራል ደረጃ በተሰጠው የኮቪድ-19 ዕለታዊ መረጃ ላይ በቤንሻንጉል ጉሙዝ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሁለት (2) ሰዎች ከታች ጉባ ለይቶ ማቆያ ተብሎ የተጠቀሰው #በስህተት መሆኑንና የጉባ ነዎሪዎች ቢሆኑም #በፓዌ ለይቶ ማቆያ የሚገኙ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ #ከይቅርታ ጋር አሳውቀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
" የተባረሩት መምህራን ወደ ስራ ገበታቸው ይመለሳሉ " - ርዕሰ መምህር ዶ/ር ወርቁ ነጋሽ

" መስተካከል ያለባቸው እጅግ ብዙ ጉዳዮች ስላሉ ት/ቤቱ ከወላጅ ተወካዮች ጋር ለመስራት የገባውን ቃል ያክብር " - PTSA

የአንድነት ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት የወላጆችን ጥያቄ በማለባበስ ፣ አግባብ ባልሆነ መንገድ 4 መምህራንን እና 1ሌላ ድጋፍ ሰጪ ሰራተኛን አባርሯል በማለት የትምህርት ቤቱ መምህራን እና የተማሪ ወላጆች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበዋል።

መምህራን እና የተማሪ ወላጆች ምን አሉ ?
  
- የተማሪ ወላጆች በ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ትምህርት ቤቱ " የመምህራኑን የደሞዝ ይጨመርልን ጥያቄ እመልሳለሁ " በማለት ወላጆች ከፍተኛ ነው ያሉትን የ75 በመቶ የተማሪዎች የትምህርት ክፍያ ጭማሪ ተደርጓል ብለዋል።

- ትምህርት ቤቱ #ለመምህራን ከ60 እስከ 100 % የደሞዝ ጭማሪ አደርጋለሁ በማለት ከወላጅ ኮሚቴ ጋር ተስማምቶ ወላጆች የ75 በመቶ የክፍያ ጭማሪ ያድርጉ እንጂ ትምህርት ቤቱ ለወላጆች እና ለመምህራን የገባውን ቃል በማጠፍ በአማካይ ከ10 - 15 በመቶ ብቻ ጭማሪ ማደረጉ ቅሬታ ማሳደሩን ገልጸዋል።

- የትምህርት ቤቱ አስተዳደር የተከተለው አሰራር ልክ አይደለም ያሉት ወላጆች " ጥሩ መምህራን እንዳይለቁብን የደሞዝ ጭማሪ ይደረግላቸው፣ የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ባለሙያ ይቀጠርላቸው፣ አስፈላጊ የትምህርት መማሪያ ግብአቶች ይቅረቡ " ተብሎ በተደጋጋሚ ለት/ ቤቱ ጥያቄ ቢቀርብም ትምህርት ቤቱ ምላሽ መንፈጉን ወላጅ የሆኑት ዶ/ር ቴዎድሮስ ወ/ገብርኤል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።

ይህንን ተከትሎ የተማሪ ወላጆች ፦
° ልጆቻችንን የመማሪያ መፅሃፍት በሌለበት ፣
° ጥያቄአችን ባልተመለሰበት ፣
° መምህራን አላግባብ እየተባረሩ ባለበት ሁኔታ ልጆቻችንን ወደ ት/ቤት የምንልክበት ምክንያት የለም በማለት ልጆቻቸውን ከታህሳስ 3/ 2016 ዓ/ም ጀምሮ ወደ ትምህርት ቤት እንዳይሄዱ አድርገው ቆይተዋል።

የአንድነት ትምህርት ቤት የወላጅ የአስተማሪዎችና የተማሪዎች ማህበር (PTSA) ጉዳዩን ወደ ትምህርት ሚኒስቴር የወሰደው ሲሆን በትምህርት ሚኒስቴር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ መሪነት በትምህርት ቤቱ እና በወላጅ የአስተማሪዎችና የተማሪዎች ማህበር ኮሚቴ መሃል ውይይት ተደርጓል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህን ጉዳይ በተመለከተ የአንድነት ኢንተርናሽናል ት/ቤት ርዕሰ መምህር የሆኑትን ዶ/ር ወርቁ ነጋሽን አነጋግሯል።

ዶ/ር ወርቁ ምን አሉ ?

* በትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የተመራው ውይይት " #ፍሬያማ ነበር " ብለዋል።

* ከስራ የተሰናበቱት 4 መምህራን እና 1 ድጋፍ ሰጪ ሰራተኛ ወደስራ ገበታቸው እንዲመለሱ መወሰኑን ገልፀውልናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፦
>  የመምህራን ደሞዝ ፣
> የወላጆች የተማሪና መምህራን መፅሃፍ ችግር ጥያቄ ላይ የተደረሰው ስምምነት ምን እንድነው ? ብሎ ርዕሰ መምህሩን ጠይቋል።

ርዕሰ መምህሩ ዶ/ር ወርቁ ፤ ስብሰባው ላይ አዲስ የወላጅ ተወካይ ተመርጦ በሚቀጥሉት ቀናት የትምህርት ሚኒስትሩ የመደቡት ተወካይ በሚገኙበት ድርድር እንዲደረግባቸው አቅጣጫ ተቀምጧል ብለዋል።

የተባረሩት መምህራን ወደስራቸው ሲመለሱ ፦

° በፋይላቸው ምንም አይነት መጥፎ ሪከርድ ሳይኖር፣
° የነበራቸው ጥቅማ ጥቅም እንደተጠበቀ ሆኖ
° የተፈጠረው ስህተት ታምኖ #ከይቅርታ ደብዳቤ ጋር እንዲመለሱ የሚል ውሳኔ መወሰኑን ሰምቻለሁ ያሉት መ/ርት ብሩክታይት ፍቃዱ ነገር ግን በይፋ ወደ ት/ት ቤቱ መመለሳቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ እንዳልደረሳቸው ገልፀዋል።

ት/ቤቱ ያለአግባብ ከስራ ያሰናበታቸውን 5 ሰራተኞች ወደስራቸው ለመመለስ በመወሰኑና እንዲሁም ለሌሎች ጥያቄዎች መፍትሔ ለማምጣት እንዲቻል ለመወያየት ዝግጁነቱን በማሳየቱ ልጆችን በቤት ለማቆየት የተላለፈው ውሳኔ አብቅቶ ልጆቹ ወደ ት/ቤት እንዲሄዱ ማድረጋቸውን ያናገርናቸው ወላጆች ሲያስረዱ በዛሬው እለት ትምህርት መጀመሩን ርዕሰ መምህሩ አሳውቀውናል።

የትምህርት ቤቱ የወላጅ የአስተማሪዎችና የተማሪዎች ማህበር (PTSA) በት/ቤቱ ርዕሰ መምህር ዶ/ር ወርቁ ነጋሽ የተወሰዱ የእርምት እርምጃዎች ይበል የሚያሰኝ መሆኑን ጠቁሞ ሆኖም መስተካከል ያለባቸው ብዙ ጉዳዮች ስላሉ ከወላጅ ተወካዮች ጋር ለመስራት የገቡትን ቃል #እንዲያከብሩ ጠይቋል።

@tikvahethiopia