TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሰበር ዜና‼️

"ወንጀል ሰርተው ከሀገር የወጡ የሱማሌ ክልል #ባለስልጣናትን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ዝግጅት #ተጠናቋል"- ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ
.
.
.
በሱማሌ ክልል በተፈጠረው ግጭት እጃቸውን በማስገባት ወንጀል ሰርተው ከሀገር የወጡ ባለስልጣናትን ወደሀገር #በመመለስ በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ከተሸሸጉባቸው ሀገራት ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አስታወቀ።

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ #ዝናቡ_ቱኑ ዛሬ ከሰዐት በፅ/ቤታቸው በሰጡት መግለጫ 46 ያህል ተጠርጣሪዎች በሱማሌ ክልል በተፈጠረው ግጭት የሰው ህይወት #እንዲጠፋ፣ ህገመንግስታዊ ስርዐትን ለመናድ በመንቀሳቀስ ንብረት እንዲወድምና በተያያዥ ወንጀሎች መጠርጠራቸውን የተናገሩ ሲሆን ስድስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ሌሎቹ 40 ግን በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገር ተሸሽገዋል ብለዋል።

እንደ አቶ ዝናቡ ገለፃ ከሀገር የወጡ ባለስልጣናትን ወደሀገር በመመለስ በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ከተሸሸጉባቸው ሀገራት ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን በሀገር ውስጥ የተደበቁትንም አፈላልጎ በህግ ተጠያቂ ለማድረግ እየተሰራ ነው።

የተወሰኑ ተጠርጣሪዎች #ያለመከሰስ መብት ያላቸው በመሆኑ መብታቸውን #በማንሳት በቁጥጥር ስር ለማዋል ስራዎች እየተሰሩ ነው ተብሏል።

ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ትልቅ ዝግጅት ተደርጓል ያሉት አቶ ዝናቡ ህዝቡ የተሸሸጉ ግለሰቦችን አሳልፎ በመስጠት ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞ጥር 17/2011 ዓ.ም.

ዘንድሮ ለሰባተኛ ጊዜ የሚከበረው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቀን በአየር ኃይልና በኦሮሚያ ክልል መንግሥት ትብብር #በአዳማ ከተማ እንደሚከበር፣ የኢፌዴሪ መከላከያ ኢንዶክትሪኔሽንና የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት አስታውቋል፡፡ በዓሉም የካቲት 7 ቀን 2011 ዓ.ም. እንደሚከበር ተገልጿል፡፡
.
.
ዛሬ ማለዳ በተካሄደው የዱባይ ማራቶን ጌታነህ ሞላ የቦታውን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አሸንፏል። በሴቶች ኬንያውያን እኤአ ከ2006 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አሸንፈዋል፡፡
.
.

አቶ #በረከት_ስምዖንና አቶ #ታደሰ_ካሳ በተጠረጠሩበት የጥረት ኮርፖሬት የሀብት ብክነት ጉዳይ ዛሬ በባሕር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡
.
.
#የአገር_መከላከያ_ሰራዊት አባላት እና የሶማሌ ክልል #ልዩ_ሀይል አባላት ዛሬ #በጅግጅጋ_ከተማ የፅዳት ስራ አከናውነዋል።
.
.
በነጭ ሣር ፓርክ ላይ ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት እሳት ተነስቶ 1 ሺ ሄክታር የሚሆን የፓርኩ ክፍል ወድሟል።
.
.
በድሬዳዋ ከተማ #የተቀሰቀሰው_ተቃውሞ ዛሬ ጥር 17/2011 ዓ.ም. ቀጥሎ ውሏል። የኢንተርኔት አገልግሎት ተዘግቷል።
.
.
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2 ዙር በተካሄደ ነፃ የስራ ዘመቻ 3.5 ሚሊዮን ብር የሚገመት ስራ መሰራቱን ተናግሯል።
.
.
የኢፌዲሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የ100 ቀናት እቅዱን በአርባምንጭ ከተማ ገምግሟል።
.
.
በሱማሌ ክልል በተፈጠረው ግጭት እጃቸውን በማስገባት ወንጀል ሰርተው ከሀገር የወጡ ባለስልጣናትን ወደሀገር #በመመለስ በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ከተሸሸጉባቸው ሀገራት ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አስታውቋል።
.
.
በሳኡዲ አረቢያ በተለያየ ምክንያት ታስረው የነበሩ 368 ኢትዮጵያውያን ዛሬ ወደ አገራቸው ገብተዋል።
.
.
በድሬዳዋ ከተማ የተፈጠረው የሰላም መደፍረስ የሕዝቡን አብሮነት እና ተቻችሎ የመኖር እሴት የሚሸረሽር በመሆኑ ሰላምን በማወክ ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የከተማ አስተዳደሩ አሳስቧል።
.
.
በኢትዮጵያ #የመጀመሪያ የሆነ የሚዲያ ኤክስፖ በኤግዚብሽን ማዕከል ዛሬ ተከፍቷል።
.
.
የቀድሞ የደህንነት ኃላፊ አቶ #ጌታቸው_አሰፋን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከክልሉ መንግሥት ጋር እየሰራ እንደሆነ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጿል።
.
.
በጉጂ ዞን ይንቀሳቀሱ የነበሩ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር /ኦነግ/አባላት ከጫካ ወጥተው #በሰላማዊ መንገድ ለመታገል መወሰናቸውን ገልፀዋል።
.
.
የሱማሌ ክልል መሪ--አቶ #ሙስጠፋ_ኡመር-የፌዴራል ገንዘብ ሚኒስትሩን አቶ #አህመድ_ሺዴን-በይፋ በክልሉ መንግስት ላይ "ዓመፃ-ክህደት በመፈፀም" እጅግ ከባድ ወንጀል #ከሰዋል

ምንጭ፦ አዲስ ስታንዳርድ፣ fbc፣ ኢዜአ፣ ኢ.ፕ.ድ.፣ elu፣ ቢቢሲ፣ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት

.
.
አመሰግናለሁ! ሰላም እደሩ!!
ሀገራችን ቸር ትደር!!
ጥር 17/2011 ዓ.ም.
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰላም...

ባለፉት ቀናት #ኢትዮጵያ የተረጋጋች፣ ኢትዮጵያውያንም ሰከን ያሉ ይመስላል። በምዕራብ ጎንደርና በደቡብ ክልል የተለያዩ ዞኖች የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀያቸው #በመመለስ ላይ ይገኛሉ።

#ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia