TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ለማስታወስ ፖሊስ የኢንጂነር ስመኘው በቀለን ግድያ እና ከግድያው ጋር ተያይዞ የተደረጉትን ምርመራዎች በተመለከተ #በጥቂት ቀናት ውስጥ ለህዝብ ይፋ አደረጋለሁ ብሎ ከተናገረ ሳምንት አልፎታል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ለማስታወስ ኢትዮጵያ ጀግናውን ኢንጂነር ስመኘው በቀለን ካጣች ሁለት ሳምንት ሆኗታል። እስከ ዛሬ ድረስ ፖሊስ ስለደረሰበት የምርመራ ውጤት ለህዝብ ይፋ አላደረገም።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#YouTube ቲክቫህ ኢትዮጵያ የዩትዩብ ቻናል የለውም! ከሰሞኑን በTIKVAH-ETH (Tikvah-Ethiopia) ስም ዩትዩብ ላይ እውቅና የሌላቸው፣ ሰዎችን የሚያሸብሩና የሚያስደነግጡ የተለያዩ መረጃዎች እየተሰራጩ እንደሆኑ እየተመለከትን ነው። እነዚህ የሚሰራጩት መረጃዎች በቀን ውስጥ ከ50,000 በላይ ሰዎች አንዳንዴም በመቶ ሺ የሚጠጉ ሰዎች ጋር እየደረሱ በርካቶችን እያሳሳቱ ነው። የቲክቫህ ባለቤቶች…
#YouTube

ዩትዩብ ላይ በTIKVAH-ETH ስም ሀሰተኛ መረጃዎችን ሲያሰራጩ የነበሩ አካላት አጠቃላይ መረጃዎችን ከገፁ ላይ አጥፍተውታል ፤ በተጨማሪ ስሙን ከTIKVAH-ETH ወደ "Hagere Ethiopia ሀገሬ ኢትዮጵያ" ቀይረውታል።

በTIKVAH-ETH የቤተሰብ አባላት ስም የዩትዩብ ገፅ ከፍተው ሀሰተኛ መረጃዎችን ሲያሰራጩ የነበሩት አካላት ላይ አስፈላጊው የማጣራት ስራ እየተሰራ ነው።

ምንም እንኳን ከዚህ ቀደም ያሰራጯቸውን ሀሰተስኛና ሰዎችን ሚያሸበሩ መረጃዎች ከገፃቸው ቢያጠፉም በአንድ እና በሁለት ቀን በመቶ ሺ ለሚቆጠር የዩትዩት ተጠቃሚ ደርሰዋል ፤ እኛም እኚህ አካላት ማንነታቸውን እንደደረስንበት #በህግ የምናስጠይቃቸው ይሆናል።

በድጋሚ #ለማስታወስ TIKVAH-ETHIOPIA ዩትዩብ ላይ ምንም አይነት ቻናል #የለውም። አሁንም በቲክቫህ ስም ዩትዩብ ቻናል ከፍተው #ገንዘብ ለመሰብሰብ ሲሉ ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ ወገኖች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እናሳስባለን።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ለዘንድሮ ተፈታኞች ማስታወሻ!

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር የዘንድሮውን የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ፈተናዎችን በወረቀት እና ቴክኖሎጂን በመጠቀም በኦን ላይን ለመስጠት ዝግጅት እያጠናቀቀ መሆኑን መረጃ ሰጥተናችሁ ነበር።

ተማሪዎች ለምትወስዱት ፈተና ዝግጅት እያደረጋችሁ ፈተና የሚሰጥበት ቀን እስኪገለፅ እንድትጠብቁ ፤ ወላጆች ልጆችን በማበረታታት ለፈተናው እንዲዘጋጁ ማድረጉን እንዳትዘነጉ #ለማስታወስ እንወዳለን።

@tikvahethiopiaBot @tsegabwolde