#ፀደይ_ባንክ
አማራ ብድር እና ቁጠባ ተቋም (አብቁተ) በሚል ስያሜ ከሩብ ክፍለ ዘመን በላይ ሰፊ መሠረቱን በገጠር አድርጎ ብዙኃኑን የፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽና ተጠቃሚ በማድረግ የቆየውና በያዝነው ዓመት መጀመሪያ ላይ ወደ ግዙፍ ባንክነት ያደገው ፀደይ ባንክ አርቲስት ሰሎሞን ቦጋለን የብራንድ አምባሳደሩ አድርጎ ሰይሟል፡፡
ባንኩ በስካይ ላይት ሆቴል ባዘጋጀው ፕሮግራም ላይ እንዳስታወቀው፥ በበርካታ ፊልሞችና ድራማዎች ላይ በመተወን ታዋቂነት ያተረፈውና በበጎ አድራጎት ሥራው ጎልቶ የሚጠቀሰው አርቲስት ሰሎሞን ቦጋለ፥ በሁሉም ቦታ፣ ሁሉንም ማኅበረሰብ በቅርበትና በልዩነት ማገልገል መለያው የሆነው ፀደይ ባንክን በትክክል የሚወክል መሆኑንና በመልካም ሥነ ምግባሩና ስብዕናው የባንኩ ብራንድ አምባሳደር እንዲሆን በሙሉ እምነት መመረጡን ገልጿል፡፡
አርቲስት ሰሎሞን ቦጋለ በሕዝብ ዘንድ ታላቅ ተወዳጅነትን ያተረፈ አርቲስት ሲሆን በተሰማራበት የጥበብ ዘርፍ ከ68 በላይ ፊልሞችን፣ ከ16 በላይ የመድረክ ቴአትሮችን፣ ከ8 በላይ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማዎችን እና በርካታ የራድዮ ድራማዎችን የተጫወተ ከመሆኑም በላይ ኅብረት ለበጎ በሚል መርሕ በሚያከናውናቸው የበጎ አድራጎት ሥራዎቹ የሚታወቅና በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት በተለያዩ ዘርፎች በርካታ ሽልማቶችን ያገኘ ነው፡፡
የቀድሞው አማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም(አብቁተ)፥ የዛሬው ፀደይ ባንክ ፦
- በ3 ሚሊዮን ብር ካፒታል ነው ጉዞውን የጀመረው። ዛሬ የተጣራ ካፒታሉ ከ11.6 ቢሊዮን ብር በላይ ሆኖ ጠቅላላ ሀብቱም ከ49.7 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሷል፡፡
- በአሁኑ ወቅት ከ13 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን ያፈራ ሲሆን በመላው ሃገሪቱ ከ500 በላይ ቅርንጫፎች አሉት።
- ባንኩ ፤ ከ12,270 በላይ ለሆኑ ዜጎች የሥራ እድል ለመፍጠር ችሏል።
- በአዲስ አበባ ከተማ ሰንጋ ተራ አካባቢ ባለ 39 ወለል የዋና መሥሪያ ቤቱን ትልቅና ዘመናዊ ሕንጻ አስገንብቶ በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል።
@tikvahethiopia