TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ልጆቼ ርቧቸው ሲያለቅሱብኝ አእምሮዬ በጣም ይጨናነቃል ፤ የማበላቸው የለኝም ሲጨንቀኝ ጥያቸው ወጣና ዛፍ ስር እቀመጣለሁ " -  ወ/ሮ ትብለፅ ሃዱሽ (የኢሮብ ወረዳ ነዋሪ) #እናት

በትግራይ በነበረው ጦርነት ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው የሚገኙ የኢሮብ ወረዳ ነዋሪዎች እርዳታ መቋረጡን ተከትሎ የከፋ ችግር ላይ መሆናቸው ለክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ ተናግረዋል።

ወ/ሮ ትብለፅ ሃዱሽ፤ በጦርነቱ ምክንያት ከቄያቸው ተፈናቅለው ህፃናት ልጆቻቸውን ይዘው በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ ይገኛሉ።

" የሰብዓዊ እርዳታ ካቆመ ብዙ ጊዜ ተቆጥሯል " ያሉት ወ/ሮ ትብለፅ ልጆቻውን ለመመገብ መቸገራቸውን ገልፀዋል።

ወ/ሮ ትብለፅ ፤ " በጦርነቱ ምክንያት ተፈናቅዬ በመጠለያ ውስጥ ነው ያለሁት፤ እርዳታ ብዙም አላገኝም ነበር  ፤ አሁን ደግሞ ካቆመ ብዙ ጊዜ አልፎታል። በዚህ ሁኔታ ቤተሰብ ለማስተዳደር በጣም ከባድ ነው በፈጣሪ ኃይል ነው ያለነው። " ሲሉ ተደምጠዋል።

" እርዳታ ቆሟል ፤ ይህ ከፍተኛ ስጋት ነው ያሳደረብን " የሚሉት ወ/ሮ ትብለፅ " ልጆቼ ርቧቸው ሲያለቅሱብኝ አእምሮዬ በጣም ይጨናነቃል ፤ የማበላቸው የለኝም ሲጨንቀኝ ጥያቸው ወጣና ዛፍ ስር እቀመጣለሁ " ሲሉ ምን ያህል አስከፊ ሁኔታ ላይ እንዳሉ አስረድተዋል።

ቀድሞውኑም ችግር ላይ የነበሩት እነዚህ ዜጎች አሁን ላይ እርዳታ ማቆሙ የከፋ ችግር ላይ ጥሏቸዋል።

አንዲት የኢሮብ ነዋሪ በሰጠችው ቃል " በአሁን ሰዓት ለህፃናት #ወተት ለመስጠት ቀርቶ አንድ ዳቦም ቢሆን አይናቅም ለእኛ ትልቅ እርዳታ ነው ፤ እርዳታ ወደዚህ መምጣት ካቆመ ብዙ ወራት አልፏል ረሃብ ላይ ነው ያለነው " ስትል ሁኔታውን ገልጻለች።

ወ/ሮ ትብለፅ ሃዱሽ፤ አሁን ላይ የተገኘው ሰላም በጣም እንደሚያስደስት ገልፀው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

" ህዝባችን ወደቦታው ተመልሶ ሰርቶ እንዲበላና ከእርዳታ ጠባቂነት እንዲላቀቅ የሚመለከታቸው አካላት በጋር መስራት አለባቸው " ሲሉ መልዕልት አስተላልፈዋል።

የኢሮብ ነዋሪዎቹ በአካባቢያቸው የኤርትራ ኃይሎች እንደሚንቀሳቀሱ በመጠቆም ይኸው ኃይል ከአካባቢው ለቆ እንዲወጣ እንዲደረግ የሚመለከታቸው አከላት እንዲሰሩ ጥሪ ማቅረባቸውን የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

@tikvahethiopia