TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የጅማ አባጅፋር ደጋፊዎች ለኢትዮጵያ ሚዲያዎች ያስተላለፉት መልዕክት...⬇️

ይድረስ ለኢትዮጵያ ሚዲያዎች።

#ውድ የኢትዮጵያ ሚድያዎች በያላቹበት የጅማ አባጅፋርን ውድቀት የምትመኙ እንደምን አላቹ እኛ ጅማዎች በመጣን በአመታችን እንደዚህ ታላላቅ ቡድኖች የሚያስጨንቅና ሌሎችን የሚያሳስቅ ቡድን ገንብተን ይኸው ድፍን ዓመት ሊሞላን ነው

#እናንተ ሚድያዎች ግን ምን ያክል አድሎ በቡድኖች ላይ እንደምታደርጉ ያየንበትን ዓመት አሳልፈናል የኛ ጅማ አባጅፋር ዓመቱን በሙሉ እንደዚህ የሚገርም እንቅስቃሴ እያደረገ አንድም ግዜ ስለክለባችን ድንቅ ብቃትና ጥንካሬ ዘገባ ሳትሰሩ ውጤቱንና ደረጃውን ከመግለፅ ባልዘለለ ዓመቱን ዘለቃቹት

#እኛ ጅማዎች ስለ ክለባችን እንድታወሩ ለማድረግ ቢራ ፋብሪካ🍺 የለንም ነገር ግን ድንቅ የሆነ የፍቅር መገለጫ ቡና☕️ አለን ፍቅር ማሳየት እና ቡና በነፃ ማጠጣት እንጂ እንድታወሩልን መቼም ገንዘብ አንሰጣቹም ነገር ግን ለሙያቹ ታማኝ ሆናቹ ሁሉንም አገልግሉ

#ይህን ስንል ግን በየቦታው እየተጓዙ ጫወታውን በቀጥታ በRadio ለጅማና ወዳጆቿ የሚያስተላልፉትን እና OBN, Fano እና ጅማ ማህበረሰብ ሳናመሰግናቹና ሳናደንቃቹ አናልፍም

#በስተመጨረሻም ገና ቻምፒዎን እኖናለን ገና አንድ ነጥብ ስንጥል ምን እንዳላቹ እናውቃለን እኛ በልጆቻችን ትልቅ እምነት አለን በወሬያቹ ቢሆንማ እነ....... ቻምፒዮንስሊግ ሁላ ባነሱ ነበር

#እኛ ግን ፍቅር ነን እንወዳቹዋለን ማብራርያም ከፈለጋቹ ኑ ቡና እየጠጣን እንጨዋወት

#የኛ ጅማ አባጅፋር ታሪክ መስራቱን ይቀጥላል
#ይህን መረጃ በየSocial ሚድያው Share በማድረግ እየተሰራብን ያለውን ለሰው እናሳውቅ።

@tsegabwolde @tikahethiopia
#update ኮ/ል በዛብህ ጴጥሮስ⬆️

በኢትዮ- ኤርትራ ጦርነት ወቅት የሚያበረው ተዋጊ አውሮፕላን ተመቶ ወድቆ በኤርትራ ቁጥጥር ስር ውሎ ስለነበረው ኮ/ል በዛብህ ጴጥሮስ ወንድማቸውን ፕ/ር በየነ ጴጥሮስን በተለይ "ሊፈታ ነው" ስለሚባለው ጉዳይ #ENF ከቀናት በፊት አናግሯቸው ነበር።

በጉዳዩ ላይ ፕሮፌሰር በየነ ይህን ምላሽ ነው የሰጡት⬇️

"እኛ ጥረት እየተደረገ ነው ተብሎ በስማ በለው ከሚወራው ውጪ ምንም የምናውቀው ጉዳይ የለም። እኔን የሚገርመኝ ወንድሜ ልጆች እና ቤተሰብ እንዳለው እየታወቀ እንዲህ አይነት ያልተረጋገጠ ወሬ መወራቱ ነው። በሶሻል ሚድያ የሚወራው misinformation ነው። እኔም አልኩ እየተባለ የሚወራው ሀሰት ነው። ቤተሰብ ምንም መረጃ የለውም"

©Elias Meseret

#ውድ ኢትዮጵያዊያን የሀሰት መረጃዎች ከማሰራጨትና ለሰዎች ከማጋራት ተቆጠቡ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ውድ_ቤተሰቦቻችን_ጥንቃቄያችሁን_አጠናክሩ

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1,621 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ13 ሰዎች ህይወት ደግሞ ጠፍቷል።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 10,620 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 1,621 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

በተመሳሳይ በ24 ሰዓታት ውስጥ 13 ዜጎች ህይወታቸው አልፏል።

@tikvahethiopia
#ውድ_ቤተሰቦቻችን_ጥንቃቄያችሁን_አጠናክሩ😷

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1,458 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ12 ሰዎች ህይወት ደግሞ አልፏል።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 9,292 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 1,458 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

በተመሳሳይ በ24 ሰዓታት ውስጥ 12 ዜጎች ህይወታቸው አልፏል።

ወደፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡ ታማሚዎች ቁጥር በእጅጉ እየጨመረ ሲሆን በአሁን ሰዓት 580 ሰዎች በፅኑ ታመው ህክምና ላይ ናቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ ቤተሰቦች ስለ አንፋጋው የኢትዮጵያ የሙዚቃ ሰው ምን አሉ ? ፍርድዮስ ዩሱፍ ለኤፍ ኤም 97.1 ሬድዮ የተናገሩት ፦ " ... አሊ በራ ሞተ ምናምን እያሉ በየጊዜ ያወጣሉ። ነገር ግን የትላንትናው በጣም እኛንም የጎዳ ያሳዘነን ነው። ከትላንት ወዲያ ነው ከሆስፒታል የወጣው ፤ በጤንነት ጥዋት ላይ ደግሞ የሚገርመው በእግሩ እኔ ሄዳለሁ አብራችሁኝ ሂዱ ብሎ በመኪና ይዘነው…
አንጋፋው የኢትዮጵያ አርቲስት ክቡር ዶ/ር አሊ ቢራ #በህይወት አለ።

በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ አንጋፋው የሀገራችን አርቲስት ክቡር ዶክተር አሊ ቢራ " አረፈ / ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ " እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው።

ክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ ባጋጠመው የጤና እክል የተነሳ በአዳማ ጄነራል ሆስፒታል ለላፉት ቀናት #የሕክምና_ክትትል እየተደረገለት ይገኛል።

የ75 ዓመቱ አርቲስት አሊ ቢራ ፤ ከዚህ ቀደምም የጤና እክል አጋጥሞት በአዲስ አበባ እና አዳማ ከተሞች በሚገኙ ሆስፒታሎች የውስጥ ደዌ ህክምና ተደርጎለት ነበር።

ከዚህ ቀደም ህክምና ላይ እያለ ህይወቱ እንዳለፈ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሀሰተኛ መረጃዎች ተሰራጭተው የነበረ ሲሆን በዚህ ሀሰተኛ መረጃ ቤተሰቦቹ እጅግ #መጎድታቸው እና #ማዘናቸውን መግለፃቸው ይታወሳል።

ሳናረጋግጥ የምናወራው ወሬ ምን ያህል የሰዎችን ህይወት እንደሚበጠብጥ እናውቀው ይሆን ?  ሁሉ ነገር ስርዓት አለው ፤ የሰውን ሀዘን ለማርዳት ይሄን ያህል መቸኮል ምንድነው ? ቤተሰብ ዘመድ አዝማድ ወዳጅ ይደነግጣል አይባልም ? በችኮላ እና መረጃ አደረስኩ ለማለትና ለዩትዩብ ገንዘብ መሰብሰቢያ ሲባል ያልተረጋገጠ መረጃ ማሰራጨት ፍፁም ስርዓት የጎደለው ተግባር ነው።

#ውድ_ቤተሰቦቻችን ፤ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የምትመለከቱትን ሀሰተኛ መረጃ ከማጋራት ተቆጠቡ።

@tikvahethiopia