TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Amhara #Afar #Tigray #ICRC #ERCS

በአማራ እና በአፋር ክልሎች ውስጥ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የተፈናቀሉ ዜጎች ህይወታቸውን ለማዳን ቤታቸውን ጥለው በመሠደዳቸው በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ።

ተፈናቃዮቹ ምቹ ማረፊያ ባለማግኘታቸው በተጨናነቁ መጠለያዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ እንዲሁም በማንኛውም ክፍት ቦታ ላይ ለመተኛት ተገደዋል፡፡

ተፈናቃዮቹ በተሰደዱበት አካባቢ በሚኑሩ ማህበረሰቦች ቢደገፉም፣ በቂ የውሀና የምግብ አቅርቦት ይሻሉ።

የጤና ተደራሽነት በአሁኑ ወቅት ዋነኛው የሰብአዊ ጉዳይ ሆኗል።

በቅርቡ በአማራ እና በአፋር ክልሎች የተካሄደውን ግጭት ተከትሎ ፣ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ወደ ጤና ተቋማት የሚመጡ የቆሰሉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው።

የአለምአቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጋር በመተባበር በአማራና አፋር ክልሎች የመጠለያ፣ የንጽህና መጠበቂያ፣ የጤና አገልግሎትና ሌሎች የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፎችን እያደረገ ነው፡፡

ከነሐሴ ወር መጀመሪያ እስካሁን ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በትግራይ፣ አማራና አፋር ክልሎች ለ100,600 ሰዎች ፦
- ብርድልብሶች፣
- የማብሰያ ዕቃዎች
- የፋኖስ መብራቶች የመሳሰሉትን ቁሳቁሶች ስርጭት አድርጓል፡፡

በትግራይ ክልል በሚገኙ 18 ሆስፒታሎች ለ145,000 ህሙማንና የህክምና ባለሙያዎች የምግብ ድጋፍ የተደረገ ሲሆን በአማራ ክልል ለሚገኙ 13 ሆስፒታሎች ደግሞ 2000 ቁስለኞችን ለማከም የሚበቃ መድሐኒት ተሠራጭቷል፡፡

በተጨማሪም በአፋር ለሚገኘው የዱፕቲ ጠቅላላ ሆስፒታልና በትራይ የሱሁልና ሽራሮ ሆስፒታሎችን ጨምሮ በትግራይ ክልል የሚገኙ 14 የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ጣቢያዎችን መሠረተ ልማት መልሶ የመገንባት ስራም ተሠርቷል፡፡

ያንብቡ : telegra.ph/ERC-09-12

@tikvahethiopia
#ERCS

• የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የአምቡላንስ ሹፌር በታጣቂዎች ተገደለ።

• ማኅበሩ በባልደረባው ሞት የጥልቅ ሐዘን እንደተሰማው ገልጾ ግድያውን አውግዟል። ታጣቂ ሃይሎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም ማህበሩ ተማፅኗል።


የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የሰሜን ጎንደር ቅርንጫፍ #የአምቡላስ_ሾፌር የነበረው አቶ መንግስት ምንይል ታጣቂ ሃይሎች በፈፀሙት ጥቃት ተገድለዋል።

ማህበሩ፤ ግድያውን በአፅንዖት አውግዟል።

አቶ መንግስት ምኒል በምዕራብ ደንቢያ ሰብዓዊ አገልግሎት በመስጠት ላይ የነበረና በሰብዓዊ ህይወት የማዳን ስራ ወልቃይት አዲ ረመፅ ሆስፒታል ተመድቦ አገልግሎት በመስጠት ላይ ነበር።

አቶ መንግስት አድዋ፣ ትግራይ ተሰማርተው በግጭት የተጎዱ ወገኖችን በማገዝ ላይ ከነበሩ 2 አምቡላንሶች አንዱን በማሽከርከር ከአድዋ ወደ ወልቃይት አዲ ረመፅ ሆስፒታል ቁስለኞችን ለማድረስ በተንቀሳቀሰበት ወቅት ቁስለኞቹን ጨምሮ በታጣቂ ሃይሎች በተፈፀመባቸው ጥቃት መገደላቸውን የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ገልጿል።

የአምቡላንስ ሹፌሩ አቶ መንግስት ምኒል የ40 ዓመት ጎልማሳ እና የሁለት ሴት ልጆች አባት ነበር።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ አምቡላንስ በማሽከርከር ሰብኣዊ አገልግሎት በመስጠት ላይ በነበረው  ባደረባው ግድያ ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማው ገልጿል።

በመላ ሀገሪቱ በሰብዓዊ አገልግሎት የተሰማሩ የቀይ መስቀል ማኅበር  ሠራተኞችና በጎ ፈቃደኞችን ሰብዓዊ ተግባራቸውን በገለልተኝነት እና በአለማዳላት መንፈስ በነፃነት ተንቀሳቅሰው መስራት እንዲችሉ፣ እንዲሁም ደህንነታቸው እንዲጠበቅ፣ ታጣቂ ሃይሎች ከእንደዚህ አይነት ጥቃት እንዲቆጠቡ ተማፅኗል።

@tikvahethiopia
#ERCS

" በአምቡላንስ ተሽከርካሪዎች ላይ የሚፈፀም ጥቃት በተለይም በወላድ እናቶች ላይ የሚፈፀም ጥቃት መሆኑን ሁሉም አካል ሊያውቀው ይገባል " - ቀይ መስቀል

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የምዕራብ ወለጋ ዞን ሀሩ ወረዳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ንብረት የሆነ ማኅበሩ ለሰብዓዊ አገልግሎት የሚጠቀምበት ታርጋ ቁጥሩ ET05-01939 አምቡላንስ ተሽከርካሪ በዛሬው ዕለት ማለትም ጥቅምት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከንጋቱ 12፡00 ሰዓት በሀሩ ወረዳ ጤና ጣቢያ ግቢ ውስጥ በቆመበት በታጣቂ ኃይሎች ተቃጥሏል፡፡

ማኅበሩ መሰል ድርጊቶች ኢትዮጵያ የፈረመችውን ዓለም አቀፍ የጄኔቫ ሥምምነቶች የሚጥሱና በኢትዮጵያ የወንጀል ህግ የሚያስጠይቁ መሆናቸውን ገልጿል።

በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአምቡላንስ ተሽከርካሪዎቹ ላይ እየደረሱ ያሉ ጥቃቶች በሰብዓዊ አገልግሎቱ ላይ እንቅፋት እየፈጠሩበት እንደሚገኙ ማህበሩ አመልክቷል።

በአምቡላንስ ተሽከርካሪዎች ላይ የሚፈፀም ጥቃት በተለይም በወላድ እናቶች ላይ የሚፀም ጥቃት መሆኑን ሁሉም አካል ሊያውቀው ይገባል ሲል አስገዝቧል።

ማህበሩ " አሁንም በድጋሚ በመላው አገራችን በሰብዓዊ አገልግሎት የተሰማሩ የቀይ መስቀል ሠራተኞችና በጎፈቃደኞች እንዲሁም አምቡላንሶችና ሌሎች ተሽከርካሪዎች በነፃነት ተንቀሳቅሰው መስራት እንዲችሉ፣ ደህንነታቸው እንዲጠበቅ፣ መሰል ድርጊቶችን የሚፈፅሙ አካላት ከእንደዚህ አይነት ድርጊት እንዲቆጠቡ እንጠይቃለን " ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE  የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ያወጣውን የሃዘን መገለጫ ዋቢ በማድረግ ጥር 3 /2016 በትግራይ ማእከላዊ ዞን ‘የእምባስነይቲ ቅርንጫፍ’ የአምቡላንስ ሹፌር አቶ ወልዱ አረጋዊ በርሀ የወላድ እናትን ህይወት ለማዳን እያሽከረከረ ባለበት ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች በተተኮሰበት ጥይት ህይወቱ ማለፉ መዘገባችን ይታወሳል። የቀይ መስቀል የአምቡላንስ ሹፌሩ እንዴት ለህልፈት እንደበቃ የሚያትት…
#ERCS

በአማራ ክልል #ታጣቂዎች የሰብዓዊ አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎችን መውሰዳቸው ተሰማ።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ንብረት የሆኑ ባለ 5 በር ላንድክሩዘር የሰሌዳ ቁጥራቸው ፦
➡️ 5-02826
➡️ 5-02830 ተሽከርካሪዎች የካቲት 6 ቀን 2016 ዓ.ም ማኅበሩ የሚያከናውነውን ሰብዓዊ ተግባር ለማገዝ ወደ ደቡብ ጎንደር እና ሰሜን ጎንደር ዞኖች በመጓዝ ላይ እያሉ በምስራቅ ጎጃም ዞን ከሞጣ ከተማ 30 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ልዩ ሥሙ " አስተርዮ ማርያም " በሚባል ቦታ በታጠቁ ኃይሎች ተወስደዋል፡፡

ማህበሩ ከላይ የተጠቀሱትን ተሽከርካሪዎች በመጠቀም ለሚፈፀመው የትኛውም ዓይነት ተግባር ኃላፊነት እንደማይወስድ አሳውቋል።

ተሽከርካሪዎቹን የወሰዱት ታጣቂ ኃይሎች ለማኅበሩ እንዲመልሱና ለተለመደው ሰብዓዊ አገልገሎት ተግባር እንዲውሉ ጠይቋል።

በተመሳሳይ የካቲት 09 ቀን 2016 ዓ.ም በዋግ ኸመራ ዞን ያጋጠመውን ድርቅ ተከትሎ ለጉዳት የተጋለጡ ወገኖችን ለመርዳት የሚያስችል ሰብዓዊ ተግባር አከናውኖ ከሰቆጣ ከተማ ወደ ኮረም ከተማ በመጓዝ ላይ በነበረ የማኅበሩ ቀላል ተሽከርካሪ ኮረም ከተማ ለመድረስ 3 ኪ.ሜ ሲቀረው ልዩ ሥሙ " ፋላ ገበያ " በተባለ አካባቢ በታጣቂ ኃይሎች በተከፈተበት ድንገተኛ ተኩስ #በሰው_ላይ_የደረሰ_ጉዳት_ባይኖርም በተሽከርካሪው ላይ ጉዳት ሊደርስ መቻሉ ተገልጿል።

ማኅበሩ ከቀን ወደ ቀን በሠራተኞቹ፣ በጎፈቃደኞቹ እና ተሽከርካሪዎቹ ላይ በሚፈፀምበት ጥቃት ምክንያት ሰብዓዊ አገልግሎቱን ለሚፈልጉ ወገኖች ለመድረስ ፈተና እየሆነበት እንደመጣ አሳውቋል።

ጥቃት ሚፈፅሙ የትኛውም ተፋላሚ ኃይሎች ድርጊቱ ኢትዮጵያ የፈረመችውን ዓለም አቀፍ የጄኔቫ ሥምምነቶችን የሚፃረር እና ከማኅበሩ ዓላማ ውጪ መሆኑን ተረድተው ከመሰል ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እንዲሁም ማኅበረሰቡ ድርጊቶቹን #እንዲያወግዝ ተማፅኗል።

@tikvahethiopia