#ZemenBank
ዘመን ባንክ አዲስ ያስገነባውን ዋና መስሪያ ቤት በመጪው ቅዳሜ እንደሚያስመርቅ አስታወቀ።
ከተመሰረተ 15 ዓመታትን ሊደፍን ጥቂት የቀረው ዘመን ባንክ አምስት ዓመታት የፈጀውንና በአዲስ አበባ ሰንጋተራ አከባቢ ያስገመባውን ህንፃ ቅዳሜ ያስመርቃል።
ስለ ህንፃው ፦
- በ2300 ካሬ ሜትር ላይ የተገነባ ነው።
- 1.2 ቢሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል
- ምድር ቤቱን ጨምሮ ሕንጻው 36 ወለሎች አሉት።
- በተለየ መልኩ የተገነባ ገንዘብ እንዲሁም የከበሩ ማዕድናት የሚቀመጡበት ወለል ጨምሮ በርካታ ዘመናዊ የግንባታ ጥበቦችን ተጠቅሟል።
- ከምድር ቤቱ በተጨማሪም እስከ 5 ፎቅ ድረስ 200 የሚሆኑ መኪና ማቆም የሚችል ፖርኪንግ አለው።
ዘመን የባንክ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በ2008 በአንድ ማዕከል፣ በ 87.2 ሚሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል የተመሰረተ ሲሆን አሁን ላይ ቅርንጫፎቹን ወደ 100 ከፍ ማድረጉን ገልጿል።
በ2021/22 በጀት ዓመት 2.1 ቢሊዮን ያልተጣራ ትርፍ ማግኘቱን የገለጸው ባንኩ አጠቃላይ ካፒታሉ 6 ቢሊዮን ብር በላይ እንዲሁም የተከፈለ ካፒታሉ 4.7 ቢሊዮን ብር መሆኑን አስታውቋል።
በተጨማሪም የባንኩ ጠቅላላ ሀብት 40 ቢሊየን መድረሱን ገልጾ ለደንበኞቹም የ30 ቢሊየን ብር ብድር ማቅረቡን አስታውቋል።
ከሚቀጥለው በጀት ዓመት ጀምሮ የባንኩን ካፒታል 15 ቢሊዮን ለማሳደግ ማቀዱን ያሳወቀ ሲሆን የዚህ ዓመት ትርፉ 3 ቢሊየን ይሆናል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።
@tikvahethiopia