TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.91K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጋምቤላ

በጋምቤላ ክልል በተፈጠረ የእርስ በእርስ ግጭት 9 ሰዎች ሲገደሉ ፤ 17 ሰዎች ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ክልሉ አሳወቀ።

ከሰሞኑን በጋምቤላ ክልል በኢታንግ ልዩ ወረዳና በጋምቤላ ከተማ የፀጥታ ችግር ተከስቶ እንደነበር የክልሉ ፕሬዜዳንት  ዛሬ በሰጡት መግለጫ ገልፀዋል።

የክልሉ ፕሬዜዳንት አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በሰጡት መግለጫ ፤ " በክልሉ በኢታንግ ልዩ ወረዳና በጋምቤላ ከተማ ሰሞኑን ተከስቶ የነበረዉን የፀጥታ ችግር በክልሉና በፌዴራል የፀጥታ አካላት ቅንጅታዊ ስራ በቁጥጥር ስር ለማዋል ተችሏል " ብለዋል።

በኢታንግ ልዩ ወረዳ በፒኝዋ እና ሌር ቀበሌዎች በሚኖሩ ግለሰቦች መካከል የተነሳዉ አለመግባባበት ወደ ግጭት ማምራቱን የገለፁት የክልሉ ፕሬዜዳንት በዚህም በወረዳውና በጋምቤላ ከተማ አለመረጋጋት ተፈጥሮ እንደነበር አስታውሰዋል።

በኢታንግ ልዩ ወረዳ እና በጋምቤላ ከተማ በተከሰተው የእርስ በርስ ግጭት የዘጠኝ (9) ሰው ህይወት ሲያልፍ 17 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት ከፌዴራልና ከክልል የፀጥታ አካላት አስፈላጊው ኃይል ተጨምሮ የማረጋጋት ስራ መከናወኑን አመልክተዋል።

ፕሬዜዳንቱ ፤ " ለዘመናት በአብሮነትና ወንድማማችነት ተከባብሮ የኖረውን ህዝብ ለማለያየት የሚሞክሩ አካላት አሉ " ያሉ ሲሆን " በህብረተሰቡና በፀጥታ ሀይሎች ጥረት ሴራቸው ሳይሳካ ቀርቷል " ብለዋል።

የክልሉ ፕሬዜዳንት ማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጭ የሀሰት መረጃዎችን የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አስጠንቅቀው አሻፈረኝ ባሉት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia
ትላንት ሌሊት 10:30 ቡድናቸውን ለመደገፍ ወደ ሀዋሳ ሊያቀኑ የነበሩ የባህር ዳር ከተማ ደጋፊዎች ላይ በደረሰ የቦንብ ፍንዳታ ጉዳት መድረሱ ታውቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከክለቡ የደጋፍ ማህበር ለማጣራት እንደሞከረው ደጋፊዎቹ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ለሚያደርጉት ተጠባቂ ጨዋታ ቡድናቸውን ለማበረታት በሚያደርጉት ጉዞ ሙሉአለም አዳራሽ አካባቢ ላይ ጉዳቱ እንደደረሰባቸው ለማወቅ ችለናል።

ሁለት ደጋፊዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ሲደረስ አንድ ደጋፊ የጭንቅላት ጉዳት ደርሶባት በአሁን ሰዓት በፅኑ ህሙማን መከታተያ ( ICU ) ውስጥ እንደምትገኝ ተገልፆልናል።

ጉዳት የደረሰባቸው ደጋፊዎች በባህርዳር ፈለገ ህይወት አጠቃላይ ሆስፒታል የህክምና ክትትል እያደረጉ ይገኛሉ።

በቦንብ ጥቃቱ የሞተ ሰው ባይኖርም ከ20 በላይ በሚሆኑ ደጋፊዎች ላይ ጉዳት ደርሷል።

@tikvahethiopia @tikvahethsport
የባህር ዳር አስተዳደር ምን አለ ?

የባህር ዳር ከተማ ከንቲባና የክለቡ የቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ በትላንትናው ለሊት ስለተፈፀመው የቦንብ ጥቃት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ከንቲባው ፤ " ክለባችን ባህር ዳር ከነማ በዘንድሮው የቤትኪንግ ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመርቂ ውጤት በማስመዝገብ ዋንጫ ለማንሳት እየተፎካከረ ይገኛል " ብለዋል።

ይህንን መሠረት በማድረግ ግንቦት 18 ቀን 2015 ዓ.ም የፕሪሚየር ሊጉ መሪ ከሆነው ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ጋር ለሚያደርገው ወሳኝ ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች በርካታ ኪሎ ሜትሮችን አቆራርጠው በአካል ተገኝተው ለመደገፍ ጉዞ ወደ ሀዋሳ ለማድረግ ዝግጅት ጨርሠው ወደ ተዘጋጀላቸው አውቶብስ እየገቡ ባሉበት ሁኔታ በተወረወረባቸው ቦንብ 23 የክለቡ ደጋፊዎች ቀላል እና ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ገልጸዋል።

ከንቲባው ቦንቡን የወረወሩት " ለጊዜው ማንነታቸው ያልታወቁ አካላት " ናቸው ብለዋል።

ቀላልና ከባድ ጉዳት ያደረሰባቸው የክለቡ ደጋፊዎች የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ከንቲባው ገልጸዋል።

ከንቲባው ፤ " ከጊዜ ወደ ጊዜ በከተማችን ላይ እየተፈፀመ ያለው የቦንብ ጥቃትና ግድያ የከተማችንን ነዋሪ በሠላም ወጥቶና ተንቀሳቅሶ የመስራት ፍላጎት የሚገድብ፣ የከተማችንን እድገትና ልማት የሚጎዳ፣ ብሎም የከተማችንን ገፅታ የሚያበላሽ የፀረ ሠላም እንቅስቃሴ በመሆኑ መላ ህብረተሠባችን ሊያወግዘው ይገባል። " ብለዋል።

" ከዚህ ባለፈ ህብረተሠቡ የፀጥታው ባለቤት በመሆን ከፀጥታ ኃይሉ ጎን በመሠለፍ የከተማውን ሠላም የሚያውኩ አካላትን በመለየት ለህግ እንዲቀርቡ ማድረግ ይገባል " ሲሉ አክለዋል።

ከንቲባው የከተማው የፀጥታ አካላት የከተማውን ሠላምና ደህንነት ለማረጋገጥ እየሠሩ እንደሚገኙ የገለፁ ሲሆን " አሁንም እንደከዚህ ቀደሙ እንዚህን ወንጀል ፈፃሚወች ተከታትለው ለህግ የሚያቀርቡ ይሆናል " ብለዋል።

@tikvahethiopia
የስዕል ተስዕጦ ላላቸው የቀረበ ዕድል!

ሪድም ዘጀኔሬሽን USAID ጋር በመተባበር ዕድሜያቸው ከ18 -29 ለሆኑ ወጣቶች በቡድን ሆነው የሚሳተፉበት የስዕል ውድድር አዘጋጅቷል። ውድድሩ በሁሉንም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የሚገኙ 80 የሚሆኑ ወጣቶች ክህሎታቸውን ተጠቅመው ስለሰላም በጋራ እንዲሰሩ የሚያግዝና መልዕክት የሚያስተላልፉበት ነው።

ምዝገባው ከዛሬ ግንቦት 14 እስከ18 ድረስ የሚቆይ ሲሆን ተሳታፊዎች በሥራ ሰዓት በሪድም ቢሮ በአካል ወይም በኦላይን https://forms.gle/rQr7ojZ8jXkCrkA18 ላይ መመዝገብ ይችላሉ።

አንደኛ ለሚወጣው የሥዕል ሥራ የ60,000 ብር ሽልማት የተዘጋጀ ሲሆን፤ ሁለተኛ ለወጣው አሸናፊ ደግሞ የ40,000 ብር ሽልማት ያስገኛል። በማኅበራዊ ሚዲያ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ላገኘው የሥዕል ሥራ ደግሞ የ10,000 ብር ሽልማት ተዘጋጅቷል።

ስለውድድሩ ዝርዝር መረጃና ለመሳተፍ ስለሚያስፈልጉ መስፈርቶች በቀጣዩ ሊንክ ይጠቀሙ https://telegra.ph/Call-for-Applicants-05-22

ለተጨማሪ መረጃ  0930098219 / [email protected] ላይ ይጠይቁ።
#ZemenBank

ዘመን ባንክ አዲስ ያስገነባውን ዋና መስሪያ ቤት በመጪው ቅዳሜ እንደሚያስመርቅ አስታወቀ።

ከተመሰረተ 15 ዓመታትን ሊደፍን ጥቂት የቀረው ዘመን ባንክ አምስት ዓመታት የፈጀውንና በአዲስ አበባ ሰንጋተራ አከባቢ ያስገመባውን ህንፃ ቅዳሜ ያስመርቃል።

ስለ ህንፃው ፦

- በ2300 ካሬ ሜትር ላይ የተገነባ ነው።

- 1.2 ቢሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል

- ምድር ቤቱን ጨምሮ ሕንጻው 36 ወለሎች አሉት።

- በተለየ መልኩ የተገነባ ገንዘብ እንዲሁም የከበሩ ማዕድናት የሚቀመጡበት ወለል ጨምሮ በርካታ ዘመናዊ የግንባታ ጥበቦችን ተጠቅሟል።

- ከምድር ቤቱ በተጨማሪም እስከ 5 ፎቅ ድረስ 200 የሚሆኑ መኪና ማቆም የሚችል ፖርኪንግ አለው።

ዘመን የባንክ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በ2008 በአንድ ማዕከል፣ በ 87.2 ሚሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል የተመሰረተ ሲሆን አሁን ላይ ቅርንጫፎቹን ወደ 100 ከፍ ማድረጉን ገልጿል።

በ2021/22 በጀት ዓመት 2.1 ቢሊዮን ያልተጣራ ትርፍ ማግኘቱን የገለጸው ባንኩ አጠቃላይ ካፒታሉ 6 ቢሊዮን ብር በላይ እንዲሁም የተከፈለ ካፒታሉ 4.7 ቢሊዮን ብር መሆኑን አስታውቋል።

በተጨማሪም የባንኩ ጠቅላላ ሀብት 40 ቢሊየን መድረሱን ገልጾ ለደንበኞቹም የ30 ቢሊየን ብር ብድር ማቅረቡን አስታውቋል።

ከሚቀጥለው በጀት ዓመት ጀምሮ የባንኩን ካፒታል 15 ቢሊዮን ለማሳደግ ማቀዱን ያሳወቀ ሲሆን የዚህ ዓመት ትርፉ 3 ቢሊየን ይሆናል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።

@tikvahethiopia
#ኢዜማ

ከኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ  / ኢዜማ  መስራቾች መካከል የሆኑት የፓርቲው አባላት በገዛ ፍቃዳቸው ከፓርቲው አባልነት ለቀቁ።

ፓርቲውን በገዛ ፍቃዳቸው የለቀቁት ፦
- አቶ የሽዋስ አሰፋ
- ወ/ሮ ናንሲ ውድነህ
- አቶ ሀብታሙ ኪታባ
- አቶ የጁአልጋው ጀመረ
- አቶ ተክሌ በቀለ
- አቶ ኑሪ ሙደሲር               
- አቶ ዳንኤል ሺበሺ ናቸው።

ለምን ከኢዜማ ለቀቁ ?

በመሠረቱት ኢዜማ ፓርቲ ውስጥ በአንዳንዶች መሀል መጠነኛ የአቋም ልዩነት እንደነበር ገልጸዋል።

ይህ ልዩነት ግን በሂደት በውይይት እና በስራ እየጠበበ እና እየተስተካከለ ይሄዳል በሚል እሳቤ አብረው መጓዣቸውን አመልክተዋል።

የኃላ ኃላ ግን የአቋም ልዩነቱ ላይ የአካሄድም ልዩነት ተጨምሮበት ትግሉ መስመር ስቶ ከፍተኛ በሆነ በውስጠ ፓርቲ ትግል  ተጠልፈው ለመዎየት መገደዳቸውን ገልጸዋል።

" የኢትዮጵያ አሁን ሕዝብ በታሪኩ ገጥሞት የማያውቅ እዚህ መከራ ውስጥ ከመግባቱ በፊት መንገዳችንን እንድናስተካክል በፓርቲው ውስጥም በብዙ ታግለናል፡፡  " ያሉት እኚህ የፓርቲው አባላት " ስህተቶች ይታረሙ ይሆናል በማለት የትግሉን መድረክ ለማስፋት ብንሞክርም በተለያዩ ውስጣዊ እና ውጫዊ ምክንያቶች ማሳካት አልተቻለም " ብለዋል።

ኢዜማን ጠግኖ ለማዳን ያደረግነው ትግልም ከንቱ ቀርቷል ሲሉ አሳውቀዋል።

የኢዜማ ከፍተኛ አመራር ሀገርን ለመታደግ ሕዝብንና ፓርቲዎችን አስተባብሮ ከማታገል ይልቅ አገዛዙ እየፈፀመ ላለው ሀገር አቀፍ ግፍ ድጋፍ እየሰጠ ይገኛል ሲሉ ወቅሰዋል።

" ለዚህ ሥርዓት ምሶሶ እና ማገር ሆኖ በማገልገል የአንድነት ኃይሉን አቅም አላባ በማድረግ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ለመሆኑ የአባላት ብቻ ሳይሆን የሕዝብም ቅሬታ ሆኖ በመሰማት ላይ ይገኛል " ያሉት የፓርቲው አባላት " ይህም ኢዜማ ከቆመላቸው መሠረታዊ አላማዎች፤ መርሆች እና እሴቶች በመውጣት የገዢውን ቡድን እሴቶች እና አላማዎች እያራመደ እንደሆነ ግልፅ ሆኗል " ብለዋል።

በዚህም ፤ ኢዜማ የተለየ ቁመና የሌለውና ተክለ ሰውነቱም ሆነ ህልውናው በየዕለቱ ለትውልድ የሚተላለፍ ጠባሳዎችን ጥሎ ከሚያልፈው አገዛዝ የተለየ እንዳይመስል ተደርጎ እየተሠራ እንደነበር ግልጽ ሆኗል ሲሉ አሳውቀዋል።

በዚህና በሌሎች በርካታ ምክንያቶች ፓርቲውን ማዳን በማይቻልበት ሁኔታ ላይ በመደረሱ ፤ እንዲሁም " አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በሂደት በምንገልጻቸው በርካታ ምክንያቶች " ፓርቲውን ወደ ሃዲዱ ለመመለስ ያደረግነው ትግል ግቡን ስላልመታ ራሳችንን ከኢዜማ አባልነት አግልለናል ብለዋል።

(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል)

NB. ከዚህ ቀደም ጉምቱው ፖለቲከኛ እና ከኢዜማ መስራቾች አንዱ አቶ አንዱዓለም አራጌ ኢዜማን በገዛ ፍቃዳቸው መልቀቃቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
ፕራይም ቴሌቪዥን የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጠው፤ ለምን ?

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለ " ፕራይም ቴሌቪዥን " የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ መስጠቱን አሳውቋል።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለምንድነው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የሰጠው ?

" የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ እና በሌሎች ተያያዥ ሕጎችም፤ የመገናኛ ብዙኃን በተለይ የጋራ እሴቶችን የሚንዱ ፤ አለመቻቻል እንዲፈጠር ምክንያት የሚሆኑ እና ዜጎችን ለግጭት ሊያነሳሱ የሚችሉ ስርጭቶችን ከማስተላለፍ እንዲታቀቡ ይደነግጋሉ " ያለው ባለስልጣን መ/ቤቱ ፤ " ፕራይም ቴሌቪዥን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እነዚህን ሕግጋት የሚጥሱ ዜናዎችንና ፕሮግራሞችን ሲያሰራጭ መቆየቱን በክትትል ሥራችን አረጋግጠናል " ሲል ገልጿል።

ፕራይም ቴሌቪዥ የዜጎችን አብሮነት የሚጎዳ ይልቁንም ከፍተኛ ጥንቃቄ በሚሹ #ሃይማኖታዊ ጉዳዮች ዙሪያ አሉታዊና ሕግን የሚተላለፉ ይዘቶችን በማሰራጨት ዜጎችን ላልተገባ ውጥረትና አደጋ አስተዋፅኦ የማድረግ አዝማሚያ ታይቶበታል ብሏል።

ፕራይም ቴሌቪዥን እንደ ንግድ ፤ ብሮድካስተር ከገባው የውል ግዴታና ከተቋቋመለት አላማ አንጻር ተገቢ ያልሆነ ተግባር እንደሆነ እንደታመነበት ገልጿል።

በዚህም ምክንያት የቴሌቪዥን ጣቢያው ከዚህ ድርጊቱ እንዲታረም የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጠው አሳውቋል።

@tikvahethiopia
" ... መሬት ቆፍረው ሊያመልጡ ሙከራ ያደረጉት 10 የከባድ ውንብድና ፍርደኛ ታራሚዎች ናቸው " - ቃሊቲ ማረሚያ ቤት

ከቃሊቲ ማረሚያ መሬት ቆፍረው ሊያመልጡ ነበሩ የተባሉ ታራሚዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተሰምቷል።

ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት  መሬት ቆፍረው ሊያመልጡ ሙከራ ያደረጉር የከባድ ውንብድና ወንጀል ፍርደኛ ታራሚዎች መሆናቸው ተነግሯል።

ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ጥበቃና የደኅንነት አስተባባሪ ኢንስፔክተር ድሪባ ሰንበታ ለኤፍ ቢ ሲ የሰጡት ቃል ፦

" ትናንት ሌሊት 10 ሰዓት ከ30 ላይ መሬት ቆፍረው ሊያመልጡ ሙከራ ያደረጉ 10 የከባድ ውንብድና ፍርደኛ ታራሚዎች ላይ ማረሚያ ቤቱ ባደረገው ክትትል በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ለማምለጥ ሙከራ ካደረጉ ፍርደኞች መካከል ከዚህ በፊት #አምልጦ ከጣልያን ሀገር በኢንተርፖል ተይዞ የመጣ ታራሚ ይገኝበታል።

ሌሎችም በተደጋጋሚ ከጤና ጣቢያ ፣ከመኪና ላይ ጭምር ለማምለጥ ሞክረው የተያዙ ፍርደኞች አሉ።

ማረሚያ ቤቱ  ዛሬ በተለያዩ ፍርድ ቤቶች ቀጠሮ የነበራቸው ታራሚዎችን አጅቦ በማቅረብ መደበኛ ስራውን ሲሰራ ውሏል።

ታራሚዎቹ  ከመሰል ድርጊት እንዲቆጠቡ ተገቢ የሆነ  የክትትልና የቁጥጥር ስራው ይቀጥላል። "

Credit : #FBC

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

ባላችሁበት ሆናችሁ የአፖሎ ሞባይል መተግበሪያን በመጠቀም ፊታችሁንና መታወቅያችሁን ስካን በማድረግ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች በማስገባት 5 ደቂቃ ባልፈጀ ጊዜ ውስጥ የአቢሲንያ ባንክ አካውንት መክፈት ትችላላችሁ።

መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።
https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo

#Apollodigitalproduct #AbyssiniaDigital #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
#AddisAbaba

ሰሞኑ በአዲስ አበባ ከተማ የንግድ ቤቶችን የማፍረስ ስራ እየተከናወነ ሲሆን በዚህም " የንግድ ቤቶቻችን ያላግባብ ፈርሰዋል  ንብረቶቻችን በአጠቃላይ ተወስደዋል " ያሉ የአካል ጉዳተኞች ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መልዕክታቸውን የላኩ የቤተሰቡ አባላት " ይሄንን ግፍ እና በደል አቤት ለማለት ቅሬታችንን ለማቅረብ በሄድንባቸው የመንግሥት ተቋማት በጸጥታ አካላት ማዋከብ እና እንግልት እየደረሰብን ነው። " ብለዋል።

እንደዜጋ ተመልክቶ ምላሽ ሊሰጠን ፈቃደኛ የሆነ የመንግስት አካል የለም ሲሉ አሳውቀዋል።

" እንለምን አይደለም ያልነው እንስራ እንጂ ፤ እራሳችንን ችለን መንግስትን እናግዝ እንጂ መንግስትን አግዙን እርዱን አላልንም " የሚሉት እኚህ ወገኖች " ለራሳችን እና ለቤተሰባችን ጉሮሮ መሸፈኛ ከዛም አልፎ ሌሎች የስራ ዕድል የፈጠርንበት ረጅም የድካም አመታት አሳልፈን በአካል በጉዳተኝነታችን የሚደርስብንን ተፅዕኖ ተቋቁመን የገነባነውን ነገር ነው እንደቀልድ በሌሊት መተው አፍርሰውብናል " ሲሉ አስረድተዋል።

" እየተከናወነ ያለው የንግድ ቤቶች ፈረሳ ሕጋዊ ሥርዓትን ባልተከተለ መልኩ ነው " የሚሉት አካል ጉዳተኞቹ  " በተለይ አገራችን ከዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች የመብት ኮንቬንሽን ከፈረመችው ስምምነት ውጭ  ነው " ብለዋል።

ይህም አካል ጉዳተኞችን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ሥነ-ልቦናዊ ቀውስ ውስጥ የከተተ መሆኑን ከግንዛቤ በማስገባት በአፋጣኝ ተገቢውን ምላሽ ከሚመለከተው አካል ሊሰጠን ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በተጨማሪ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት መልዕክት እንደ ወንጀለኛ አካል ጉዳተኞችን በየመስሪያ ቤቱ እየተከታተሉ የሚያሸማቅቁ የሚያንገላቱ የሕግ አካላት መኖራቸውን በመጠቆም " በሀገራችን የሕግ የበላይነት ካለ በህግ አምላክ መብታችንን አስከብሩልን ለማለት እንወዳለን " ብለዋል።

ለመሆኑ የንግድ ቤቶች የፈረሱት የት ነው ?

" ሰላም ለሁሉም የአካል ጉዳተኞች ንግድ አክስዮን ማኅበር " በአዲስ ከተማ ክ/ ከተማ፣ ወረዳ 8፣ ከረሜላ ፋብሪካ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የ181 አባላቱ የንግድ ቤቶች እንደነበሩ ገልጿል።

ቦታው በ2001 ዓ.ም. አካል ጉዳተኞቹ በጊዜያዊነት እንዲሠሩበት የተሰጣቸው እንደነበር የገለፀው ማህበሩ አባላቱ ላለፉት 15 ዓመታት ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ሲያስተዳድሩበት መኖራቸውን አመልክቷል።

ባለፈው ሳምንት ግን " ከሸራ የተሠሩ ንግድ ቤቶች ይፍረሱ " ተብሏል በሚል፣ የንግድ ቤቶቹ መፍረሳቸውን አሳውቋል።

መንግሥት እና ኢሰመኮ ምን አሉ ?

የአዲስ አበባ ከተማ የሴቶች፣ የሕፃናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ፤ ከንግድ ቤቶች ፈረሳ ጋር በተያያዘ ቀረበ ስለተባለው ቅሬታ የሚያውቀው ነገር እንደሌለ የቢሮው ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ገነት ቅጣው ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በበኩሉ ፤ ከንግድ ቤቶች ፈረሳ ጋር በተያያዘ ከ160 በላይ የሚሆኑ አካል ጉዳተኞች የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ቅሬታ እንዳቀረቡለት አሳውቋል።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ ከሰሞኑ በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወነ ካለው የንግድ ቤቶች የማፍረስ ሂደት ጋር በተገናኘ የንግድ ቤቶቻቸው ያላግባብ እንዲፈርሱ መደረጉን፣ ንብረታቸው መወሰዱን እንዲሁም ቅሬታቸውን ለማቅረብ በሄዱባቸው የመንግሥት ተቋማት በጸጥታ አካላት ማዋከብ እና እንግልት የደረሰባቸው መሆኑን ለኮሚሽኑ አስረድተዋል። 

ኮሚሽኑ ፤ ቅሬታቸውን ተቀብሎ የክትትል እና የምርመራ ሥራዎችን በአፋጣኝ እንደሚጀምር እና ግኝቶቹንም እንደሚያሳውቅ ገልጿል።

Credit : የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት፣ ኢሰመኮ፣ ቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ
ቪድዮ ፦ በወረቀት

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

አሁንም በተለያየ ምክንያት የጋራ መኖሪያ ቤት ውል ላልተዋዋሉ የቤት ባለዕድለኞች የመጨረሻ እድል ተሰጠ።

የቤት እድለኞችን ውል የማዋዋል ጊዜም እስከ ግንቦት 30/2015 ዓ.ም ድረስ ተራዝሟል።

በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን  ፤ የ14ኛው ዙር የ20/80 እና የ3ኛው ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት እድለኞች ውል የማዋዋል ሂደት እሰከ ግንቦት 30/2015 ባሉ የስራ ቀናት /ቅዳሜ ግማሽ ቀንን ጨምሮ/ መራዘሙን አሳውቋል።

ከጥር 1 ጀምሮ እስከ ግንቦት 7 ተጠቃሚውን ሲያዋውል መቆየቱን ኮርፖሬሽኑ ባወጣው ማስታወቂያ የገለፀ ሲሆን አሁንም በተለያየ ምክንያት ያልተዋዋሉ የጋራ መኖሪያ ቤት እድለኞችን የመጨረሻ እድል ለመስጠት ሲባል እሰከ ግንቦት 30 ማራዘሙን ገልጿል።

በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ያልተዋዋለ የቤት እደለኛ #ቤቱን_እንዳልፈለገው ተቆጥሮ ለኮርፖሬሽኑ ተመላሽ እንደሚሆን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ቀሪዎቹ 3 ሺህ 69 ቤቶች ከሁለት ወር በኃላ ጨረታ ይወጣባቸዋል " - ኮርፖሬሽኑ የ4ኛ ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ንግድ ቤቶች ጨረታ አንደኛ እና ሁለተኛ የወጡ ተጫራቾችን ስም ዝርዝር ይፋ የተደረገ ሲሆን 5 ሺህ 397 ቤቶች ለጨረታ ቀርበው 2 ሺህ 328 ቤቶች አሸናፊ እንደተገኘላቸው ተገልጿል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የ4ኛ ዙር…
#Update

የ40/60 ንግድ ቤቶች ጨረታ ወጣ።

የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ፤ ከተማ አስተዳደሩ በ40/60 ፕሮግራም በተለያዩ ክ/ከተሞች ያስገነባቸፍን 3310 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሕንፃ ላይ የሚገኙ ንግድ ቤቶችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ እንደሚፈልግ አሳውቋል።

ኮርፖሬሽኑ ለሽያጭ ያቀረባቸውን የንግድ ቤቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ተወዳድሮ ለመግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ድርጅት በኮርፖሬሽኑ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከግንቦት 17/2015 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ሰኔ 19/2015 ዓ.ም. ባሉት 28 የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡30 ድረስ ፣ቅዳሜ ግማሽ ቀንን ጨምሮ እስከ 6 ሰዓት ድረስ በአካል በመቅረብና የማይመለስ ብር 400 በመክፈል መግዛት ይችላል ሲል ገልጿል።

የጨረታ ሳጥን ሰኔ 19/2015 ከምሽቱ 11 ሰዓት ተዘግቶ በማግስቱ ሰኔ 20/2015 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራጮች በተገኙበት ይከፈታል ተብሏል።

ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎችን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል።

የጨረታ ሰነድ የት ነው የሚሸጠው ?

- አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ቤቶች ጽ/ቤት 1ኛ ፎቅ

- ሰንጋ ተራ 40/60 ቤቶች ብሎክ 4

- የካ ክ/ከተማ ቤቶች ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ

- አራዳ ክ/ ከተማ ግቢ ውስጥ ግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ቢሮ ቁ/G03

- 40/60 ቦሌ ቡልቡላ ቅርንጫፍ 1 ጽ/ቤት

- 40/60 አያት 49 ማዞርያ ብሎክ 21 ቅርንጫፍ 2 ጽ/ቤት

@tikvahethiopia