TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.89K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በአዲስ አበባ ከተማ የመሬት መንሸራተት ሊያጋጥም ይችላል ተባለ!

በዘንድሮው የክረምት ወራት ከሚያጋጥመው መጠኑ ከፍ ያለ ዝናብ ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ ከነሐሴ 1 እስከ ነሐሴ 30 ድረስ ድንገተኛ መሬት መንሸራተት ያጋጥማል ተብሎ እንደሚጠበቅ የብሔራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ አስታውቋል።

ኤጀንሲው ጨምሮ እንደገለጸው በክረምቱ ወራት ከፍ ያለ የዝናብ መጠን የሚያገኙ የኢትዮጵያ ክፍሎች ውስጥ ድንገተኛ ጎርፍና የመሬት መንሸራተት እንደሚያጋጥማቸው ገልፆ ከእነዚህም ውስጥ መዲናችን አዲስ አበባ በመሬት መንሸራተት ልትመታ እንደምትችል እና ነዋሪው ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርግ አሳስቧል።

መግለጫው ጨምሮ እንደገለፀው፤ ከመዲናዋ አዲስ አበባ በተጨማሪ የዝናብ ስርጭቱ በበርካታ አካባቢዎች ላይ ጎልቶ የሚታይ ሲሆን በውሃው ዘርፍ እንቅስቃሰው ላይ ሊያሳድር የሚችለው አዎንታዊ አስተዋፅዖ ሲሆን፤ በአብዛኛው የክረምት ተጠቃሚ ተፋሰሶች ላይ በመጠንም ሆነ በስርጭት የተሻለ እርጥበት ይኖራቸዋል ተብሎ ይገመታል።

#ኢጀንሲው አያይዞም ከአዲስ አበባ #በተጨማሪ ከፍተኛ የዝናብ መጠን ያገኛሉ የተባሉትን አካባቢዎችንም ይፋ አድርጓል። ከዚህም ጋር ተያይዞ #በአብዛኛው_የአባይ፣ ተከዜ፣ ባሮ አኮቦ፣ የኦሞ ጊቤ የላይኛውና የመካከለኛው አዋሽ፣ ስምጥ ሸለቆ፣ ዋቢ ሸበሌ እና የላይኛው ገና ሌዳዋ ተፋሰሶች ላይ ከከፍተኛ እርጥበት እስከ እርጥበታማ የዝናብ መጠን ይኖራቸዋል ሲል አስታውቋል።

#አዲስ_ማለዳ_ጋዜጣ

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/AA-08-12-4
«ቀጣይ ትውልድ»

ትዴት የአማራ እና ትግራይ ወጣቶች የወዳጅነት መድረክ ሊያዘጋጅ ነው!

የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) «ቀጣይ ትውልድ» በሚል መሪ ቃል የአማራና ትግራይ ክልል ወጣቶች የሚሳተፉበት የወዳጅነት መድረክ በባህር ዳር፣ ቆቦ፣ አላማጣ፣ አዲስ አበባ እና መቀሌ ከተሞች በመስከረም 2012 መካሄድ እንደሚጀመር አስታወቀ።

የትዴት ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሙሉ ብርሃን ኃይለ፣ ዝግጅቱን በቀጣዩ መስከረም ወር ላይ ለመጀመር ፈቃደኛ ከሆኑ ግለሰቦች ገንዘብ ማሰባሰብ መጀመራቸውን ለአዲስ ማለዳ ገልጸው፣ የትዴት ድጋፍ እንዳለ ሆኖ ከአማራ ክልል መንግስትም የገንዘብ ድጋፍ መጠየቃቸውን አውስተዋል።

የፓርቲው የትዴት ምክትል ሊቀመንበር ግደይ ዘርዐጽዮን ለአዲስ ማለዳ እንዳስታወቁት፣ በሁለቱ ክልሎች አመራሮች መካከል የሚታየው ሽኩቻ ወደ ወጣቱ አምርቶ ሌላ ችግር ከማምጣቱ በፊት፣ የሁለቱ ክልል ወጣቶች መክረውና ተወያይተው ችግሮቻቸውን መፍታት ይችላሉ፣ በሚል ዝግጅቱን ለማከናወን መታሰቡን ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። ‹‹ፓርቲው መድረኩን ከማዘጋጀት ባለፈ ሌላ ሚና አይኖረውም፣ ከማንም ጣልቃ ገብነት ነጻ በሆነ መልኩ በሁለቱ ክልል ወጣቶች ብቻ የሚከናወን ይሆናል። ያለአግባብ የሆኑ እንቅስቃሴዎች ተቀርፈው ታሪካዊ ወዳጅነት እንዲፈጠርና አብሮ የመሥራት ተሞክሮ እንዲኖርም ለማድረግ ያግዛል›› ሲሉ ተናግረዋል።

#አዲስ_ማለዳ_ጋዜጣ

ይህን ተጭነው ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-27-6
#ADDISABEBA

‘የአልሸባብ አባል’ በ10 ቦታዎች የሽብር ጥቃት ሊፈፅሙ ነበር በሚል ተከሰሱ!

•የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና አዲስ አበባ ስቴዲየም ከኢላማዎቹ መካከል ነበሩ ተብሏል

ከስድስት ወራት በፊት በብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት ክትትል #የአልቃይዳ የምስራቅ አፍሪቃ ክንፍ ብሎ ራሱን የሚጠራውን የአልሸባብን ዓላማ ለማሳካት በአዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ 10 ቦታዎች የሽብር ጥቃት ለመፈፀም ዝግጀት ሲያደርጉ ነበር የተባሉት አዲሃመን አብዶ ክስ ተመሰረተባቸው።

ግለሰቡ በኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ታንዛኒያ እና ኢትዮጵያ ላይ በተመሳሳይ ወቅት በተነጣጠሩ ጥቃቶች ላይ የአዲስ አበባ ጥቃት ለማቀናጀት የቦታ መረጣ እንዲያከናውኑ ተመልምለው ነበር ሲል ዓቃቤ ህግ ክሱን መስርቷል። ግለሰቡ ከትላልቅ ህንጻዎች ላይ በመሆን የቦሌ አየር መንገድ ማረፊያን በምስል አስቀርተዋል ሲል ያተተው ክሱ ሀያት ሬጀንሲ፣ ስካይ ላይት ሆቴል፣ በመገንባት ላይ ያለውን የንግድ ባንክ ህንፃ አና ሌሎችም ሰዎች በብዛት የሚሰበሰቡባቸውን ቦታዎች በምስል አስቀርተዋልም ብሏል።

ሁለተኛ ተከሳሽም ለዋና ወንጀል አድራጊ ሀሰተኛ ሰነዶችን በማዘጋጀት በሽብር አዋጁ መሰረት የሽብር ወንጀልን በመርዳት ተጠርጥረው ክስ ተመስርቶባቸዋል። ለዋና ወንጀል አድራጊ የትምህርት ማስረጃ ሰነዶችን በጅግጅጋ ከተማ ተምረው እንዳጠናቀቁ በማስመሰል አዘጋጅተዋል፤ በዚህም ሊፈፀም ለታቀደው ወንጀል እገዛ አድርገዋል ሲል ዐቃቤ ህግ በአባሪነት ከሷቸዋል።

የሶማሊያ ዜግነት ያላቸው አንደኛ ተከሳሽ የጅቡቲን ሕገወጥ የጉዞ ሰነድ ፓስፖርት ይዘው በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ወደ ቱርክ ለመብረር ቪዛ በማግኘት በቀጣይ እቅድ እንደነበራቸው ለማወቅ ተችሏል።

https://telegra.ph/E-09-16

ምንጭ፦#አዲስ_ማለዳ_ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አብዱልዋሀብ መሐድ ከአሶሳ ማረሚያ ቤት አመለጠ።

የቤንሻጉል ሕዝቦች ነጻ አውጭ ንቅናቄ (ቤሕነን) የቀድሞ ሠራዊት መሪ አብዱልዋሀብ መሐድ ታሥሮ ከነበረበት አሶሳ ዞን ማረሚያ ቤት ማምለጡን አንድ ስማቸው ያልተገለፀ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ እንደነገሩት አዲስ ማለዳ ጋዜጣ አስነበበ።

የ9 ዓመት ዕሥር የተፈረደበት አብዱልዋሀብ ያመለጠው ታኅሣሥ 18/2014 መሆኑ ተገልጿል።

ግለሰቡ ከዚህ በፊትም እንዲሁ 2001 ዓ/ም የዕድሜ ልክ ዕሥራት ተፈርዶበት የነበረ ሲሆን፣ 2002 ላይ ከማረሚያ ቤት አምልጦ ወደ ኤርትራ በመግባት ኢትዮጵያን ከሚወጉ ኃይሎች ጋር ሲሠራ እንደነበር ተገልጿል።

ከዚያ በመቀጠል 2009 ዓ/ም ላይ የፌዴራሉ እና የክልሉ መንግሥት ግለሰቡ ከሚመራው ቡድን ጋር ባደረጉት የሠላም ድርድር ተስማምቶ ወደ ኢትዮጵያ በመግባት ሠላማዊ ኑሮ መምራት ጀምሮ ነበር።

ግለሰቡ ይመራቸው የነበሩ ታጣቂዎች ከመንግሥት 20 ሚሊዮን ብር መቋቋሚያ ተቀብለው ተበታትነው ከቆዩ በኋላ፣ ሰኔ 2010 ዳግም አሶሳ ላይ ጥቃት በፈጸሙበት ወቅት መሪው ራሱ ተሳታፊ በመሆን የሰው ነፍስ አጥፍቷል ተብሏል።

በዚህም ግለሰቡ ተከሶ ሲከራከር ከቆዬ በኋላ፣ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የ16 ዓመት ከስድስት ወር ዕሥራት ተፈርዶበት እንደነበር ታወቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ፍርደኛው ለፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ይግባኝ አቅርቦ ቅጣቱ ወደ ዘጠኝ ዓመት ዕሥር ዝቅ ተደርጎለት የነበረ ቢሆንም፣ ዐቃቤ ሕግ በቅጣት ውሳኔው ባለመስማማቱ በፍርድ ክርክር ሒደት ላይ ሳለ ግለሰቡ አምልጦ መጥፋቱ ነው የተነገረው።

ግለሰቡ ፍርድ የተሠጠው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተዘዋዋሪ ችሎት ሆኖ ለቤተሰብ እንዲቀርብ በሚል ወደ አዲስ አበባ ሌሎች ፌዴራል ማ/ ቤቶች እንዳልተወሠደ ነው የተጠቆመው።

ታሳሪው በፌዴራልና በክልሉ መንግሥት በጥብቅ ሲፈለግ እና ከፍተኛ ክትትል ሲደረግብት የነበረ ከመሆኑም አንጻር፣ በርካታ ዕሥረኞች ካሉበት ማረሚያ ቤት ቀን ላይ በግልጽ ለኹለተኛ ጊዜ ማምለጡ፣ ሴራ ሳይኖርበት እንዳልቀረ ያመላክታል ሲሉ ስማቸው ያልተሀለፀድ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊው ጠቁመዋል።

በአሁን ሰዓት የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፀጥታ ኃይሎች እሥረኛውን እየፈለጉት ቢሆንም ቦታው ለሱዳን ካለው ቅርበት እንዲሁም ሰውዬው መውጫ እና መግቢያውን የሚያውቅ፣ በትግልም ለ20 ዓመት ገደማ የቆዬበት በመሆኑ በቀላሉ ሊገኝ ይችላል ተብሎ እንደማይታሰብ ነው የሥራ ኃላፊው የገለጹት።

ግለሰቡ ሱዳን ከገባ በኋላም እንደከዚህ ቀደሙ ወጣቶችን መልምሎ በማሠልጠን፣ በመተከልና አሶሳ ዞኖች ውስጥ በሚገኙ ወረዳዎች ላይ ተመሳሳይ የሆነ የሽብር ድርጊቱን ሊቀጥል እንደሚችል ነው የተመላከተው።

የአብዱልዋህብ አጋር የነበሩ ሰዎች ሱዳን ውስጥ በርካታ ወጣቶችን በማሰልጠን ክልሉ ውስጥ ረብሻ ሲፈጥሩ ቆይተዋል ያሉት ኃላፊ ፥ በዚህ የሰውዬው ከእስር ማምለጥ ለአካባቢው ሠላምና ደኅንነት አደገኛ ነው ብለውታል።

የአሶሳ ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ሐሩን አብዱራማን ፥ አብዱልዋህብ ከተፈረደበት ከስድስት ወር በኋላ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የተጣለበት ቅጣት ላይ ጥያቄ ማቅረቡ ስሜታዊ እንዳደረገው እና ለልማት ሥራ በሚል ከማረሚያ ቤት ሲወጣ በነበረበት ወቅት ላይ እንዳመለጠ ለጋዜጣው ተናግረዋል።

ከአብዱልዋህብ መሐድ ውጭ ከማረሚያ ቤቱ ያመለጠ ሌላ ታራሚ እንደሌለ የተናግሩት ኃላፊው ፣ እሱም በቅርብ ቀን በቁጥጥር ሥር ይውላል የሚል ግምት እንዳለቸው ተናገረዋል።

ግለሰቡ ወደ ሱዳን እንዳይወጣ ሁሉም ቦታዎች በፀጥታ ኃይሎች መዘጋታቸውን ገልጸው፣ እሥረኛው ወደ ሱዳን ከመሸሽ ይልቅ ተጸጽቶ ተመልሶ ይመጣል የሚል ዕምነት እንዳለቸው ተናግረዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Addis-Maleda-01-01

ምንጭ፦ #አዲስ_ማለዳ_ጋዜጣ