ተጠንቅቃችሁ አሽከርክሩ ⚠️
በዚህ ሳምንት ፤ በሲዳማ ክልል በበንሳ ወረዳ ፤ በንሳ ዋሬ ቀበሌ ልዩ ቦታው " ሬዎ " በሚባል ቦታ በሁለት #ሞተር_ሳይክሎች ግጭት በተከሰተ የሞተር አደጋ የ3 ሰው ህይወት #ወዲያውኑ ሲያልፍ አንድ ሰው ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል።
ከመጠን በላይ ፍጥነትና ከአቅም በላይ መጫን የፈጠረዉ አደጋ መሆኑ የተነገረለት ይህ አሰቃቂ አደጋ ለማህበረሰቡ ታላቅ ድንጋጤ የፈጠረና በአንድ ሞተር ላይ ከሁለት በላይ ሰዉ መጫን ለከፋ አደጋ እንደሚያጋልጥ ያሳየ ነዉ ተብሏል።
በጉዳዩ ላይ ለቲክቫህ ኢትዮጽያ አስተያየታቸውን የሰጡት የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር ከበደ ኬኔራ ፤ አደጋዉ በሁለት ሞተር ሳይክሎች ግጭት የተፈጠረ መሆኑን ገልጸዉ የሶስቱ ሰዎች ህይወት ወዲያዉኑ ሲያልፍ አንደኛዉ የከፋ አደጋ ደርሶበት ሆስፒታል እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
ኮማንደሩ ፤ አሁን ላይ የትራፊክ ህግን ሳያከብሩ ማሽከርከር በተለይም በሞተረኞች ላይ የሚታይ ችግር መሆኑን ገልጸዉ ይኸውም ህይወት እየቀጠፈ በመሆኑ የሚመለከታቸዉ አካላት ሁሉ ለትራፊክ አደጋ መቀነስ የሚችሉትን እንዲያደርጉና አሽከርካሪዎችም በተፈቀደዉ ፍጥነት ልክ እንዲያሽከረክሩ ጠይቀዋል።
@tikvahethiopia