TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Joint_Report_of_the_EHRC_OHCHR_Joint_Investigations_on_Human_Rights.pdf
" Genocide ተካሂዷል ለማለት መረጃ የለም" - ሚሼል ባሽሌት

ጄኔቫ ላይ መግለጫ የሰጡት የተመድ (UN ) የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሼል ባሽሌት በተለያየ ደረጃ በሁሉም አካላት የተፈፀሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን መኖራቸውን ገልፀዋል።

ኮሚሽነር ሚሼል ባሽሌት እጅግ በተደጋጋሚ ምርመራው ጭብጦች (Facts) ላይ ተመስርቶ ለማድረግ ጥረት መደረጉን ገልፀዋል።

የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች በሁሉም አካላት ቢፈፀሙም #Genocide ዘር ላይ ያተኮረ የጅምላ ፍጅት (የዘር ማጥፋት ወንጀል) ተካሂዷል ለማለት በቂ መረጃ የለም ብለዋል።

@tikvahethiopia
ከዘር ማጥፋት እልቂት ለማምለጥ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተሸሸጉ 2 ሺህ ቱትሲዎች እንዲገደሉ ትዕዛዝ በመስጠት የተጠረጠረው ግለሰብ ተያዘ።

እ.አ.አ በ1994 በሩዋንዳ በነበረው የዘር ማጥፋት እልቂት፣ ከጥቃት ለማምለጥ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተሸሸጉ ሁለት ሺሕ #ቱትሲዎች እንዲገደሉ ትዕዛዝ አስተላልፏል በሚል የተጠረጠረው ግለሰብ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ መያዙን የሩዋንዳውን የዘር ማጥፋት የሚከታተለው፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጦር ወንጀል ችሎት አስታውቋል።

የቀድሞው የፖሊስ አባል፣ ፉልጌንሴ ካይሼማ፣ ፍ/ቤቱ በይፋ ክሥ ከመሠረተበት ካለፉት 22 ዓመታት ጀምሮ በሽሽት ላይ ነበር።

በተመድ የተቋቋመው ችሎት፣ ሥራውን ለሩዋንዳ በማስረከቡ፣ ካይሼማ፥ ለሩዋንዳ ተላልፎ እንደሚሰጥ የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ካይሼማ ያለበትን ለሚጠቁም፣ የአምስት ሚሊዮን ዶላር ጉርሻ እንደሚሰጥ አስታውቆ ነበር።

ሌላው የዘር ማጥፋቱ ጠንሳሽ የተባለው ፌሊሲን ካቡጋ፣ ከ26 ዓመታት ሽሽት በኋላ ከሦስት ዓመት በፊት በፈረንሳይ ውስጥ መያዙ ይታወቃል።

እ.አ.አ በ1994 በሩዋንዳ፣ በአክራሪ ሁቱዎች በተፈጸመ የዘር ማጥፋት፣ 800ሺሕ የሚሆኑ ቱትሲዎች መገደላቸው ይታወሳል።

#ቪኦኤ #ሩዋንዳ #Genocide

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Genocide

የዘር ፍጅት (ጄኖሳይድ) እንዳይፈጸም በመከላከል እና ሲፈጸምም በማስቆም ላይ የሚሰራው ተቋም " የጄኖሳይድ ዎች " ባደረገው ምርምር የሰው ልጆች ልባቸው ሲደድር የሚጠናወታቸው የዘር ጭፍጨፋ አባዜ 8 ደረጃዎች አሉት።

እነዚህም #በተደራጀ እና #ተቋማዊ በሆነ መንገድ የሚፈጸሙት ናቸው።

ደረጃዎቹ :-

1ኛ. መከፋፈል (Classification) - እኛና እነርሱ ብሎ በመከፋፈል ለየት ይላሉ ተብለው ሚታሰቡትን የኅብረተሰብ ክፍሎች #በቀልድም_ጭምር በማንቋሸሽ በሰዎች መካከል ያለውን ልዩነት አለማክበር።

2ኛ. የሚታይ መገለጫ መስጠት (Symbolization) - ይህ የጥላቻ ግልጽ መገለጫ ሲሆን ይሁዲዎች በናዚ ጀርመን ቢጫ ኮከብ ያለበት ልብስ እንዲለብሱ እንደተደረገው ነው፡፡

3ኛ. ከሰው ክብር ዝቅ ማድረግ (Dehumanization) - ይህ ተግባር ከራስ የተለዩትን ሰብዓዊ ክብርም ሆነ መብት በመንፈግ ይፈጸማል፡፡ በሩዋንዳ አክራሪ ሁቱዎች የቱትሲ ዘውግ ተወላጆችን " #በረሮ#እባብ " ይሏቸው እንደነበረው መሆኑ ነው፡፡ ይህ ሂደት ገዳዮቹ ' እየገደልን ያለነው ሰው አይደለም፤ ታዲያ ድርጊታችን ምኑ ላይ ነው ጥፋትነቱ ? ' እንዲሉ መንገዱን ይጠርግላቸዋል፡፡

4ኛ. ማደራጀት (Organization) - በጥላቻ ላይ የተመሠረቱ መንግሥታት አንድን ሕዝብ የሚያጠፋላቸውን ኃይል #ያሰለጥናሉ፡፡

5ኛ. በተቃራኒ ጎራዎች ማሰለፍ (Polarization) - ሕዝቡ በዘውጉ ከጨፍጫፊው እና ከተጨፍጫፊው ወገን ሚናውን እንዲለይ ይደረጋል፡፡ በብዛት ይህ የሚሆነው በጥላቻ ቡድኖች ውትወታ በመገናኛ ብዙሃን የጥላቻውን መርዝ በመርጨት ነው፡፡ አንዱን ዘውግ ከሌላው ለይቶ በማውጣት " ጠላት ነው " ብሎ ማወጅ ፤ ይህ የገዳዩን ዘውግ አባላት በቀላሉ ለማሳመንና ለህሊናው እንዲቀለው ለማድረግ ጥቅም ላይ የሚውል ነው።

6ኛ. ዝግጅት (Preparation) - ሰለባዎቹ በልዩነቶቻቸው ተለይተው ይፈረጃሉ፡፡ የጭፍጨፋው ንድፍ አውጭዎች ሰዎችን በመኖሪያ አድራሻቸውና በሌሎችም መለያዎች ይፈርጁና ለፍጅት ያዘጋጇቸዋል፡፡

7ኛ. ፍጅት (Extermination) - በታቀደና ሆነ ተብሎ በተመቻቸ ዘመቻ የጥላቻ ቡድኖቹ ሰለባዎቻቸውን ይጨፈጭፋሉ፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በዘር ፍጅት ማንነታቸውን መለየት እስኪከብድ ድረስ ተጨፍጭፈዋል፡፡

8ኛ. ክህደት (Denial) - ግድያውን የፈጸሙትም ሆኑ ቀጣይ ትውልዶች ምንም ዓይነት ጥፋት ያልተፈጸመ በማስመሰል ክህደት ይፈጽማሉ፡፡

ከዚህ የጭፍጨፋ ሂደት እንደምንረዳው የዘር ፍጅት በአንድ ሌሊት ያለምንም ዝግጅት ስለማይፈጸም ራሳችንን ከላይ ከተጠቀሱት በሌላው ላይ ጉዳት ከሚያደርሱ ከስተቶች ፈጽሞ ማራቅና የዕለት ከዕለት ድርጊቶቻችንን መገምገምም ያሰፈልገናል።

እነዚህን የዘር ፍጅት አመላካች ሂደቶች በማናቸውም ደረጃ በእንጭጩ መቅጨት ከተቻለ የከፋ እልቂትን ሙሉ በሙሉ ማስቀረት ይችላል።

ሁቱትሲ
ኢማኪዩሌ ኢሊባጊዛና ስቲቭ ኤርዊን
በመዘምር ግርማ

#Rwanda2024 #Kwibuka #Remembering

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
2016 ዓ/ም

@tikvahethiopia