TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የሶማሊያ ወታደሮች ጉዳይ ?

ወደ #ኤርትራ ለሥልጠና ተልከው የነበሩ በሺዎች ሚቆጠሩ የሶማልያ ወታደሮች በትግራይ ውስጥ በተደረገው ውጊያ ተካፋይ ሆነዋል በሚል፣ በዚህ ሳምንት በወጣው ሪፖርት የተነሳ በሶማልያ መንግሥት ላይ የሚደረገው ግፊት እያየለ መምጣቱ ተነግሯል፡፡

የልጆቻቸው አድራሻ የጠፋባቸው የወታደሮቹ ቤተሰቦች የሱማሊያ ፕሬዚዳንት የሆኑትን መሀመድ አብዱላሂ መሀመድን (ፈርማጆን) ተጠያቂ ያደረጉ ሲሆን እሳቸው ግን ሪፖርቱን አስተባብለዋል፡፡

ቪኦኤ እንደዘገበው የተወካዮቹ ምክር ቤት ኮሚቴ የወታደሮችን አድራሻ በሚመለከት ምርመራ እንዲደረግ ጥያቄ ማቅረባቸው ተነግሯል፡፡

በተባበሩት መንግስታት (UN) የሰአብአዊ መብት ጉባኤ በዚህ ሳምንት የወጣው ዘገባ እንዳመለከተው “ለሥልጠና ወደ ኤርትራ ተልከው የነበሩ ወታደሮች በኢትዮጵያው የትግራይ ውጊያ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡”

የሶማልያ መንግሥት ግን ወታደሮቹ ትግራይ ውስጥ የነበሩ መሆናቸውን አስተባብሏል፡፡

የሱማሊያ ኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ኦስማን ዱቤ ትላንት ለሚዲያዎች በሰጡት መግለጫ ከሱማሊያ ወታደሮች ጋር የሚወጡት መረጃዎች ሀሰተኛ፣ መሰረተቢስ አሉባልታ፣ እና ፖለቲካዊ ፕሮፖጋንዳ ነው ብለዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/SOMALIA-06-11

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ🇪🇹 #ኤርትራ🇪🇷

የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ቡድን ከኤርትራ አቻቸው ጋር ዛሬ ከ ቀኑ 9:00 ሰዓት ጀምሮ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታውን የሚያካሂስ ይሆናል።

ከጨዋታው አስቀድሞ ልዩ የመክፈቻ ስነ- ስርዓት እንደሚኖር የተገለፀ ሲሆን፤ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንደሚታደሙበት ይጠበቃል።

More : @tikvahethsport
#ኢትዮጵያ🇪🇹 #ኤርትራ🇪🇷

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከአዛም ቲቪ ጋር በመተባበር የሴካፋ ከ23 ዓመት በታች ውድድር የመክፈቻ ጨዋታ ከ8:30 ጀምሮ በአማራ ቴሌቪዥን በቀጥታ እንደሚተለላፍ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሳውቋል።

More : @tikvahethsport
#China

ኢትዮጵያ ፣ ኤርትራ እና ሱዳን ስለ ቻይና-ታይዋን ጉዳይ ምን አሉ ?

#ኢትዮጵያ

ሀገራችን ኢትዮጵያ የሰሞኑን የቻይና-ታይዋን ጉዳይ የተከሰተውን ውጥረት በትኩረት እየተከታተለች መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም ለኢዜአ ተናግረዋል።

አምባሳደር መለስ ፤ ኢትዮጵያ ለረጅም ዓመታት ስታራምድ የቆየችውን የአንድ ቻይና ፖሊሲ አቋሟን እንዳጸናች መሆኑን ተናግረዋል።

" የኢትዮጵያ የአንድ ቻይና ፖሊሲ አቋም ዛሬ የተጀመረ አይደለም ያሉት " አምባሳደር መለስ፤ " ከቻይና ጋር በነበረን ግንኙነት ሁሉ የኢትዮጵያ መንግስታት አፅንተው የያዙት አቋም ነው " ብለዋል።

አሁንም ቢሆን ኢትዮጵያ ለ #አንድ_ቻይና ፖሊሲ ፅኑ አቋም አላት ያሉ ሲሆን ፖሊሲውን ኢትዮጵያ አባል የሆነችባቸው የተመድና የአፍሪካ ህብረት የሚያራምዱት አቋም መሆኑን ገልፀዋል።

#ሱዳን

ሱዳን ለአንድ ቻይና መርህ ድጋፏን እንደምትሰጥ አሳውቃለች። ታይዋንም የቻይና ግዛት አካል መሆኗን ገልጻለች።

ሱዳን ፤ ቻይና ሉዓላዊነቷን እና የግዛት አንድነትዋን በመጠበቅ ረገድ የምታደርገውን እንቅስቃሴ እንደምትደግፍም አስታውቃለች።

#ኤርትራ

ኤርትራ የአሜሪካ አፈጉባዔ ወደ ታይዋን ያደረጉት ጉዞ ከዓለም አቀፍ ህግና መርህ ያፈነገጠ ነው ብላለች።

የአፈጉባኤዋ ድርጊት የቻይና መንግስት ሉዓላዊነት ደንቦችን እና ድንጋጌዎች እንዲሁም " የአንድ-ቻይና " ፖሊሲ የሚጻረር እና የቻይናውያን ውህደት ሂደትን የሚያደናቅፍ ነው ስትል ገልፃለች።

ኤርትራ፤ አሜሪካ ቻይናን ለመቆጣጠርና ለመያዝ ጥረት እያደረገች ነው ብላ ድርጊቱ አጸያፊ ነው ብላለች።

#CGTN #ENA #AlAIN #Shabait

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ ኤርትራ ያሉ የሶማሊያ ብሄራዊ ጦር አባላት ዛሬ በፎቶ ታይተዋል። አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሙሃሙድ ላለፉት 2 ዓመታት በኤርትራ ስልጠናቸውን እየተከታተሉ የሚገኙትን የሶማሊያ ብሄራዊ ጦር አባላትን ጎብኝተዋል። ፕሬዜዳንቱ ኤርትራ ያሉ የሶማሊያ ጦር አባላትን ከኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በመሆን ነው የጎበኙት ተብሏል። የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ከትላንት ጀምሮ በኤርትራ የስራ…
#ሶማሊያ #ኤርትራ

የ5 ሺህ የሶማሊያ ወታደሮች ጉዳይ ከምን ደረሰ ?

የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ ፤ የሶማሊያ ወታደሮች ከኤርትራ ያልተመለሱበት ምክንያት ፤ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሀገሪቱ ውስጥ (በሶማሊያ) ባለው የፖለቲካ ልዩነት ምክንያት ሊመልሷቸው ፈቃደኛ ባለመሆናቸው መሆኑን ገልፀዋል።

ኤርትራ የሶማሊያን ኃይል በማሰልጠን ረገድ ጥሩ ሀሳብ እንዳላትም ፕሬዜዳንቱ ተናግረዋል።

ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ ፤ ኤርትራ 5000 የሶማሊያ ወታደሮችን ማሰልጠን ብቻ ሳይሆን እያስታጠቀችም ነው ብለዋል።

የሶማሊያ መንግስት በኤርትራ የሰለጠኑ ወታደሮቹን ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ እየሰራ መሆኑን የገለፁት ፕሬዜዳንቱ ለዚህም የአሜሪካን ድጋፍ መጠየቁን (ወታደሮቹን ለመመለስ) አሳውቀዋል።

ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ በቅርቡ ወታደሮቹ እንደሚመለሱና ከአልሸባብ ጋር በሚደረገው ጦርነት የራሳቸውን አስተዋፆ እንደሚያበረክቱ " አረጋግጣለሁ " ሲሉ ተናግረዋል።

በነገራችን ላይ የሶማሊያው ፕሬዜዳንት በአሁን ሰዓት አሜሪካ የሚገኙ ሲሆን ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር ጨምሮ ከሌሎች የአሜሪካ ባለስልጣናት እና የዓለም አቀት ተቋማት ኃላፊዎች ጋር በሀገራቸው ጉዳይ መክረዋል።

ከአንቶኒ ብሊንከን ጋር በነበራቸው ቆይታ ፤ በሶማሊያ ሽብርተኝነትን መዋጋት፣ መልካም አስተዳደርን ማስፈን እና ለድርቅ ምላሽ መስጠት ላይ መስማማታቸውን ገልፀዋል። አሜሪካ በሶማሊያ የዘላቂ ልማት እና እድገት ስትራቴጂክ አጋር መሆኗንም ገልጸዋል።

መረጃ ምንጭ፦ የቪኦኤ ሶማሊኛ ክፍል ጋዜጠኛ ሀሩን ማሩፍ ፣ ቪላ ሶማሊያ እና የፕሬዜዳንቱ (ሀሰን ሼክ ሞሀመድ) ትዊተር ገፅ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA አሜሪካ ትላንት ምሽት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ አንቶኒ ብሊንከን አማካኝነት በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ዙሪያ መግለጫ አውጥታለች። በዚህ መግለጫ ምንድነው ያለችው ? - በሰሜን ኢትዮጵያ በተለይም በትግራይ ክልል " በሽሬ ዙሪያ " ግጭት እየጨመረ መምጣቱ፣  የሰው ህይወት እያለፈ መሆኑ፣ ሰላማዊ ሰዎችን ያለየ ጥቃት እና ውድመት መከሰቱ  በጣም ያሳስበናል ብላለች። - " የኢትዮጵያ…
#Update

ትላንት ለሊት አሜሪካ ሰኞ ሊደረግ ከታቀደው የሰላም ንግግር ጋር በተያያዘ መግለጫ አውጥታለች።

በዚህ መግለጫ በኢትዮጵያ መንግስት እና በትግራይ ክልል ባለስልጣናት መካከል በአፍሪካ ህብረት መሪነት ሊደረግ የታቀደውን የሰላም ንግግር በደስታ እንደምትቀበለው ገልፃለች።

አሜሪካ ፤ " ደቡብ አፍሪካ ውይይቱን ስላስተናገደች እናደንቃለን " ያለች ሲሆን የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ ተወካይ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ እና የአፍሪካ ህብረት የፓናል አባላት ፑምዚሌ ምላምቦ-ንጉካ እና ኡሁሩ ኬንያታ ፤ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በመስከረም ወር ላይ ለተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ እንደተናገሩት በኢትዮጵያ ጦርነቱ የሚያበቃበትን እና የህዝቡን ደህንነት ወደ ነበረበት እንዲመለስ ስምምነት እንዲደረግ ለማመቻቸት የሚያደርጉትን ጥረት ለመደገፍ ዝግጁ ነን ስልት አሳውቃለች።

አሜሪካ የአፍሪካ ህብረት አጋር እንደመሆኗ መጠን በሰሜን ኢትዮጵያ ሰላም ለማስፈን በሚደረገው ጥረት ንቁ ተሳትፎዋን ለመቀጠል ቁርጠኛ መሆኗን ገልፃለች።

ለሰብዓዊ ድጋፍ ሲባል ለ5 ወር የዘለቀው ግጭት የማቆም ውሳኔ ነሃሴ ወር ላይ ከፈረሰ በኃላ የሰው ህይወት ስለመጥፋቱ ፣ ውድመት ስለመድረሱ ፣ ሲቪሎችን ባለየ ሁኔታ የተፈፀሙ ድብደባዎች እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ረገጣዎችን የሚመለከቱ ሪፖርቶች ያሳስቡኛል ብላለች።

አሜሪካ በትላንት መግለጫዋ ፤ ሁሉም ወገኖች በአስቸኳይ ግጭት እንዲያቆሙ ፣ የኢትዮጵያ መከላከያ እና የኤርትራ መከላከያ የጋራ ወታደራዊ ኦፕሬሽን እንዲያቆሙና ሰላማዊ ሰዎችን እንዲጠብቁ በድጋሚ ጠይቃለሁ ብላለች።

በተጨማሪ #ኤርትራ ጦሯን ከሰሜን ኢትዮጵያ እንድታስወጣና ያልተቆራረጠ ሰብዓዊ ድጋፍ ለተቸገሩ ወገኖች ሁሉ መደረሱን እንዲቀጥል ጠይቃለች።

@tikvahethiopia
#ኤርትራ #ኦርቶዶክስ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ ፓትርያርክ ዘሀገረ ኤርትራ አረፉ።

የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን 5ኛ ፓትርያርክ የነበሩት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው በዘጠና ስድስት (96) ዓመታቸው ማረፋቸውን ተሰምቷል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ ከሰኔ 6 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ ቤተክርስቲያኒቱን በፓትርያሪክነት ሲያገለግሉ ነበር።

@tikvahethmagazine @tikvahethiopia
#ኤርትራ #ሱዳን

የጎረቤት ሀገር ሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዜዳንት የሆኑት ጄነራል ሞሀመድ ሃምዳን ደጋሎ (ሄመቲ) ዛሬ ሰኞ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ #ኤርትራ፣ አስመራ ማቅናታቸው ተሰምቷል።

ሄሜቲ በአስመራ ቆይታቸው ከፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት እና በሁሉም መስክ ግንኙነታቸውን ማሳደግና ማጎልበት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ይፋዊ ውይይት ያደርሉ ተብሏል።

@tikvahethiopia
#ሶማሊያ #ኢትዮጵያ #ኤርትራ

የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሐሰን ሼይክ መሐሙድ " የሶማልያ እና የኢትዮጵያን የሁለትዮሽ ግንኙነት እና ስልታዊ አጋርነት ለማጠናከር ቁርጠኛ ነኝ " ሲሉ አሳውቀዋል።

ፕሬዝደንቱ ይህን የገለጹት ዛሬ በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር ሞሐመድ ዋሬ የሹመት ደብዳቤ በተቀበሉበት ወቅት እንደሆነ የሶማሊያ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።

ፕሬዝደንት ሐሰን ሼይክ መሐሙድ ዛሬ የአምባሳደሩን የሹመት ደብዳቤ የተቀበሉት ለሥራ ጉብኝት ከተጓዙበት አስመራ ወደ ሞቃዲሾ ከተመለሱ በኃላ ነው።

ፕሬዝደንቱ በአስመራ ከኤርትራው አቻቸው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ተገናኝተው መወያየታቸው ታውቋል።

ውይይቱ " የጋራ ጠቀሜታ ባላቸው የቀጠናዊ ጉዳዮች " ላይ እንደነበረ የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል መናገራቸውን ዶቼ ቨለ ዘግቧል።

የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ወደ ስልጣን ከመጡ በኃላ ለስራ ጉብኝት ወደ ኤርትራ በተደጋጋሚ ጊዜ መጓዛቸው ይታወቃል።

@tikvahethiopia
#ኤርትራ #ሩስያ

የሩሲያ ፕሬዚደንት ቭላዲሚር ፑቲን #የኤርትራ ፕሬዚደንት ኢሳይያስ አፈወርቂን በክሬምሊን ቤተ መንግሥት ተቀብለው አነጋገሩ።

የኤርትራ የማስታወቂያ ሚንስትር የማነ ገብረ መስቀል በትዊተር ገጻቸው ባወጡት ቃል ፤ ፕሬዚደንት ኢሳይያስ እና ፕሬዚደንት ፑቲን ዛሬ ረቡዕ ከቀትር በኋላ ባደረጉት ቆይታ የአገሮቻቸውን የሁለትዮሽ ግንኙነት፤ ዐለም አቀፍ ጉዳዮች እንዲሁም በጋራ ትኩረት በሚሰጧቸው ሁኔታዎች ዙሪያ በስፋት መወያየታቸውን አስታውቀዋል፡፡

አያያዘውም ፤ “የኤርትራ ፕሬዚደንት ኢሳይያስ በሩሲያ ፌዴሬሽን ያደረጉት #የመጀመሪያ ጉብኝት ለሁለቱ ሀገሮች ግንኙነት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ፕሬዚደንት ፑቲን አስምረውበታል” ብለዋል፡፡

“የሁለቱ ሀገሮች ግንኙነት ርምጃ ሙሉ በሙሉ አመርቂ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ” ፑቲን መናገራቸው አክለው “በመጪው ሐምሌ ወር ሞስኮ በምታስተናግደው ሁለተኛው የሩሲያ እና የአፍሪካ የመሪዎች ጉባዔ ላይ እንዲገኙ ጋብዘዋቸዋል” ብለዋል፡፡

የኤርትራ ፕሬዚደንት በበኩላቸው ጉብኝታቸው የሁለቱን ሀገሮች ከፍተኛ የአጋርነት እና የምክክር ግንኙነት የሚያንጸባርቅ መሆኑን መናገራቸውን የማስታወቂያ ሚኒስትሩ የማነ ገብረ መስቀል አመልክተዋል፡፡

#ቪኦኤ
ፎቶ፦ የማነ ገ/መስቀል

@tikvahethiopia
#አሜሪካ

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አንደኛ ዓመትን አስመልክተው መልዕክት አስተላልፈዋል።

አንቶኒ ብሊንከን ምን አሉ ?

- ብሊንከን በደፈናው #ኢትዮጵያ እና #ኤርትራ ጠብ ከሚያጭሩ ድርጊቶች እንዲቆጠቡና የአካባቢውን አገራት ነጻነት፣ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ማክበር አለባቸው ብለዋል።

- የኤርትራ ኃይሎች ከትግራይ ክልል ሙሉ ለሙሉ መውጣትን እንዳለባቸው ገልጸዋል።

- ስምምነቱን ተከትሎ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር መመሥረቱን ጨምሮ የተወሰዱ በጎ እርምጃዎችን አሜሪካ እንደምትደግፍ አሳውቀዋል።

- ህወሓት ኃይሎቹ ከባድ መሳሪያቸውን ፈትተው ተዋጊዎች ማሰናበት በተጀመረበት ጊዜ በትግራይ ውስጥ ዘላቂ ሰላም ለማስፍን ተጨማሪ እርምጃዎች መውሰድ ያስፈልጋል። ለዚህም የኤርትራ ኃይሎች ሙሉ ለሙሉ መውጣት አለባቸው ብለዋል።

- ብሊንከን አሜሪካ በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በሌሎችም አካባቢዎች ያሉት ግጭቶች እንደሚያሳስባት ገልጸዋል። ያለው ነገር  በቀላሉ ሊታወክ የሚችለውን የኢትዮጵያን ሰላም አደጋ ላይ እንደጣለው አመልክተዋል።

- በአገሪቱ በተለያዩ ወገኖች የቀጠለው የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እና ጥቃት፣ " የመርዛማ ንግግሮች " መስፋፋት በጦርነቱ ምክንያት የሳሳውን ማኅበራዊ ትስስር የበለጠ እየሸረሸረው መሆኑን ገልጸዋል። ለዚህም ፦
🔹አስተማማኝ የሽግግር ፍትሕ፣
🔹ሐቀኛ እና አካታች ብሔራዊ ምክክር በመላዋ አገሪቱ ተግባራዊ እንዲሆን እንዲሁም በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች የሚካሄዱትን ግጭቶች ለመፍታት ውይይት እንዲደረግ አስቸኳይ ጥሪ አቅርበዋል።

#BBC
#SecretaryofStateAntonyJBlinken

@tikvahethiopia
#ኤርትራ

ኤርትራ የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌላ ቤርቦክን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረን አውሮፕላንን ከአየር ክልሏ ማስወጣቷ ተነግሯል።

የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌላ ባየርቦክ ትላንት እንዳስታወቁት፤ ወደ ጂቡቲ ሲጓዝ የነበረው የጀርመን መንግስት አውሮፕላን ያለ እቅድ ሳዑዲ አረቢያ ለማረፍ መገደዱን ገልጸለዋል።

ይህ የሆነ በኤርትራ የአየር ክልል ላይ ለማለፍ ፍቃድ ባለማግኘቱ እንደሆነም አስታውቀዋል።

ሚኒስትሯ በ3 የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ለ3 ቀናት ጉብኝት ለማድረግ በጉዞ ላይ የነበሩ ሲሆን፤ የመጀመሪያ ጉብኝታቸውም ጂቡቲ ነበረች።

ሚኒስትሯ ፤ ያለ እቅድ በሳዑዲ አረቢያ ለማረፍ መገደዳቸው በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ያለውን አለመረጋጋት ያመለክታል ብለዋል።

ትላንት ወደ ሳዑዲ አረቢያ ሄደው ለማደር የተገደዱት ሚኒስትሯ ዛሬ በጅቡቲ ጉብኝታቸውን ጀምረዋል።

የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ " አውሮፕላኑን በኤርትራ የአየር ክልል ላይ ለማብረር ፈቃድ እንዳልተሰጠው ያወቅነው ትናንት ጠዋት ከበረራው ጥቂት ደቂቃዎች ቀደም ብሎ ነበር " ብሏል።

አውሮፕላኑ #በበረራ_ላይ_እያለ ፈቃዱን ያገኛል ተብሎ በመወሰኑ ወደዚያ መሄዱንም ገልጿል።

ከቤርቦክ ጋር የተጓዙት ልዑካን ፤ አውሮፕላኑ እየበረረ ፈቃድ ማግኘት እንግዳ እንዳልሆነ ተናግረዋል።

ቤርቦክን ፤ የሱዳን ጦርነት ጉዳይ እና የቀይ ባህር የመርከብ መንገድ ጉዳይ ትኩረት አድርጓል የተባለው የምሥራቅ አፍሪቃ ጉብኝታቸውን ነገ በደቡብ ሱዳን ያጠናቅቃሉ ተብሏል።

#AlAinNews #DW

@tikvahethiopia
የኤርትራ መንግሥት 46 እስረኞችን ለቀቀ።

በትግራይ ክልል ጦርነት ወቅት ከክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ወደ #ኤርትራ ተወስደው በኤርትራ መንግሥት ታስረው ከነበሩ የትግራይ ተወላጆች ውስጥ 46ቱ በዛሬው ዕለት ተለቀው ሽራሮ ከተማ ገብተዋል።

የሽራሮ ከንቲባ አቶ ሙሉ ብርሃነ ለ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ድርገጽ በሰጡት ቃል ፥ እስረኞቹ በኤርትራ የጋሽ ባርካ ዞን መቀመጫ በሆነችው የባረንቱ ከተማ ታስረው የቆዩ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ዛሬ ጠዋት በ”አይሱዙ” ተሽከርካሪ ተጭነው ሽራሮ እንደገቡ ተናግረዋል።

በእስር ላይ የቆዩት የትግራይ ተወላጆች “ ምህረት ተደርጎላቸው ” የተለቀቁ ሲሆን ይህም በኢፌዲሪ የመከላከያ ሰራዊት እና በኤርትራ ሰራዊት መካከል ሲካሄድ በቆየ ንግግር መሆኑን ከንቲባው ገልጸዋል።

እስረኞቹ ተለቅቀው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የተደረገው፤ በጦርነቱ ጊዜ “ ከባድ የሆነ ወንጀል ያልፈጸሙ ናቸው ” በሚል ምክንያት ነው።

በኤርትራ እስር ላይ ከሚገኙ የትግራይ ተወላጆች መካከል አሁንም ያልተፈቱ አሉ።

የዛሬው እርምጃ የቀሩትም እንደሚለቀቁ “ ተስፋ ሰጪ ነው ” ሲሉ የሽራሮ ከተማ ከንቲባ ለድረገፁ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

@tikvahethiopia