አምቦ ዩኒቨርሲቲ⬆️
በአምቦ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለተመደቡ ተማሪዎች በከተማው ነዋሪዎች አቀባበል ተደረገላቸው።
የአምቦ ከተማና አከባቢዋ ነዋሪዎች ከተለያዩ የአገሪቱ አከባቢዎች አዲስ ወደ አምቦ ዩኒቨርሲቲ ለተመደቡ 5 ሺ ለሚሆኑ ተማሪዎች አቀባበል አድርገዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር #ታደሰ_ቀነዓ፣ አባገዳዎች፣ የእምነት አባቶችና የአምቦ ከተማ ቄሮዎች ለእነዚህ ተማሪዎች አቀባበል አድርገዋል፡፡
በዩኒቨርሲቲው አዲስ ከተመደቡት ተማሪዎች ውስጥ አስተያየት የሰጡት ተማሪዎች በአምቦ ከተማና አከባቢዋ ነዋሪዎችና በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ የተደረገላቸው አቀባበል እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል፡፡
ምንጭ፦OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia

አምቦ ዩኒቨርሲቲ!
#የአምቦ_ዩኒቨርሲቲ በሎሬት #ፀጋዬ_ገብረመድህን ስም የባህል ማዕከል እንደሚያቋቁም አስታውቋል። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር #ታደሰ_ቀነዓ ለኢዜአ እንደገለጹት ማዕከሉ የሚቋቋመው የሎሬቱን ጨምሮ በኪነ ጥበብ ሥራዎች ላይ ጥናትና ምርምር ለማድረግና ተሰጥኦ ያላቸውን ጠቢባን ለማፍራት ነው።
“ማእከሉን ለሟቋቋም ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ሥራ ተገብቷል” ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ ማዕከሉን ለማቋቋም ከአዲስ አበባ፣ ከባህር ዳርና ከደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲዎች ልምድ ቀስሟል ብለዋል።
ከሎሬት ጸጋዬ ወጥ ሥራዎች መካከል የአቴቴ ሥርዓት፣ የገዳ ሥርዓት፣ ዝክረ መርካቶ፣የኩሽ ሕዝቦች ሥልጣኔ፣ዳግማዊ ቴዎድሮስ፣ ኦዳና አቡነ ጴጥሮስን የሚዘክሩት ተጠቃሽ ናቸው።
ከትርጉም ሥራዎቻቸው መካከል የዊሊያም ሼክስፒር ድርሰቶች ሃምሌትና ኦቴሎ ዘመን ተሻጋሪ ሥራዎች ይገኙበታል።
#የአምቦ_አካባቢ_ተወላጅ የሆኑት ሎሬት ፀጋዬ በ60 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም የተለዩት በ1998 ነበር።
ምንጭ፦ ኢዜአ