TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከዓለም ዙሪያ #1 ፦

➡️ #ሴኔጋል ፦ በምዕራብ ሴኔጋል ፤ ቲቫዋን በምትሰኝ ከተማ በአንድ ሆስፒታል ውስጥ በደረሰ ቃጠሎ 11 አዲስ የተወለዱ ህጻናት መሞታቸውን ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል ተናግረዋል።

➡️ #አፍጋኒስታን ፦ በአፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል እና ሰሜናዊ ከተማ ማዛር ኢ ሻሪፍ ከተከታታይ በደረሱ ፍንዳታዎች ቢያንስ 14 ሰዎች መገደላቸው ተነግሯል። ዳኢሽ ለጥቃቱ ኃላፊነት መውሰዱን ሮይተርስ ዘግቧል።

➡️ #ሩስያ ፦ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን ላይ ለሚያካሂዱት ኦፕሬሽን ወታደሮቻቸውን ወደ ሀገሪቱ ከላኩ በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ዩክሬን ውስጥ በወታደራዊ ዘመቻው ከቆሰሉ ወታደሮች ጋር ተገናኝተዋል። በሌላ የሩስያ ጉዳይ ፤ ሀገሪቱ ያለባትን የውጭ ሀገራት እዳ በራሷ መገበያያ ገንዘብ “ሩብል” ለመክፈል ወስናለች ፤ እዚ ውሳኔ ላይ የደረሰችው የአሜሪካ ግምጃ ቤት ከቀናት በፊት በሩሲያ በአሜሪካ ባንኮች በኩል የምትፈጽመውን የውጭ ዕዳ ክፍያ ፍቃድ መሰረዙን ተከትሎ ነው።

➡️ #ዩክሬን ፦ ወደ ሰቨሮዶንስክ ከተማ የሚወስደውን አውራ ጎዳና ለመቆጣጠር በሩስያ እና ዩክሬን ኃያሎች መካከል ከፍተኛ ጦርነት እየተደረገ ነው። ሩሲያ ይህን ከተማ ለመቆጣጠር ተቃርቢያለሁ ብትልም አንድ ከፍተኛ የዩክሬን ባለሥልጣን ነገሩን አስተባብለዋል። ይህ ጎዳና ዩክሬን የምትቆጣጠራቸውን ከተሞች ሩሲያ ከያዘቻቸው ከተሞች ጋር የሚያገናኝ ከፍ ያለ ወታደራዊ ዋጋ ያለው ነው።

➡️ #ጋምቢያ ፦ የጋምቢያ መንግስት የቀድሞ ፕሬዝዳንት ያህያ ጃሜህ ከ20 አመታት በላይ በዘለቀው የስልጣን ዘመናቸው ተፈጽመዋል በተባሉ ግድያ፣ አስገድዶ መድፈር፣ ማሰቃየት እና ሌሎች ወንጀሎች ላይ ክስ እንደሚመሰርት አስታውቋል።

#አልጀዚራ #ቲአርቲወርልድ #ስፑትኪን #ሮይተርስ

@tikvahethiopia