TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጀርመን

ጀርመን ውስጥ በአስራዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሁለት ሴቶችን በስለት የወጋው ኤርትራዊ የዕድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት።

ጥገኝነት ጠያቂ የሆነው ይህ ኤርትራዊ በስለት ከወጋቸው ሁለት ታዳጊ ሴቶች መካከል የአንዷ ሕይወቷ አልፏል።

ኡቁባ ቢ በሚል ስም ብቻ የተጠቀሰው የ27 ዓመቱ ግለሰብ፣ ሁለቱ ታዳጊ ሴቶች ላይ ጥቃቱን የፈጸመው በዚህ ዓመት ኅዳር ወር ላይ " ኢሌራኪራቸበርግ " ተብላ በምትጠራ የጀርመን ከተማ ውስጥ ነው።

በጀርመን ከፍተኛ ቁጣን በቀሰቀሰው በዚህ የወንጀል ድረጊት ኤስ የተባለችው የ14 ዓመት ታዳጊ 23 ጊዜ በስለት ተወግታ ሕይወቷ ሲያልፍ፤ የ13 ዓመት ጓደኛዋ ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባታል።

ዐቃቤ ሕግ ምን አለ ?

የዕድሜ ልክ እስራት የተፈረደበት ኤርትራዊ ስለቱን የያዘው በአካባቢው በሚገኝ የኢሚግሬሽን መሥሪያ ቤት ውስጥ ሊጠቀመው አስቦት የነበረ ነው።

ነገር ግን ግለሰቡ የያዘውን ቢላ ታዳጊዎቹ ከተመለከቱበት በኋላ ጥቃት ሰንዝሮባቸዋል አንደኛዋን ለሞት ሲዳርጋት ሌላኛዋ ክፉኛ ጎድቷታል።

ዐቃቤ ሕግ እንዳለው ግለሰቡ ታዳጊ ሴቶቹ " ለፖሊስ ይጠቁሙብኛል " በሚል ድንገት ወንጀሉን ፈጽሞባቸዋል።

ግለሰቡ ወደ #ኢትዮጵያ ተጉዞ ጋብቻ ለመፈጸም ከጀርመን ባለሥልጣናት የጠየቀው የጉዞ ሰነድ ስላልተሰጠው በኢሚግሬሽን ኃላፊዎች ተበሳጭቶ ነበር።

በደቡብ ጀርመን የሚገኘው ፍርድ ቤት ኤርትራዊው የፈጸመው ወንጀል " እጅግ ከባድ " በመሆኑ ግለሰቡ 15 ዓመታት በእስር ከቆየ በኋላ እንኳን ከእስር የመለቀቅ ዕድሉ በጣም የጠበበ ነው ተብሏል።

ኤርትራዊው ጀርመን መች ገባ ?

ይህ ኤርትራዊ ጀርመን የገባው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ስደተኞች ጦርነት እና እስርን በመሸሽ አውሮፓን ባጥለቀለቁበት ዓመት እአአ 2015 ላይ ነበር።

ኡቁባ ቢ ለፍርድ ቤት ምን አለ ?

ኡቁባ ቢ ፍርድ ቤት በቀረበበት ወቅት በፈጸመው የወንጀል ድርጊት #መጸጸቱን ገልጾ የተጎጂ ቤተሰቦች ይቅርታን ጠይቋል።

ይግባኝ ...

ግለሰቡ የተላለፈበትን ብይን ይግባኝ መጠየቅ ይችላል ተብሏል።

ፍርደኛው የሚያቀርበው ይግባኝ ውድቅ ከተደረገ ግን በእስር ጊዜው ወቅት ወደ ትውልድ አገሩ እንዲመለስ ሊደረግ እንደሚችል ዐቃቤ ሕግ ገልጿል።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia