TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
107 ፓርቲዎች

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እባካችሁ ተዋሃዱ ብሎ ሲማፀናቸው የነበሩት ወደ ሰማንያ (80) አካባቢ የሚገመቱ ፓርቲዎች በጥቂት ወራት ውስጥ 107 ደርሰዋል።
--
ከ 107ቱ ውስጥ ሰላሳ ሶስቱ (33) "#ኢትዮጵያ "ን በፓርቲያቸው ስያሜ ውስጥ ተጠቅመዋል። #አማራ የሚል ስያሜአቸው ውስጥ ያላቸው
#አምስት ሲሆኑ #አስራ_ሶስቱ ደግሞ #የኦሮሚያ ፓርቲዎች ናቸው። እነ አንዳርጋቸው ፅጌ ብዙ ጊዜ ክፍፍል ያለው "በዘውግ" የተደራጁ ፓርቲዎች ላይ ነው ቢሉም በኢትዮጵያዊነት ስም የተደራጁት 33 ፓርቲዎች ራሱ ተቀራርበው መዋሃድ አልቻሉም። #ሰማያዊ_ፓርቲ ለምሳሌ #ከአግ7ጋር ተዋህዶ ፈርሷል ቢባልም ዝርዝሩ ውስጥ ተካቷል።
--
ኢህአዴግ እንደ ግንባርም በተናጠልም የፈረመበት ምክንያት ግራ ያጋባል። በዛ ላይ የተፈረመበት ሰነድ ላይ አዴፓ እና ኦዴፓ ሳይሆን #ብአዴን እና #ኦህዴድ ነው የሚለው። አንድ ወጥ ሀገር አቀፍ ፓርቲ ሆነው በድጋሚ ለመመዝገብ ነው ለስያሜው እንኳን ቸልተኛ የሆኑት?
--
ለማንኛውም ሰማንያ አካባቢ ፓርቲ የተሳተፈበት የ 1997 (2005) ምርጫ ላይ የክልል ምክር ቤት መቀመጫ ያሸነፉት ፓርቲዎች ከላይ ያሉት ነበሩ። በርካቶቹ አንድም መቀመጫ እንዳላገኙ የሚታወቅ ነው።

Via THE FINFINNE INTERCEPT
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#LemmaMegersa #PP

"...አይሆንም ያልኩበት ምክንያት አንደኛ እኛ የኦሮሞ አመራር አባላት የኦሮሞ ህዝብ አምኖን ያቀረበልን ትላልቅ ጥያቄዎች አሉ፤ እነዚህ ጥያቄዎችን እንመልስላችኃለን ብለን ቃል ገብተናል። ህዝባችን ይህን ጥያቄ ያቀረበልን የትላንቱን #ኦህዴድ ስም ለውጠንለት #ኦዴፓ ካልን በኃላ ነው። ስለዚህ ህዝቡ ጥያቄውን አንድ፣ ሁለት፣ ሶስት ብሎ የሰጠው ለሀገራዊ ፓርቲ ሳይሆን ለኦዴፓ ነው። ስለዚህ የህዝቡን ጥያቄ ሳንመልስ ይህን ማድረግ ትክክል አይደለም፤ እምነት ማጉደል ይሆናል እናም ጥያቄዎቹን ቆጥሮ እንደሰጠን መመለስ አለብን የሚል እምነት አለኝ።" አቶ ለማ መገርሳ

.
.
"...የመደመር ፍልስፍና የምንለው ለውጡ የሚመራበት ፍኖተ ካርታ፤ እይታ ነው። በበፊቱ አግባብ መሄድ አንችልም። ጠንካራ ጎኖችን ከድሮ እናስቀጥላለን። ደካማ ጎኖችን ማረም አለብን። ይሄ ለውጡ በምን አይነት ፍኖተ ካርታ ይመራ የሚል የህዝብም የሊሂቃንም ጥያቄ ነበር። በምንድነው የምንመራው ? ፍኖተ ካርታ የለም የሚል አንድ አመት፣ አንድ አመት ተኩል ይሆናል ለውጡ ከተጀመረ በኃላ፤ የመደመር ዋነኛው አስፈላጊነት ለውጡ በምን ጎዳና ይመራል? ከዴሞክራሲ አኳያ እንዴት ነው የምንመራው? ከሰላም አኳያ እንዴት ነው የምንመራው? ከኢኮኖሚ አኳያ እንዴት ነው የምንመራው? ከፖለቲካ አኳያ ቀጣይ እይታችን፣ ቀጣይ ሃሳባችን ፍኖተ ካርታው ባጠቃላይ ሚመራበት ምንድነው የሚለውን ሚመልስ ነው።" አቶ ፍቃዱ ተሰማ (የብልፅግና ፓርቲ ኦሮሚያ ፅ/ቤት ኃላፊ)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot