TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ለሁሉም የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት በሙሉ፦

▪️ጥር 1 እስከ ጥር 21-TIKVAH-ETH▪️

የሰላም፣ የፍቅር እና አንድነት ሳምንታትን በመላው ሀገሪቱ አውጀን የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን እያደረግን እንገኛለን። በፌስቡክ ላይ ተፅእኖ እንዲፈጠር እያደረጋችሁት ላለው ትልቅ ስራ ምስጋና ይገባችኃል።

#ነገ_ሰኞ ሁሉም የቤተሰባችን አባል ተከታዮቹን ስራዎች እንዲሰራ በታላቅ ትህትና እንለምናለን፦

•ሰራተኞች ወደስራ ከመግባታችሁ በፊት አንዳች መልካም ስራ እንድትሰሩ፦ በጎዳና ላይ ካሉ አቅም ከሌላቸ ወገኖች አንዱን እንኳን ቁርስ ብታበሉ። አልያም እናተ ለአእምሯቹ ደስታን የሚሰጣችሁን መልካም ስራ ብትሰሩ። ስራ ቦታ በሚኖራችሁ የእረፍት ጊዜ በሀገራችን ሰላም ማስጠበቅ ዙሪያ ከጓደኞቻችሁ ጋር ውይይት ብታደርጉ።

•የታክሲ ሹፌሮች በስራ እንቅስቃሴያችሁ ሰላም እና አንድነትን የሚያጎለብቱ ሙዚቃዎችን ለተሳፋሪዎች በመክፈት ተፅእኖ እድትፈጥሩ። ተሰብስባችሁ ምሳ በምትመግቡበት ወቅት ስለሰላም እና አንድነት እንድትመክሩ።

•ተማሪዎች በእረፍት ጊዚያችሁ ስለሰላም እንድትነጋገሩ። በቀጣይ ሳምንታት በተለያዩ መልካም ስራዎች ላይ ስለመሳተፍ ብትመክሩ። (በቡድን ሆናችሁ ደም ልገሳ፣ ህሙማንን መጠየቅ፣ የተቸገሩትን መርዳት...)

🔹ሁላችንም በፌስቡክ ብሄር ተኮር የጥላቻ መልዕክቶችን እና ግጭት ቀስቃሽ መልዕክቶችን የሚያስተላልፉ ገለሰቦችን #Block ማድረጋችንን አጠናክረን እንቀጥላልን!!

🙏መልዕክቱ ተፈፃሚ እንደሚሆን ባለሙሉ ተስፋ ነን!! በቤተሰባችን አፍረን አናውቅም!!🙏
@tsegabwolde @tikvahethiopia