TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.48K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
እጅግ በጣም አሳዛኝ! የሶሪያ መንግስት በምስራቃዊ ጎህታ እያካሄደ ባለው የአየር ድብደባ የክሎሪን ጋዝ ቦምብ መጠቀሙ እየተነገረ ነው።

የሶሪያ የሲቪል መብቶች ተከላካይ ቡድንም በትናንትናው እለት በሰጠው መግለጫው፥ መንግስት የክሎሪን ጋዝ ቦምብ ተጠቅሟል፤ እስካሁን የአንድ ህጻን ልጅ ህይወት አልፏል ብሏል።

#ሶሪያ
ሪፖርት📌በ2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ብዛት ከዓለም የሚበልጣት ሀገር እንደሌላት ተገለጸ።

በጦርነት የሚታመሱት #የመንና #ሶሪያ እንኳ የኢትዮጵያን ያሕል አልተፈናቀለባቸውም፡፡

ዛሬ ይፋ በተደረገው የ“ኢንተርናሽናል ዲስፕሌስመንት ሞኒተሪንግ ሴንተር” (IDMC) ሪፖርት መሰረት በኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 1.4 ሚሊየን ሰዎች ከቀዬአቸው ተፈናቅለዋል፡፡

የኖርዌይ ስደተኞች ምክር ቤት የክልሉ ዳይሬክተር ናይገል ትሪክስ 1.4 ሚሊየን ሕዝብ አካባቢውን ጥሎ ሲፈናቀል ዓለም ተገቢ ትኩረት አለመስጠቱን ተችተዋል፡፡ በምዕራብ ጉጂ እና ጌዲዮ በተቀሰቀሰ ግጭት ብቻ ከአንድ ሚሊየን በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው በተቋሙ ሪፖርት ተጠቅሷል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወገን! ሰከን ማለት ዋጋ አለው! #ሰላምን እስክታጣት ድረስ ምንም ላይስመስልህ ይችላል። ነገር ግን ሰላም አንዴ ከእጅህ ከወጣች የልጅ ልጅህን #ብትገብር እንኳን መልሰህ ላታገኛት ትችላለህ።

#ሶሪያ የቀደመው ገፅታዋን እና #አሁን ያለውን ገፅታዋን ከላይ ባለው ፎቶው ተመልከት። ያኔ በትንሽ በትልቁ አትባላም።

ሰላም ለኢትዮጵያ!
ተወያይተን ችግራችንን እንፍታ!
#ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወገን! ሰከን ማለት ዋጋ አለው! #ሰላምን እስክታጣት ድረስ ምንም ላይስመስልህ ይችላል። ነገር ግን ሰላም አንዴ ከእጅህ ከወጣች የልጅ ልጅህን #ብትገብር እንኳን መልሰህ ላታገኛት ትችላለህ።

#ሶሪያ የቀደመው ገፅታዋን እና #አሁን ያለውን ገፅታዋን ከላይ ባለው ፎቶው ተመልከት። ያኔ በትንሽ በትልቁ አትባላም።

ሰላም ለኢትዮጵያ!
ተወያይተን ችግራችንን እንፍታ!
#ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ይህ ነው #የግጭት_ትርፉ! ይህን እንኳን አይተን እንማር፤ እኛ ላይ ሲደርስ ደም እንባ ከምናነባ ሁላችንም ለኢትዮጵያ ሀገራችን #ሰላም ዘብ እንቁም!
.
.
#ሰውነት ከብሄር፣ ከዘር፣ ከቀለም ይቅደም!
.
.
ፎቶ ቁጥር 1. #ሶሪያ
ፎቶ ቁጥር 2. #ኢትዮጵያ/የሶርያ ስደተኛ ህፃን-አዲስ አበባ/

#እኔ ለሀገሬ ሰላም ዘብ እቆማለሁ የምትሉ የቤተሰባችን አባላት ይህቺን🕊የሰላም ምልክት የሆነችን እርግብ ተጫኗት!

#ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሶሪያ #PEACE😢ከአመታት በፊት ይህቺ ምድር ማንም እንዲህ ወደ ፍርስራሽነት ትቀየራለች ብሎ አልገመተም፤ግን ሆነ! ሶሪያ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቿን አጣች፤ በሚሊዮኖች ተወልደው ካደጉበት ሀገር ተሰደዱ!! ጦርነቱ ዛሬም አላባራም ዛሬም ሰው ይሞታል!! #ያሳዝናል! #ልብ_ይሰብራል! ሶሪያውያን ይህ ከመሆኑ በፊት ከስሜታዊነት ወጥተው፤ በሰከነ መንገድ ተረጋግተው ተነጋግረው ቢሆን ኖሮ ይህ ሁሉ ሰቆቃ ባልመጣ ነበር። ማስተዋልን የመሰለ #ጥበብ ከየት ይመጣ ይሆን?

መገንባት እንደማፍረስ ቀላል አይደለም!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሜሪካ የተሳተፈችባቸው ጦርነቶች ...

#Repost

በ21ኛው ክፍለ ዘመን አሜሪካ በበርካታ ሀገራት ውስጥ በተደረጉ ጦርነቶች እጇን አስገብታለች።

በጥቂቱ...

#አፍጋኒስታን

አል-ቃይዳ መስከረም 11 ቀን 2001 በአሜሪካን ላይ ጥቃት ከሰነዘረ በኋላ አሜሪካ ታሊባንን ከስልጣን ለማስወገድ አሜሪካ የአፍጋኒስታንን ወረራ መርታለች። 20 ዓመታት የዘለቀ እጅግ ዋጋ ያስከፈለ ጦርነት ነበር። በመጨረሻ ግን ታሊባን ወደቦታው ተመለሰ። አሜሪካም ጓዟን ጠቅልላ ወጣች።

#ኢራቅ

በፕሬዚዳንት ጆርጅ ቡሽ ዘመን አሜሪካ እ.ኤ.አ. በ 2003 ኢራቅን በመውረር ሳዳም ሁሴን ከሥልጣን አስነስታለች። በኢራቅ ጦርነት በርካቶች አልቀዋል፣ ከፍተኛ ውድመት ደርሷል። ኢራቅ ዛሬም አስተማማኝ ሙሉ ሰላም የላትም። ለዳግም ግንባታም ደፋ ቀና እያለች ነው።

#ሊቢያ

የአሜሪካና የአውሮፓ አጋሮች እኤአ በ 2011 በሊቢያ የአየር ዘመቻ ከፍተው ነበር ፤ ጥቃቱ ሙአመር ጋዳፊ በአረብ አብዮት ለመቃወም በተነሳሱ ተቃዋሚዎች ላይ የደረሰውን ግፍ ለመከላከል በሚል ነው ፤ የእነ አሜሪካ መዘቻ ጋዳፊን አወረደ ፣ ሊቢያ ግን ወደ ትርምስና ቀውስ ገባች፤ ዛሬም እዛው ናት።

#ሶሪያ

አሜሪካ ከሌሎች አጋሮቿ ጋር ሆና በሶሪያ ጦርነት ውስጥም እጇ ያለበት ሲሆን በሶሪያ የሚንቀሳቀሱ የበሽር አል አሳድ ተቃዋሚዎችን ለማጥፋት በምትወስደው እርምጃ የሶሪያ ከተሞች ክፉኛ አውድማለች።

#የድሮን_ጥቃቶች

አሜሪካ ሽብርን ለመዋጋት በሚል በፓኪስታን፣ የመን፣ ሱማሊያ፣ ሊቢያ የድሮን ጥቃቶችን ፈፅማለች (አሜሪካ ከፍተኛ የሰራዊት ቁጥር አላሰፈረችም)።

እነሊቢያ፣የመን፣ ሱማሊያ ጦርነት ምስቅልቅላቸውን አውጥቶት ዛሬም ማገገም ያልቻሉ ለደህንነት አስጊ ሀገራት ሆነው ቀርተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
#ቱርክ #ሶሪያ

በቱርክ እና ሶሪያ ድንበር አቅራቢያ ባሉ ከተሞች በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የሞቱ ሰዎች ከ4,800 በላይ መድረሱን ቢቢሲ ዘግቧል።

የሟቾች ቁጥር ከዚህ ሊበልጥ እንደሚችል እየተነገረ ነው።

የነፍስ አድን ሠራተኞችም በፍርስ ራሾች ውስጥ ተቀብረው የሚገኙ ሰዎችን ለማትረፍ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ ተብሏል።

በሌላ በኩል ፤ የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን በቱርክ የሰባት ቀናት ብሄራዊ የሀዘን ቀን አውጀዋል።

ፕሬዝዳንቱ የሀዘን አዋጁን ያወጁት በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ህይወታቸው ያለፈ ዜጎችን ለማሰብ ሲሆን በቀጣዮቹ ቀናት የሀገሪቱ ሰንደቅ አላማ ዝቅ ብሎ ይውለበለባል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Turkey

ትላንት ምሽት ቱርክ በመሬት መንቀጥቀጥ ተመታች።

እጅግ አስከፊው የመሬት መንቀጥቀጥ (7.8) ከተከሰተ ከሁለት ሳምንት በኃላ ቱርክ ትላንት ምሽት በሬክተር ስኬል መለኪያ 6.3 በሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ መመታቷ ተሰምቷል።

የመሬት መንቀጥቀጡ የመታው አካባቢ ከሁለት ሳምንት በፊት በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ከባድ ጉዳት ባጋጠመው በሃታይ ግዛት ውስጥ በምትገኘው ደቡባዊዋ ሳማንዳግ ከተማ አቅራቢያ ነው ተብሏል።

አሁን በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ቱርክ ውስጥ እስካሁን የሀገሪቱ መንግስት ባስታወቀው 3 ሰዎች የሞቱ ሲሆን ከ200 በላይ ሰዎች ተጎድተዋል።

የመሬት መንቀጥቀጡ በሰሜን ምዕራብ #ሶሪያ ውስጥ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን እስካሁን በታወቀው 130 ሰዎች ተጎድተዋል።

ምናልባት በአዲሱ የመሬት መንቀጥቀጥ ተጨማሪ ተጎጂዎች ይኖሩ ይሆን እንደሆነ ተብሎ ፍለጋዎች መቀጠላቸው ታውቋል።

ከሁለት ሳምንት በፊት በደረሰው በሬክተር መለኪያ 7.8 በተመዘገበው የመሬት መንቀጥቀጥ በቱርክ እና በሶሪያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ47,000 አልፏል።

@tikvahethiopia
#BREAKING🚨

የበሽር አላሳድ አገዛዝ ተገረሰሰ።

የሶሪያው ፕሬዜዳንት በሽር አላሳድ አገዛዝ ወደቀ። እሳቸውም ሀገር ለቀው ጠፍተዋል።

የታጠቁ የሶሪያ ተዋጊዎች የፕሬዚዳንት በሽር አል አሳድን የ24 ዓመት አገዛዝ ለመደምሰስ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የተጠናከረ ወታደራዊ ዘመቻ እያካሄዱ ነበር።

በተለይም በሰሜናዊ ክፍል የሚገኙ የታጣቁ ተቃዋሚዎች ከረዥም ዓመታት በኋላ የአገሪቱ ጦር ላይ ድንገታዊ ጥቃት ከከፈቱ በኃላ ብዙ ቦታዎችን በፍጥነት ይዘዋል።

ከሳምንት በፊት ነው አሌፖን ዘልቀው የገቡት።

ከዛ በኃላ በመላ ሀገሪቱ ውስጥ ያሉ የመንግስት መከላከያዎች በአስደናቂ ፍጥነት ፈራርሰዋል።

በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች የአማጽያኑን ምት መቋቋም ከብዷቸው ድንበር አቋርጠው ኢራቅ ለመግባትና ጥገኝነት ለመጠየቅ ተገደዋል።

ተቃዋሚዎቹ በቀናት ውስጥ እጅግ በርካታ ቁልፍ ከተሞችን እና ቦታዎችን ከአላሳድ አገዛዝ ነጻ ያደረጉ ሲሆን ለሊቱን የአሳድ መቀመጫ ወደ ሆናችው ደማስቆ መግባታቸው ታውቋል።

አላሳድ ከደማስኮ ወጥተው ሄደዋል ተብሏል።

የፕሬዜዳንቱን ከደማስቆ መልቀቅ ሁለት ከፍተኛ የጦር አመራሮች ለሮይተርስ አረጋግጠዋል።

አሁን ላይ አሳድ የት እንደገቡ የሚታወቅ ነገር የለም።

የታጠቁት ተቃዋሚዎች ባወጡት መግለጫ ፤ " ጨቋኙ በሽር አላሳድ ከደማስቆ ለቀው ሄደዋል " ብለዋል።

" ደማስቆን ከጨቋኙ በሽር አላሳድ ነጻ አውጥተናል " ሲሉም ገልጸዋል።

በሽር አላሳድ ሀገሪቱን ለቀው መጥፋታቸውንም አሳውቀዋል።

ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያውንም ተቆጣጥረውታል።

አንዳንድ ቪድዮዎች እንዲሁም ሮይተርስ የአይን እማኞችን ዋቢ በማድረግ እንደዘገበው በደማስቆ ጎዳናዎች ሶርያውያን ወጥተው ' ነጻነት ! ነጻነት ! ' እያሉ መፈክር ሲያሰሙ ደስታቸውን ሲገልጹ ታይተዋል።

እነ ሩስያ ፣ ኢራን ፣ አሜሪካ እና ቱርክ ?

የአገዛዙ ዋነኛ አጋር የሆኑት ሩሲያ እንዲሁም ኢራን ለአሳድ ቀጣይነት ያለውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ሲያሳውቁ ቢሰነብቱም አገዛዙን ከመፍረስ አልታደጉም።

ሩስያ በዩክሬን በሚያደርገው ጦርነት የተጠመደች ሲሆን፣ ኢራን ደግሞ እስራኤል በሊባኖስ ሔዝቦላህ ላይ በከፈተችው ዘመቻ ምክንያት ተዳክማለች።

ጦርነቱ ሲባባስ ሞስኮ የሩሲያ ዜጎች አገሪቱን ለቅቀው እንዲወጡ ጥሪ ስታቀርብ ነበር።

በሶሪያ የረጅም አመታት የእርስ በርስ ጦርነት ዋና ተዋናይቷ አሜሪካም ብትሆን ሁኔታውን አይታ ዜጎቿን " በደማስቆ በረራዎች እስካሉ ድረስ " ሶሪያን ለቅቀው እንዲወጡ ስትጮህ ነበር።

ቱርክ በሶሪያ ያሉ አንዳንድ የታጠቁ ተቃዋሚ ቡድኖችን ትደግፋለች።

የቱርክ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ለወራት አሳድን ከተቃዋሚዎች ጋር ፖለቲካዊ መፍትሄ ላይ አንዲደርሱ ግፊት ሲያደርጉ ነበር።

ፕሬዜዳንቱ የተቃዋሚዎችን የቅርብ ጊዜ ግስጋሴ እንደሚደግፉ ተናግረው " አሳድ ጥሪዬን ቢቀበል ኖሮ ይህ አይከሰትም ነበር "  ብለዋል።

#ሶሪያ : እ.ኤ.አ. ከ2011 ጀምሮ በተቃውሞ ስትናጥ ከቆየች በኃላ በከፋ የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ የምትገኝ ሲሆን በዚህም እጅግ በርካታ ሰዎች አልቀዋል። ሀገሪቱ እንዳልነበረ ሆናለች። ለሀገሪቱ እንዲህ መሆን የውጭ ኃይሎች አገዛዙን እና አማጽያንን በመደገፍ ረገድ ትልቅ ድርሻ አላቸው።

መረጃው ከአልጀዚራ፣ ሮይተርስ እንዲሁም ቢቢሲ የተሰባሰበ ነው።

@tikvahethiopia