TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ነዳጅ

የነዳጅ ግብይት #በመላው_ሀገሪቱ  በ " ዲጅታል " መንገድ ብቻ እንዲሆን በተላለፈው ውሳኔ መሰረት ዛሬ ግንቦት 1/2015 ተግባራዊ መሆን ጀምሯል።

በክልሎች የነዳጅ ጉዳይ ከተነሳ አይቀር ...

በክልል ከተሞች ላይ #ነዳጅ በተለይም ቤንዚን እንደልብ ማግኘት የማይታሰብ ነው። ነዳጅ ሲገኝም ለሰዓታት ረጃጅም ሰልፍ መሳለፍ እና መንገላታት አይቀሬ ነው።

እንደ #ሀዋሳ ያሉ ትልቅ ከተሞች ውስጥ ነዳጅ በወረፋ ብቻ ሳይሆን በሳምንት ለተወሰነ ቀን ብቻ ነው መቅዳት የሚቻለው (ለከተማው ነዋሪ - በኩፖን) ። ይህም የሚከናወነው በታርጋ " #ሙሉ እና #ጎዶሎ ቁጥር " ነው የሚከናወነው። ማደያዎችም ከተመደበላቸው ተሽከርካሪ ውጭ ማስተናገድ አይችሉም።

" እንግዳ ነኝ ፤ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ አይደለሁም " ለሚሉት ደግሞ የነዳጅ ማደያዎች የሚኖሩበትን ከተማ የነዋሪ #መታወቂያ በማየት እንደሚቀዱ ለመረዳት ተችሏል።

ከምንም በላይ የሚገርመው እጅግ በርካታ ማደያዎች ባሉበትና አሁንም እየተሰሩባት ባለው ከኢትዮጵያ ግዙፍ ከተሞች አንዷ ሀዋሳ በየዕለቱ ነዳጅ የሚሸጡት እጅግ ውስን ቁጥር ያላቸው ማደያዎች ናቸው።

ይህ በእንዲህ እያለ ግን በከተማው ነዳጅ በጥቁር ገበያ ከፍ ባለ ብር እንደጉድ ነው የሚቸበቸበው። ሀዋሳ ብቻ ሳይሆን በሀዋሳ ዙሪያ ጭምር ነው ይህ የሚሆነው።

የከተማው የአስተዳደር አካላት ይህንን እያወቁ መፍትሄ እየሰጡ እንዳልሆነ ከተገልጋዮች ቅሬታ ይቀርባል።

እጅግ በጣም ብዙ ተሽከርካሪዎች በሌሉበት እና በርካታ ማደያዎች ባሉበት ከተማ ነዳጅ ለማግኘት በዚህ ደረጃ መቸገር ከምን የመጣ ነው ?

ከሰሞኑን በሀዋሳ ከተማ ስላለው የነዳጅ ግብይት ጉዳይ የሲዳማ ክልል ንግድ እና ኢንዱስትሪ ቢሮ ምክትል ኃላፊ በድሶ አዲሳ ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር።

ምን አሉ ?

አቶ በድሶ አዲሳ  ፦

" ችግሩ አለ ፤ ይህ የሆነው በቀን ከ3 ሚሊዮን ሊትር የማይበልጥ ቤንዚን ስለሚቀርብ በአገር ደረጃ የቤንዚን እጥረት በመኖሩ ነው።

ለዚህም ሲባል ተሸከርካሪዎችን በየቀኑ በተለያዩ የነዳጅ ማደያ ጣቢያዎች መድበን ነው እንዲቀዱ የምናደርገው።

ችግሩ ያለው ቤንዚን ላይ ነው የነዳጅ ማደያዎችም ቤንዚን ለማግኘት አንድ ወር ይጠብቃሉ።

ነዳጅ በጥቁር ገበያ ሀዋሳ ብቻ ሳይሆን አዲስ አበባም ይሸጣል ፤ ለዚህ ተብሎ ከሌላ ቦታ የሚገባ ነዳጅ አለ።

እንደዚህ ዓይነት ተግባር የሚፈጽሙ የተወሰኑ ማደያዎች መኖራቸው ታውቆም እርምጃ የተወሰደባቸው አሉ።

ግብይቱ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ስርዓት ሲሆን ችግሩ ይቀረፋል። "

ነዳጅ ለማግኘት የመቸገር ጉዳይ በሀዋሳ ብቻ ሳይሆን በጎረቤት ሻሸመኔ፣ በሌሎችም ከተሞች ያለ ጉዳይ ነው።

እንደ ነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን መረጃ ከሆነ " በሀገር ውስጥ በቂ የሆነ የነዳጅ አቅርቦት አለ " ነገር ግን በክልል ከተሞች ያለው ነዳጅ ለማግኘት የመቸገር ጉዳይና የጥቁር ገበያው ነገር መፍትሄ የሚያሻው ነው።

@tikvah_eth_BOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ከቀናት በፊት የብልፅግና ፓርቲ የወረዳ አመራር በተገደሉበት ወቅት #ወንድማቸውን ጨምሮ ሌሎችም የመኪና አሽከርካሪዎች መገደላቸውን አንድ ቃላቸውን ለቪኦኤ ሬድዮ የሰጡ የከባድ መኪና አሽከርካሪ ተናግረዋል።

ከቀናት በፊት ከአዳማ ወደ አዋሽ በሚወስደው መንገድ ላይ በተከፈተ ተኩስ በአፋር ክልል በገቢ ረሱ የሓንሩካ ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኡመር ለማ መገደላቸውን የአፋር ክልል የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ማሳወቁ ይታወሳል።

ቃላቸውን የሰጡት የከባድ መኪና አሽከርካሪው፥ ጥቃቱ ወለንጪቱ አካባቢ መሰንዘሩን አመልክተው አቶ ዑመር ለማን ጨምሮ 7 ሰዎች ናቸው የተገደሉት ብለዋል።

" አሽከርካሪዎች ሰላማዊ መንገድ ነው ብለው በሰላም እየተጓዙ እያለ በአጋጣሚ በወለንጪቲ እንደውም ከድሮው የዘረፋ ቦታ በተለየ መልኩ በጣም ለወለንጪቲ ቅርብ ከ5 ኪ/ሜ ባልበለጠ ርቀት ውስጥ መጥተው ነው ዘረፋውንም አካሂደው አሽከርካሪዎችን ገድለው እንዳለ የነበረ ንብረት ዘርፈው የሄዱት።

ሰባት አካባቢ የሞቱ አሉ ከዛ መካከል በአጋጣሚ የአፋር ክልል የብልፅግና የወረዳ ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑ ገለሰብ ከነወንድማቸው ተገድለዋል፤ 5ቱ አሽከርካሪዎች ናቸው። የሞቱ አሽከርካሪዎች ቢያንስ የዜና ሽፋን አላገኙም፤ የተረፉ አሽከርካሪዎችም አሉ።

ጥቃቱ በተለያዩ ተሽከርካሪዎች ላይ ነው የተሰነዘረው አይሱዙ አለ፣ ሱኖትራክ ተሳቢ የሌላቸው አሉ፣ የቤት መኪኖች አሉ፣ ፒካፕ፣ ቦቴ አለ እንደውም ቦቴው በጥይት ተመቶ ነዳጅ ሲፈስ ነበር "

ከዚሁ ጥቃት ጋር በተያያዘ የገቢ ረሱ ዞን 3 ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሃሰን ዲን ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ማብራሪያ አቶ ኡመር ለማ አባታቸውን አዲስ አበባ አሳክመው ወደ ቤታቸው ሲመለሱ መገደላቸውን ገልጸዋል።

ጥቃቱ ምሽት ላይ መፈፀሙን ያስታወሱት አቶ ሃሰን ወለንጪቲ አካባቢ ባልታወቁት ታጣቂዎች በተከፈተው ተኩስ ነው አቶ ዑመር የተገደሉት ብለዋል።

እንደ ኃላፊው ገለፃ፥ የአቶ ዑመር ወንድም መሐመድ ለማ አብረው ሲገደሉ መኪና ውስጥ የነበሩት አባታቸውን ጨምሮ ሌላ ወንድማቸውን (ዓሊ ለማ) ጨምሮ ተርፈዋል።

" እዛ አካባቢ ያለውን ሰላም መጠበቅ እንዳለብንና መስራት እንዳለብን ነው የሚያሳወው " ያሉት አቶ ሃሰን " የኦሮምያ አመራሮችም አከባቢዎችን ቅኝት በማድረግ ዜጎች በሰላም ወጥተው እንዲገቡ የማድረግ ሁኔታን መፍጠር ይገባል በዚህ ላይ ተባብረን መስራት አለብን " ብለዋል።

ከጥቃቱ የተረፉት የአቶ ዑመር ወንድም ዓሊ ለማ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ በሰጡት ቃል፤ ጥቃት ያደረሱት 30 የሚጠጉ የቀድሞውን የመከላከያ ልብስ የሚመስል ዩኒፎርም የለበሱ ታጣቂዎች ናቸው ብለዋል።

አቶ ዑመር ለማ ባለትዳርና የ5 ልጆች አባት ነበሩ፤ የአቶ ዑመር እንዲሁም የወንድማቸው ስርዓተ ቀብር በአዋሽ ተፈፅሟል።

ጥቃት በተፈፀመበት የአዳማ - አዋሽ ቀጠና እጅግ የለየለት የወንጀል ተግባር በታጠቁ አካላት እንደሚፈፀም ሲገለፅ እንደነበር ይታወሳል።

በዚሁ መስመር ታጣቂዎች እንደሚንቀሳቀሱና ከተማዎች ውስጥ በመግባት ጭምር ሰላማዊ ሰዎችን መግደል፣ በየመንገዱ ሰላማዊ ሰዎችን እያገቱ ከፍተኛ ገንዘብ የመጠየቅ፤ በአጠቃላይ በቀጠናው ወጥቶ ለመግባት ከፍተኛ ስጋት የመፍጠር እንቅስቃሴ እንደሚያደርጉ በተደጋጋሚ ሲገለፅ ቆይቷል።

በሌላ በኩል፤ በዛው በኦሮሚያ ባለፈው ሳምንት ሚያዚያ 26 ምሽት ከአዲስ አበባ ወደ ባቱ - ሀዋሳ በሚወስደው ፈጣን መንገድ ላይ በዓለምጤና እና ቆቃ መሀል ዝርፊያ እና የመኪና ማቃጠል ተግባር መፈፀሙን የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደም በዚሁ መስመር ግድያን ጨምሮ የንብረት ዘረፋ ፣ መኪና ማቃጠል መፈፀሙ የሚዘናጋ አይደለም።

@tikvahethiopia
#EthioTelecom

ከዛሬ ጀምሮ በሃገራችን ሁሉም አካባቢዎች የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ብቻ የሚፈጸም በመሆኑ ለተግባራዊነቱ በሁሉም የነዳጅ ማደያዎች በቂ ዝግጅት ማድረጋችንን እየገለጽን፤

ውድ ደንበኞቻችን ነዳጅ ለመቅዳት ወደ ነዳጅ ማደያ ከማምራታችሁ በፊት በቅድሚያ የበኩላችሁን ቅድመ-ዝግጅት እንድታደርጉ ለማስታወስ እንወዳለን

⛽️ የቴሌብር አገልግሎት ተጠቃሚ ካልሆኑ ቴሌብር ሱፐርአፕን ከ onelink.to/75zfa5 በማውረድ ወይም *127# በመደወል ይመዝገቡ

⛽️ ከቴሌብር ጋር ከተሳሰሩ 20 ባንኮች በሞባይል ባንኪንግ፣ በቴሌብር ወኪሎች እና በኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት መስጫ ማዕከሎች ነዳጅ ለመቅዳት የሚያስፈልግዎን ገንዘብ ወደ ቴሌብር ሂሳብዎ ያስተላልፉ

⛽️ ለተጨማሪ ድጋፍ ወደ 127 ይደውሉ ወይም በጽሁፍ ወደ 126 ወይም የቴሌብር ማህበራዊ ገጾቻችን ጥያቄዎን ይላኩ

ማስታወሻ: የነዳጅ ክፍያዎን በቴሌብር ሲፈጽሙ ምንም አይነት ተጨማሪ የአገልግሎት ክፍያ አይጠየቁም

ለተጨማሪ መረጃ bit.ly/3V3wjPF
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ የ6ኛ እና 8 ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና የሚሰጥባቸውን ቀናት ይፋ አደርጓል።

የ8ኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 19 እና 20 እንዲሁም የ6ኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 26 እና 27 እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ቢሮው ከተማ አቀፍ ፈተናዎቹን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመስጠት ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን የገለፀ ዲሆን ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቹን የበለጠ ማዘጋጀት እንዲችሉ ከከተማና ክፍለ ከተሞች ጋር በጋራ በመሆን የሞዴል ፈተናዎችን እንዲሰጡ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

በ2015 ዓ.ም 75,100 የ8ኛ እንዲሁም 75,078 የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ከተማ አቀፍ ፈተናውን ይወስዳሉ።

@tikvahethiopia
#EOTC

የቅዱስ ሲኖዶስ የግንቦት የርክበ ካህናትጉባኤ ነገ ግንቦት 2 ቀን 2015  ዓ/ም ይከፈታል።

በአሁን ሰዓት የግንቦት 2015 ዓ/ም ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ መክፈቻ የጸሎት ሥነሥርዓት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በመካሔድ ላይ ነው።

ፎቶ ፦ የኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትፈለጋለች በኦሮሚያ ክልል በሸገር ከተማ ቡራዩ ክፍለ ከተማ አንዲት እንጀራ እናት ሁለት ልጆችን በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደሏ እየተፈለገች መሆኑን ፖሊስ ገልጿል። ስለጉዳዩ የቡራዩ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምርያ የወንጀል ምርመራ ክፍል ባልደረባ የሆኑት ዋና ሳጅን ቀነኒሳ ታደሰ ምን አሉ ? ዋና ሳጅን ቀነኒሳ ታደሰ ፦ " ወንጀሉ የተፈፀመው ቅዳሜ ሚያዝያ 28/2015 ዓ.ም. በከታ ወረዳ ልዩ ስሙ ሦስተኛ…
ፎቶ ፦ በሸገር ከተማ ፤ በቡራዩ ክፍለ ከተማ ቅዳሜ ሚያዝያ 28 ቀን 2015 ዓ/ም በከታ ወረዳ ልዩ ስሙ " 3ኛ ቡራዩ " በሚባል ስፍራ ሁለት ሕጻናትን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለችው ነጋሴ ከበደ የተባለችው ተጠርጣሪ መያዟ ተገልጿል።

ተጠርጣሪዋ የእንጀራ ልጆቿ የሆኑትን ሁለቱን ሕጻናት አንገታቸውን ቀልታ ፣ በተኙበት ብርድ ልብስ አልብሳ እሳት ለኩሳባቸው አምልጣ እንደነበርና ፍለጋው እየተካሄደ እንደነበር ይታወሳል።

ዛሬ ከቀኑ 10:30 ላይ " ሳንሱሲ " በሚገኝ ጫካ ውስጥ ራሷን ለማጥፋት ስትሞክር በተደረገው ክትትል በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋሏ ነው የተገለጸው።

Photo Credit : Hachalu Lachesa

@tikvahethiopia
#big5construct

የማይገኝ አጋጣሚ ለሁሉም የኢንዱስትሪ ባለሙያዎች !

ከግንቦት 10 እስከ 12፣ 2015ዓ.ም. በሚከናወነው ቢግ 5 ኮንስትራክት ኢትዮጵያ የንግድ ትርዒት ላይ በሚካሄዱ ኢንደስትሪ ተኮር ንግግሮች እና ውይይቶች ላይ በመሣተፍ ብቻ ነፃ የሲፒዲ ነጥብ ማግኘት እንደሚቻል ያውቃሉ?

ይመዝገቡ https://bit.ly/3oI8P6L

የቴሌግራም ቻናላችንን ለመቀላቀል መስፈንጠሪያውን ይከተሉ: https://t.iss.one/big5ethiopia
#NEBE

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፤ የትግራይ ክልልን ጨምሮ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ባልተካሄደባቸው አካባቢዎች እና አካባቢያዊ ምርጫን በ2016 ዓ.ም ለማካሄድ መታቀዱን ዛሬ አሳውቋል።

ቦርዱ ይህን ያሳወቀው የ2015 በጀት ዓመት ያለፉት 9 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበበት ወቅት ነው።

የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብሸት አየለ ፥ በተለያዩ ችግሮች ምክንያት በተወሰኑ ክልሎች በሚገኙ አካባቢዎች 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ አለመካሄዱን ገልጸዋል።

ይህንኑ ምርጫ ለማካሄድ በ2015 ዝግጅት ለማድረግ ታቅዶ እንደነበር ተናግረዋል።

ነገር ግን የአካባቢ ምርጫ ለማካሄድ ቢታቀድም አለመሳካቱን ገልጸው፣ እነዚህን ምርጫዎች በ2016 ለማካሄድ ቦርዱ ዕቅዱን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማቅረቡን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ፥ ባለፉት ወራት ከፖለቲካ ፓርቲዎች አሠራር ጋር በተያያዘ አንዳንድ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤ እንዳያካሂዱ በተለያዩ አካላት መከልከላቸውን ቦርዱ ማረጋገጡን እና አንዳንድ የፓርቲ አመራሮች ለእስር መዳረጋቸውን አቶ ውብሸት ገልጸዋል። ቦርዱ ለዚህ ችግር መፍትሔ ለመስጠት ሥራዎችን እየሠራ መሆኑን አመልክተዋል።

#ኢብኮ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ የፀጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ፥ ከሀገር ውጭ የሚገኙትን ፖለቲከኛው አቶ ልደቱ አያሌውን ፣ በቅርቡ ከልዩ ኃይል ጋር በተያያዘ በአማራ ክልል የተፈጠረውን አለመግባባት በስምምነት እንደፈታ የተነገረለት የምስራቅ አማራ ፋኖ አመራር ምሬ ወዳጆን ጨምሮ በሀገር ውስጥ በተደጋጋሚ ጊዜ በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ የሚዲያ ሰዎች እና በውጭ ሀገር ያሉ በርካታ የሚዲያ ሰዎችን " ህገ መንግስታዊ…
" ክስ ከተመሰረተብኝ እመለሳለሁ " - አቶ ልደቱ አያሌው

መንግሥት በ "ሽብር ወንጀል እጠረጥራቸዋል" ያላቸውን በውጭ ሀገር ያሉና ተላልፈው እንዲሰጡ ማዘዣ ካወጣባቸው ግለሰቦች መካከል አንዱ የሆኑት ጉምቱው ፖለቲከኛ አቶ ልደቱ አያሌው "ክስ ከተመሠረተባቸው" ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱ አሳውቀዋል።

አቶ ልደቱ እስካሁን ክስ እንዳልተመሠረተባቸው በጠበቃቸው እንደተነገራቸውና ክስ ከተመሠረተባቸው ግን ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመመለሱ ገልጸዋል።

ይህን የገለፁት ከቢቢሲ አማርኛ ጋር በነበራቸው ቃለምልልስ ነው።

ፖለቲከኛው አቶ ልደቱ አያሌው ምን አሉ ?

"...ከጠበቃዬ ጋር እየተነጋገርኩ ነው። እስካሁን ክስ አልተመሠረተብኝም። ዝም ብሎ በራድዮና በቴሌቪዥን ይነገራል እንጂ የቀረበ ክስ የለም። ክስ ሲመሠረት ነው የምሄደው።

ክስ ከመመሥረቱ በፊት መሄዴ ጥቅም የለውም። በጊዜ ቀጠሮ መጉላላት ነው እንጂ ምንም ፋይዳ የለውም። እስከዚያ ድረስ ሕክምናዬን እከታተላለሁ /አቶ ልደቱ ለልብ ህመም በአሜሪካ የህክምና ክትትል ላይ ናቸው/ ።

ክስ ሲመሠረት ዳኞቹ የሚቀጥለው ሕክምናዬ ድረስ እንድቆይ የሚፈቅዱ ከሆነ እቆያለሁ። የማይፈቅዱ ከሆነም የሕክምና ቀጠሮዬን አቋርጬ እሄዳለሁ። "

አቶ ልደቱ ስለ ሽብር ክስ...

" የሕክምና ቀጠሮ ስለነበረኝ ነው እንጂ መጀመሪያም የመጣሁት እዚህ ለመኖር አይደለም። በቅርብ ጊዜ ወደ አገሬ እመለሳለሁ ብዬ እያሰብኩ ነበር። የዘገየሁት ያልተቋጨ የሕክምና ቀጠሮ ስለነበረኝ ነው። የሽብርተኛነት ክስ ሲመጣ ካሰብኩት ጊዜ ፈጥኜ ነው የምሄደው አልኩ።

የሕግ ተፈላጊነት ካለ፣በሽብርተኛነት የመጠየቅ ጉዳይ ካለ፣እኔ ከፍ/ቤት ውሳኔ እና ጥያቄ ርቄ መኖር ስለማልፈልግ ነው ለመሄድ የወሰንኩት።

...አገሪቱ ካለችበት ሁኔታ አንጻር ተመልሼ ለመውጣት ችግር ሊገጥም ይችላል ብዬ ነው እስካሁን የዘገየሁት። አሁንም የሕክምና ቀጠሮ አለኝ። ግን የሕግ ተጠያቂነት ከመጣ ምንም ማድረግ አይቻልም።

የተከሰስኩበት ወንጀል በፍጹም ከእኔ ታሪክ እና ማንነት ጋር የማይሄድ ነው። ሥርዓቱ ደግሞ ይሄንን ያደረገበት የራሱ ምክንያት አለው። አንደኛው ምክንያት እንደዚህ ዓይነት ክስ ፈርቼ ወደ አገሬ እንዳልመለስ ለማድረግ ስለሆነ ይሄንን በፈቃደኛነት ለመቀበል ዝግጁ አይደለሁም።

እኔ ሰላማዊ ታጋይ ነኝ። ሁልጊዜም በሕግ ነው የምተማመነው። ካሁን ቀደምም አምስት ስድስቴ ታስሬ በፍርድ ቤት ነው ነጻ የሆንኩት። አሁንም በዚያ መንገድ ሄጄ የግድ ሥርዓቱን መጋፈጥ አለብኝ በሚል ነው የምመለሰው።

ማናችንም ላለመታሰር፣ ዋጋ ላለመክፈል የየራሳችን ምክንያት ይኖረናል። ትግል ሲባል ግን እነዚህን ሁሉ ነገሮች ጥሶ መከፈል የሚገባውን ዋጋ መክፈል ነው።

ወደኢትዮጵያ ሲገቡ ስለሚገጥማቸው ችግር...

" ስሄድ የሚገጥመኝ ችግር ቀላል ነው ብዬ አይደለም። ከባድ እንደሚሆን አምናለሁ። ያ ችግር ምናልባት ሕይወቴንም ጭምር የሚያሳጣ ሊሆን ይችላል።

ግን ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ፣ ሕዝቡ ያለበት ሁኔታ፣ ሰዎች በዚህ ደረጃ ዋጋ ለመክፈል ካልተዘጋጀንና ካልከፈልን ይለወጣል የሚል እምነት የለኝም። በእኔ ደረጃ ያለ ሰው ያን ዋጋ መክፈል እና ለትግሉ አርአያ መሆን አለበት ብዬ አምናለሁ።

ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ በፖሊስ ሊያዙ ስለሚችሉበት ሁኔታ...

" ልምዱ አለኝ። መታሰር የመጀመሪያዬ አይደለም። በዚህ ዓይነት ትግል ውስጥ ላለፉት 31 ዓመታት ቆይቻለሁ። ወደ 6 ጊዜ ስለታሰርኩ ለእኔ አዲስ ነገር አይደለም።

ከእኔ ጋር በመግለጫ የተጠቀሱ ግለሰቦች እየታደኑ እያተሰሩ እንደሆነ አውቃለሁ፤ ኤርፖርት የሚጠብቀኝ ፖሊስ እንደሚሆንና እንደምታሰር አውቃለሁ። ለዚህ የሥነ ልቦና ዝግጅት አለኝ።"

#ቢቢሲ

@tikvahethiopia