TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ከቀናት በፊት የብልፅግና ፓርቲ የወረዳ አመራር በተገደሉበት ወቅት #ወንድማቸውን ጨምሮ ሌሎችም የመኪና አሽከርካሪዎች መገደላቸውን አንድ ቃላቸውን ለቪኦኤ ሬድዮ የሰጡ የከባድ መኪና አሽከርካሪ ተናግረዋል።

ከቀናት በፊት ከአዳማ ወደ አዋሽ በሚወስደው መንገድ ላይ በተከፈተ ተኩስ በአፋር ክልል በገቢ ረሱ የሓንሩካ ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኡመር ለማ መገደላቸውን የአፋር ክልል የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ማሳወቁ ይታወሳል።

ቃላቸውን የሰጡት የከባድ መኪና አሽከርካሪው፥ ጥቃቱ ወለንጪቱ አካባቢ መሰንዘሩን አመልክተው አቶ ዑመር ለማን ጨምሮ 7 ሰዎች ናቸው የተገደሉት ብለዋል።

" አሽከርካሪዎች ሰላማዊ መንገድ ነው ብለው በሰላም እየተጓዙ እያለ በአጋጣሚ በወለንጪቲ እንደውም ከድሮው የዘረፋ ቦታ በተለየ መልኩ በጣም ለወለንጪቲ ቅርብ ከ5 ኪ/ሜ ባልበለጠ ርቀት ውስጥ መጥተው ነው ዘረፋውንም አካሂደው አሽከርካሪዎችን ገድለው እንዳለ የነበረ ንብረት ዘርፈው የሄዱት።

ሰባት አካባቢ የሞቱ አሉ ከዛ መካከል በአጋጣሚ የአፋር ክልል የብልፅግና የወረዳ ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑ ገለሰብ ከነወንድማቸው ተገድለዋል፤ 5ቱ አሽከርካሪዎች ናቸው። የሞቱ አሽከርካሪዎች ቢያንስ የዜና ሽፋን አላገኙም፤ የተረፉ አሽከርካሪዎችም አሉ።

ጥቃቱ በተለያዩ ተሽከርካሪዎች ላይ ነው የተሰነዘረው አይሱዙ አለ፣ ሱኖትራክ ተሳቢ የሌላቸው አሉ፣ የቤት መኪኖች አሉ፣ ፒካፕ፣ ቦቴ አለ እንደውም ቦቴው በጥይት ተመቶ ነዳጅ ሲፈስ ነበር "

ከዚሁ ጥቃት ጋር በተያያዘ የገቢ ረሱ ዞን 3 ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሃሰን ዲን ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ማብራሪያ አቶ ኡመር ለማ አባታቸውን አዲስ አበባ አሳክመው ወደ ቤታቸው ሲመለሱ መገደላቸውን ገልጸዋል።

ጥቃቱ ምሽት ላይ መፈፀሙን ያስታወሱት አቶ ሃሰን ወለንጪቲ አካባቢ ባልታወቁት ታጣቂዎች በተከፈተው ተኩስ ነው አቶ ዑመር የተገደሉት ብለዋል።

እንደ ኃላፊው ገለፃ፥ የአቶ ዑመር ወንድም መሐመድ ለማ አብረው ሲገደሉ መኪና ውስጥ የነበሩት አባታቸውን ጨምሮ ሌላ ወንድማቸውን (ዓሊ ለማ) ጨምሮ ተርፈዋል።

" እዛ አካባቢ ያለውን ሰላም መጠበቅ እንዳለብንና መስራት እንዳለብን ነው የሚያሳወው " ያሉት አቶ ሃሰን " የኦሮምያ አመራሮችም አከባቢዎችን ቅኝት በማድረግ ዜጎች በሰላም ወጥተው እንዲገቡ የማድረግ ሁኔታን መፍጠር ይገባል በዚህ ላይ ተባብረን መስራት አለብን " ብለዋል።

ከጥቃቱ የተረፉት የአቶ ዑመር ወንድም ዓሊ ለማ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ በሰጡት ቃል፤ ጥቃት ያደረሱት 30 የሚጠጉ የቀድሞውን የመከላከያ ልብስ የሚመስል ዩኒፎርም የለበሱ ታጣቂዎች ናቸው ብለዋል።

አቶ ዑመር ለማ ባለትዳርና የ5 ልጆች አባት ነበሩ፤ የአቶ ዑመር እንዲሁም የወንድማቸው ስርዓተ ቀብር በአዋሽ ተፈፅሟል።

ጥቃት በተፈፀመበት የአዳማ - አዋሽ ቀጠና እጅግ የለየለት የወንጀል ተግባር በታጠቁ አካላት እንደሚፈፀም ሲገለፅ እንደነበር ይታወሳል።

በዚሁ መስመር ታጣቂዎች እንደሚንቀሳቀሱና ከተማዎች ውስጥ በመግባት ጭምር ሰላማዊ ሰዎችን መግደል፣ በየመንገዱ ሰላማዊ ሰዎችን እያገቱ ከፍተኛ ገንዘብ የመጠየቅ፤ በአጠቃላይ በቀጠናው ወጥቶ ለመግባት ከፍተኛ ስጋት የመፍጠር እንቅስቃሴ እንደሚያደርጉ በተደጋጋሚ ሲገለፅ ቆይቷል።

በሌላ በኩል፤ በዛው በኦሮሚያ ባለፈው ሳምንት ሚያዚያ 26 ምሽት ከአዲስ አበባ ወደ ባቱ - ሀዋሳ በሚወስደው ፈጣን መንገድ ላይ በዓለምጤና እና ቆቃ መሀል ዝርፊያ እና የመኪና ማቃጠል ተግባር መፈፀሙን የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደም በዚሁ መስመር ግድያን ጨምሮ የንብረት ዘረፋ ፣ መኪና ማቃጠል መፈፀሙ የሚዘናጋ አይደለም።

@tikvahethiopia