TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#USA

ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቀዳሚ ስራቸው ዶክመንት የሌላቸውን / ሰነድ አልባ ስደተኞችን በብዛት ከሀገር ማስወጣት ነው ተብሏል።

የትራምፕ ዘመቻ ቃል አቀባይ ካሮሊን ሌቪት እንደገለፁት ትራምፕ በፕሬዚዳንትነት ስልጣናቸው ከሚወስዷቸው የመጀመሪያ እርምጃዎች መካከል አንዱ ዶክመንት የሌላቸው / ሰነድ አልባ ስደተኞችን በብዛት ለማስወጣት የገቡትን ቃል መፈጸም ነው።

ሌቪት ፥ ትራምፕ በአሜሪካ ህዝብ ዘንድ አስደናቂ የተባለ ድል ማስመዝገባቸውን ገልጸው " ይህ ድል ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳቸው የገቡትን ቃል እንዲፈጽሙ ' ትዕዛዝ ' እንዲሰጡ ያስችላቸዋል " ብለዋል።

ይህም ሰነድ አልባ ስደተኞችን በብዛት / በገፍ ወደ መጡበት ሀገር መመለስ (ማስ ዲፖርቴሽን) እንደሆነ ጠቁመዋል።

አንዳንድ ሚዲያዎች ይህ ሰነድ አልባዎችን በብዛት ከአሜሪካ የማስወጣቱ /ማስ ዲፖርቴሽን/ ተግባር የትራምፕ የመጀመሪያው ቀን ስራ ይሆናል ብለዋል።

ትራምፕ በምርጫ ዘመቻቸው ወቅት ሰነድ የሌላቸውን ሰዎችን በሚመለከት " ከአሜሪካ ምድር ጓዛቸውን አስይዘን ወደ መጡበት እንልካቸዋለን " ሲሉ ቃል ገብተው ነበር።

አንዳንድ ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙት ትራምፕ በስልጣን ዘመናቸው ቢያንስ ቢያንስ ከ15 እስከ 20 ሚሊዮን ሰነድ የሌላቸው ስደተኞችን ከአሜሪካ ለማስወጣት እቅድ አላቸው።

#TikvahEthiopia
#USA #massdeportation

@tikvahethiopia