TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Tigray

📞9167 👉 ICRC የአጭር የስልክ መስመር
📞0115527110 👉 የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ስልክ ቁጥር

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ፥ እስካሁ ከ300 ያላነሱ የመቐለ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከቤተሰቦቻቸው ጋር መረጃ እንዲለዋወጡ መደረጉን አስታውቋል።

የማህበሩ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ዶክተር ሰለሞን አሊ በክልሉ ከሚገኙ አለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ጋር በመተባበር በትግራይ ክልል የሚገኙ ተማሪዎችን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለማገናኘት እየተሰራ ያለው ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።

እስካሁን ድረስ መቐለ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ከ300 በላይ ተማሪዎችን ደህንነት የሚገልፅ የሰላምታ መልክቶች በመቀበል ለቤተሰቦቻቸው ማስተላለፍ መቻሉን ዶ/ር ሰለሞን ጠቁመዋል፡፡

በሚቀጥሉት ጊዚያት በክልሉ ውስጥ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ ተማሪዎች ያሉበትን ሁኔታ በተመለከተና የሰላምታ መልክቶችን በመቀበል ለቤተሰቦቻቸው የማድረስ ሂደቱ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ዶ/ር ሰለሞን የተማሪ ወላጆች ተረጋግተው በፅናትና በትዕግስት እንዲጠብቁ አሳስበዋል፡፡

በ9167 የአለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) የአጭር የስልክ መስመር ላይ የተማሪ ወላጆች ተጨማሪ ማብራሪያ መረጃ ማግኘት ይችላሉ ብለዋል። በተጨማሪ በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ስልክ ቁጥር 0115 52 71 10 እና በ 9167 መረጃ መጠየቅ ይችላሉ ሲሉ #ለአሃዱ_ኤፍ_ኤም 94.3 ሬድዮ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia