TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ማሳሰቢያ‼️

ወህዴግ በማህበራዊ ሚዲያ በቀን 19/03/2011 ዓ.ም #በወላይታ_ሶዶ ከተማ #ሠላማዊ_ሰልፍ እንደሚያደርግ እየገለፀ ያለ ቢሆንም የዞኑ አስተዳደር አሁን ያለውን #የፀጥታ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ፍቃድ ያልተሰጠ ስለሆነና ነባራዊ ሁኔታን በመገምገም ወደፊት የሚፈቅድ መሆኑ ታውቆ በተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮችም ሆነ አባላት የሚደረገው ቅስቀሳ ተገቢ ያለመሆኑን በመገንዘብ #ጥንቃቄ እንዲደረግ እናሳስባለን፡፡

©Wolaita ZONE Culture, tourisim and Governmental Communication Affairs Office
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለወገን ደራሽ ወገን ነው🔝

በዛሬው ዕለት #በወላይታ_ሶዶ_ከተማ በተካሄደው የወላይታ ዲቻ እና የሽረ ስሁል ጨዋታ ለጌዴኦ ተፈናቃዮች የእርዳታ ማሰባሰቢያ ስራዎች ሲካሄዱ ውለዋል። እቅስሴውን ያስተባበሩት የወላይታ ወጣቶች(የለጋ) ከየወላይታ ዲቻ ስፖርት ክለብ የደጋፊዎች ማህበር ጋር በመሆን ነው። መረጃውን ያደረሰን የወላይታ ዲቻ ስፖርት ክለብ የደጋፊዎች ማህበር ፕሬዘዳንት አንዱአለም እንደነገረን በዛሬው ውሎ ከ50ሺ ብር በላይ ተሰብስቧል። 9,111 ብር ወጣቶቹ በመንገድ ላይ ሆነው ከከተማው ህዝብ የሰበሰቡት ሲሆን፤ 41,025 ብር ደግሞ በስታዲየሙ ከተገኘው ደጋፊ የተሰበሰበ እንደሆነ አዱአለም ነግሮናል። ስራው ቀጣይነት እንደሚኖረውም ጨምሮ ነግሮናል። ከገንዘብ በተጨማሪም በቁሳቁስ የከተማው ነዋሪ ለጌዴኦ ተፈናቃዮች ድጋፍ ማድረጉን በከተማው የሚኖሩ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia