TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ድሬዳዋ‼️

የመልካም አስተዳደርና የሥራ  አጥነት መሠረታዊ ጥያቄዎች በፍጥነት ለመመለስ የሚያግዝ የ60 ቀናት ዕቅድ ተዘጋጅቶ እንቅስቃሴ መጀመሩን የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ ተናገሩ።

የድሬዳዋ አስተዳደርና የሐረሪ ክልል ፖሊስ ገለልተኛ ሆኖ አገር አቀፍ ለውጡን በሚያግዝ መንገድ ማዋቀር /ሪፎርም/ እንደሚያስፈልግ የፀጥታ ጊዜያዊ ኮሚቴ ሰብሳቢ ብርጋዲዬር ጄኔራል #ተስፋዬ_ወልደማርያም አስታውቀዋል፡፡

ዕቅዱ ሕዝብ #ብሶቱን የሚያሰማባቸውን 17 መሠረታዊ ጉዳዮች በመለየት  ሁሉን አቀፍ ምላሽ ለመስጠት መዘጋጀቱን ከንቲባው አቶ #ኢብራሂም_ዑስማን አስታውቀዋል፡፡

አመራሩ ከፖለቲካ ፣ከሰላምና ፀጥታ እንዲሁም ከልማትና ከመልካም አስተዳደር አኳያ የተጀመረውን እንቅስቃሴ ዳር ለማድረስ  መሥራት እንደሚገባውም አሳስበዋል፡፡

”በዕቅዱ መሰረት የተጀመሩ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ጭምር በማጠናቀቅ የሕዝቡን  የዓመታት ጥያቄ ምላሽ የሚያገኝበት ይሆናል። በየሥፍራው የተገነቡ የመሸጫና የማምረቻ ቦታዎች ለወጣቱ ይሰጣሉ” ብለዋል፡፡

ከሚመለከተው የበላይ አካል ጋር በመነጋገር ፖሊስ በአስቸኳይ ወደ ሪፎርም እንደሚገባም አስታውቀዋል፡፡

ኅብረተሰቡ ዕቅዱ ስኬታማ ለማድረግ ድጋፍና ትብብር ከማድረግ ጎን ለሰላምና #ለፀጥታ መረጋገጥ ግንባር ቀደም ኃላፊነቱን እንዲወጣ ከንቲባው ጠይቀዋል፡፡

የድሬዳዋ ጊዜያዊ የፀጥታ ኮሚቴ ሰብሳቢ የምሥራቅ ዕዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽን ብርጋዲዬር ጄኔራል ተስፋዬ ወልደማርያም በከተማዋ ሰሞኑን የተፈጠረው ሕገ-ወጥ ተግባራትና ሁከት መንስዔ አመራሩ የተሰጠውን ኃላፊነት ባለመወጣቱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አሁንም አመራሩ ባለበት ተጠያቂነትና ይቅርታ በመጠየቅ ዕቅዱን በማከናወን ሕዝቡን መካስ እንዳለበት አሳስበዋል። ”ሕዝቡን የማያገለግል አመራር መነሳት አለበት፤ በብጥብጥና ሁከት ውስጥ የተገኘ አመራር የማያስፈልግና በሕግ መጠየቅ ያለበት ይሆናል” ብለዋል፡፡

ኅብረተሰቡ ለውጥ በሂደት የሚመጣ  መሆኑን በመገንዘብ አገራዊ ለውጡን ለማደናቀፍና በሚፈለገው መንገድ አንዳይጓዝ የሚፈልጉ አካላትን በተቀናጀ መንገድ መከላከል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

ብርጋዲዬር ጄኔራል ተስፋዬ እንደተናገሩት በድሬዳዋም ሆነ በምሥራቁ የአገሪቱ ክፍል #አስተማማኝ ሰላምና ፀጥታ የሚያሰፍን ዕቅድ ተዘጋጅቶ  በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡

ሰሞኑን በድሬዳዋ በተፈጠረው ሁከትና ነውጥ በማራገብ ሂደት #ፖሊስና #አድማ_በታኝ አሉበት፤ ይህም በፖሊስ ውስጥ መሠረታዊ ሪፎርም እንደሚያስፈልግ ያመለክታል ብለዋል።

በመሆኑም የድሬዳዋ አስተዳደርም ሆነ የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽኖች ውስጥ ሥር ነቀል ለውጥ ማድረግና የኅብረተሰቡን ሰላምና ፀጥታ በአስተማማኝ መንገድ መጠበቅ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ምንጭ፦ ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia