TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኮኮሜሎን

ካለፈው የታሕሳስ ወር አንስቶ በተለያዩ የውጭ ሀገራት ያሉ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች እና የግብረሰዶማውያን እንቅስቃሴን የሚቃወሙ አካላት "ኔትፍሊክስ" እንዳይታይ የአድማ ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ።

"ኔትፍሊክስ" ላይ የአድማ ጥሪ እያደረጉ ያሉት ባለፈው ዓመት (እኤአ) መጨረሻ ለእይታ በበቃ በአንድ የልጆች ፊልም ላይ #ግብረሰዶምን ለማስፋፋት ዓላማ ያለው ትዕይንት አለበት በሚል ነው።

ኮኮሜሎን ሌን (CoComelon Lane) በተሰኘው የልጆች ፊልም ኢፒሶድ ላይ አንድ ህፃን ልጅ የዳንሰኛ አጭር ቀሚስ ለብሶ ሲጨፍር መታየቱ ከፍተኛ ቁጣን የቀሰቀሰ ሲሆን ተቺዎች ይህ የተደረገበትን መንገድ "መጥፎና ሰይጣናዊ" ሲሉ ነው የገለጹት።

CoComelon lane ለልጆች የተሰራ የNetflix ተከታታይ ፊልም ነው። በኃላም ከ1 ወር በፊት በዩትዩብ ላይ ተጭሮ በሚሊዮኖች ታይቷል።

በዚሁ ፊልም በሲዝን 1፤ ኢፒሶድ 8 ላይ አንድ ኒኮ የተባለ ህፃን ልጅ (2 አባቶች እንዳሉት ተደርጎ የተገለፀ-ይህ ግብረሰዶማውያን አባቶች እንዳሉት የሚያሳይ ተደርጎ ተወስዷል) ከቤተሰቦቹ ጋር ለሚነሳው ፎቶ ምን መልበስ እንዳለበት ለመወሰን ተቸግሮ ይታያል።

በዚህም ወቅት የኒኮ አባቶች ተደርገው የተሳሉት ሁለቱ ገፀባህርያት " ስለ አንተ የምናውቀው ነገር ቢኖር ተነስተህ መደነስ እንደምትወድ ነው " እያሉ ይዘፍናሉ።

ከዚያም ኒኮ የዳንሰኛ አጭር ቀሚስ ለብሶ እና ዘውድ ከአናቱ ላይ አድርጎ መደነስ ይጀምራል።

የኒኮ አባት ተብሎ ከተገለፁት አንዱ፤ " ምን መምረጥ እንዳለብህ እርግጠኛ ካልሆንክ ማድረግ የምትፈልጋቸውን ነገሮች ሁሉ አስብ። አንተ እራስህን ብቻ ሁን " እያለ ይዘፍንለታል።

ከዚያም ኒኮ "እኔ ራሴን ብቻ ልሁን?" ብሎ ይጠይቃል ካዛም አባት ተብየው ገፀባህሪ " አዎ! " ሲል ይመልስለታል።

ይህ ንግግር ህፃኑ ልጅ "የማንም ተፅእኖ ሳይኖርብህ #በፈለከው_መንገድ እራስህን ሁን" የሚል ይዘት ያለው መልዕክት ለማስተላለፍ እንደሆነ ጉዳዩ ያሳሰባቸው ተቆርቋሪች ይገልጻሉ።

ትዕይቱን "ጥፎና ሰይጣናዊ" ሲሉም ገልጸው ዋነኛው አላማው ህፃናትን ማበላሸት፣ ምንም በማያውቁ ህፃናት ላይ ግብረሰዶምን ማስፋፋት ነው ብለዋል።

የግብረሰዶማውያን እንቅስቃሴና ሰዎቹን አጥብቀው የሚያወግዙት እነዚህ ተቆርቃሪዎች፤ "ትዕይንቱ ህፃናት በለጋ እድሜያቸው ስለግብረሰዶም እና ስለፆታ ማስቀየር "እንዲዘጋጁ" እያደረገ የሚሄድ ነው ብለውታል።

በዚህ ምክንያት ይህንን ለህፃናት እንዲታይ እያሰራጨው "ኔትፍሊክስ"ን ሰዎች እንዳያዩ የአድማ ጥሪ እያቀረቡ ናቸው።

ምንም እንኳን ፊልሙ በህዳር ወር ውስጥ የወጣ ቢሆን ከወጣበት ጊዜ አንስቶ ተቆርቋሪዎች ወላጆች ልጆቻቸውን ከመሰል አደገኛ ይዘት ካላቸው መልዕክቶች እንዲጠብቁ ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ።

ይህ "CoComelon" የተባለውና ለህፃናት በተለያዩ ርዕሶች እየተዘጋጀ የሚቀርበው ካርቱን ፊልም በዓለም አቅፍ ደረጃ ብዙ እይታ ያለው ነው። ብዙ ወላጆችም ለልጆቻቸው ይከፍቱላቸዋል።

ወላጆች ዘመኑ ያለበትን ሁኔታ በመረዳት ልጆች እንዲያዩ የሚያደርጉትን ማንኛውንም ነገር በቅድሚያ መገምገም፣ ጥሩነው መጥፎ፣ ከጀርባ ምን ይዟል የሚለው መመርመር አለባቸው። ዝም ብሎ ልጅ ስላስቸገረ ስልክ መስጠትንም ተገቢ አይደለም።

ከዚህ ባለፈ ልጆች በሃይማኖት ተኮትኩተው ፣ የማህበረሰቡን ባህል፣ ስርዓት አክብረው በትምህርታቸው፣ በሃይማኖታቸው ጠንካራ ሆነው እንዲያድጉና እንዲኖሩ በተገቢው አቃጣጫ መምራት ይጠበቅባቸዋል።

ኢትዮጵጵያውያን የቴክ ሰዎችም የሀገራችን ህፃናት ወደሌላ እንዳይሳቡ በሀገር ባህል፣ ስርዓት የተቀረፁ የማስተማሪያ ካርቱን ፊልሞችን በብዛት ማዘጋጀት አለባቸው። #ቲክቫህ

@tikvahethiopia