TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ከ 'አፍሪካ ህብረት' የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ በ6 ሚሊየን 50 ሺህ ዶላር የምዝበራ ሙከራ የተከሰሱት እነ ቀሲስ በላይ የጠየቁት ዋስትና ውድቅ ተደርጓል። ጥያቄውን ውድቅ ያደረገው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው። ከምዝበራ መኩራው ጋር በተያያዘ የተከሰሱት ፦ 1ኛ. ቀሲስ በላይ መኮንን፣ 2ኛ. በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ የተሰማራው እያሱ…
#Update

እነ ቀሲስ በላይ ማረሚያ እንዲወርዱ ታዘዘ።

ከአፍሪካ ሕብረት ሒሳብ የ6 ሚሊየን 50 ሺህ ዶላር የምዝበራ ሙከራ ጋር ተያይዞ የተከሰሱት እነ ቀሲስ በላይ መኮንን ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ ፍርድ ቤት አዟል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ተከሳሾች ማረሚያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ አዟል።

ዛሬ ፦
1ኛ ቄስ በላይ መኮንን፣
2ኛ በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ የተሰማራው ኢያሱ እንዳለ ወ/መስቀል፣
3ኛ በኮሚሽን ሥራ ላይ የተሰማራው በረከት ሙላቱ ጃፋር ችሎት ቀርበው ነበር።

4ኛ አለምገና ሳሙኤል ዲንሳ
5ኛ የኒሞና ንግድ ሥራ ኃላ.የተ.የግል ማኅበር ሥራ አስኪያጅ አበራ መርጋ ተስፋዬ ዛሬም ፍርድ ችሎት #አልቀረቡም

ችሎት የቀረቡ ከ1ኛ - 3ኛ ተከሳሾች የወንጀል ድርጊት መፈጸማቸውንና አለመፈጸማቸውን የማረጋገጫ ጥያቄ በፍ/ ቤት ተጠይቀው " ወንጀሉን አልፈጸምንም " ሲሉ የዕምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ዐቃቤ ሕግ ምስክሮች እንዲሰሙለት ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ፍ/ቤቱ የምስክሮችን ቃል ለመስማት ለሰኔ 26 እና 27/2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾችን በሚመለከት ፖሊስ ፦
° 4ኛ ተከሳሽ ይኖሩበታል የተባለው ቦታ የፀጥታ ችግር እንዳለ ገልጾ፤
° 5ኛ ተከሳሽ በአድራሻቸው አለመገኘታቸውን ገልጾ ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጠው በጽሑፍ ጠይቋል።

ፍርድ ቤትም ፖሊስ 4ኛው ተከሳሽ ያሉበት ቦታ የፀጥታ ችግር ስለመኖሩ ማረጋገጫ እንዲያቀርብ አዟል።

5ኛው ተከሳሽ የወረዳው ነዋሪ መሆናቸው ወይም አለመሆናቸውን ከወረዳው ማረጋጋጫ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

#FBC

@tikvahethiopia