#ELPJC
" ... የሀገራችንን የፖለቲካ ችግሮችን የአመለካከት ልዩነቶችንና ስብራቶችን እርስ በርስ በመገዳደል ለውጥ ማምጣትና ማስተካከል አይቻልም " - ምክር ቤቱ
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መገለጫ በአቶ ግርማ የሺጥላ ላይ የተፈፀመውን ግድያ እንደሚያወግዝ እና በደረሰባቸውም አሰቃቂ ሞት በእጅጉ ማዘኑን ገልጿል።
ምክር ቤቱ " የሀገራችንን የፖለቲካ ችግሮችን፣ የአመለካከት ልዩነቶችንና ስብራቶችን እርስ በርስ በመገዳደል ለውጥ ማምጣትና ማስተካከል አይቻልም " ብሏል።
" ሥር የሰደዱ ግጭቶች እንኳን ቢሆኑ በአመጽ ሳይሆን በመነጋገር፣ በመወያየት፣ በመግባባትና በመደማመጥ፣ እንዲሁም በመተባበር ብቻ መፈታት ይኖርባቸዋል " ሲልም አስገንዝቧል።
በአቶ ግርማ ላይ የተፈፀመውን ግድያ በጽኑ እንደሚያወግዝ የገለፀው ምክር ቤቱ መንግስት ይህን አስነዋሪ ተግባር የፈጸሙ አካላትን በአፋጣኝ በቁጥጥር ስር በማዋል ተገቢውን የህግ ተጠያቂነት እንዲያረጋግጥ ጠይቋል።
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia