TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አዲስ አበባ⬆️

"አፍሪ ሄልዝ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ከአዲስ አበባ ጤና ጥበቃ ቢሮ እንዲሁም ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመሆን ከአስሩ ክ/ከተሞች ከተውጣጡ 1000 ለሚሆኑ አረጋዊያን በዘውደቱ ሆስፒታል #ነፃ የቅድመ ምርመራና የህክምና አገልግሎት የተሰጣችው ሲሆን #እኔም በዚህ ተግባር ውስጥ በመሳተፊ ተደስቻለሁ። ሌሎቻሁም በተለይዩ በጎ ተግባራት #እንድትሳፉ ጥሪዬን አቀርብላችሃለሁ።"

©ዶክተር አሚር አማን(የፌስቡክ ገፅ)
@tsegabwolde @tikahethiopia
#update በአዲስ አበባ ከተማ እየተደረገ ያለው አፈሳ አነጋጋሪ ሆኗል። በርካታ ቤተሰቦች ልጆቻቸው እንደታሰሩባቸው እየጠቆሙን ይገኛሉ። ስለጉዳዩም መንግስት የሰጠው ማብራሪያ የለም።

በሌላ በኩል የፊልም ዳይሬክተሩ ያሬድ ሹመቴም ለእስር የዳርጎ እንደነበር በፌስቡክ ገፁ ላይ ገልጿል። "ፖሊስ በተሳሳተ መረጃ እና በግብታዊነት በተለያዩ ቦታዎች #ንፁኃንን እያሰረ ስለመሆኑ በቂ መረጃ አለኝ ብሏል።" #እኔም የዚህ ድርጊት ሰለባ ሆኛለሁ ያለው ያሬድ ሹመቴ እርዳታ ከሚያስተባብሩ ወጣቶች መሀል አንዱ የፖሊስን አዛዥ ፎቶ አንስተሀል በሚል ክስ ያስተባበርከው አንተ ነህ ተብዬ ለ 5 ሰዓታት ያህል ታስሬ ተፈትቻለሁ ሲል በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ላይ ፅፏል።

የኢትዮጵያ መንግስት ስለሰሞኑን የአዲስ አበባ ጉዳይ የሚሰጠው ማብራሪያ ካለ ተከታትዬ አቅርብላችኋለሁ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
8 ቀን ብቻ ቀረው! #እንገናኝ

የዚህ ገፅ ባለቤቶች ሁላችሁም እንደሆናቹ ታውቃላችሁ። ላለፉት አመታት ከተቸገረው ጋር ስትቸገሩ የቆያችሁ፣ በየቦታው ሰላም ሲደፈርስ ቁጭ ባላችሁ ስትጨነቁ ስታድሩ የቆያችሁ፣ እውነተኛና በአይናቹ ያያችሁትን የተረጋገጠ መረጃ ለህዝብ ስታደርሱ የቆያችሁ፣ የታመሙትን #ስታሳክሙ የቆያችሁ፣ በሀዘን ወቅት #ብሄር እና #ዘር ሳትለዩ ስለሰው ልጅ ሁሉ ስታለቅሱ የነበራችሁ፣ ለሀገራችሁ ሰላም መሆን የበኩላችሁን ድርሻ ስትወጡ የቆያችሁ፣ ለመልካም ነገሮ ቀድማችሁ ስትደርሱ የነበራችሁት እናተው ናችሁ!! አዎን ክብር ይገባችኃል!! በሰውነት ጥላ ስር ያሰባሰብን፤ በልዩነቶቻችን የምንከባበርበት፤ በንግግር ችግሮችን የምንፈታበት፤ ጥላቻን የምንፀየፍበት፤ ለሀገር ሰላም ቅድሚያ የምንሰጥበት TIKVAH-ETH #ቤታችን ከተመሰረተ እንሆ ሁለተኛ አመቱን ሊያከብር ሀምሌ 21 ቀጠሮ ይዟል። የዚህ ገፅ ባለቤት #እኔም ነኝ የምትሉ ሁሉ ይህ ቀን የናተ ነውና እሁድ ሀምሌ 21 በአበበች ጎበና ሕፃናት እንክብካቤ እና ልማት ድርጅት ተገኙ፤ ከእናታችሁም #ምርቃት ተቀበሉ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
6 ቀን ቀረው! #እንገናኝ

የዚህ ገፅ ባለቤቶች ሁላችሁም እንደሆናቹ ታውቃላችሁ። ላለፉት አመታት ከተቸገረው ጋር ስትቸገሩ የቆያችሁ፣ በየቦታው ሰላም ሲደፈርስ ቁጭ ባላችሁ ስትጨነቁ ስታድሩ የቆያችሁ፣ እውነተኛና በአይናቹ ያያችሁትን የተረጋገጠ መረጃ ለህዝብ ስታደርሱ የቆያችሁ፣ የታመሙትን #ስታሳክሙ የቆያችሁ፣ በሀዘን ወቅት #ብሄር እና #ዘር ሳትለዩ ስለሰው ልጅ ሁሉ ስታለቅሱ የነበራችሁ፣ ለሀገራችሁ ሰላም መሆን የበኩላችሁን ድርሻ ስትወጡ የቆያችሁ፣ ለመልካም ነገሮ ቀድማችሁ ስትደርሱ የነበራችሁት እናተው ናችሁ!! አዎን ክብር ይገባችኃል!! በሰውነት ጥላ ስር ያሰባሰብን፤ በልዩነቶቻችን የምንከባበርበት፤ በንግግር ችግሮችን የምንፈታበት፤ ጥላቻን የምንፀየፍበት፤ ለሀገር ሰላም ቅድሚያ የምንሰጥበት TIKVAH-ETH #ቤታችን ከተመሰረተ እንሆ ሁለተኛ አመቱን ሊያከብር ሀምሌ 21 ቀጠሮ ይዟል። የዚህ ገፅ ባለቤት #እኔም ነኝ የምትሉ ሁሉ ይህ ቀን የናተ ነውና እሁድ ሀምሌ 21 በአበበች ጎበና ሕፃናት እንክብካቤ እና ልማት ድርጅት ተገኙ፤ ከእናታችሁም #ምርቃት ተቀበሉ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኦገት.pdf
379.8 KB
#እኔም_የዕርቅ_ሀሳብ_አለኝ

#ኦገት (የሀላባ ብሔረሰብ ባህላዊ የግጭት አፈታት ሥርዓት)

አዘጋጅ :- ዬጎሬ ዳቆሮ ዲዶ

- የሀላባ ብሔረሰብ ባህላዊ የእርቅ ሥርዓት ኦገት ሲባል ይህ የዳኝነት ስርዓት ከዝቅተኛዉ የአስተዳደር እርከን ከሆነው ‹‹ቦኪ ኦገት›› (የቤተሰብ ሸንጎ) እስከ ከፍተኛው እርከን ‹‹ሀላቢ ኦገት›› ይደርሳል፡፡

- በሀላባ ባህላዊ የአስተዳደር ስርዓት አንድ ማዕከላዊ ስልጣን የለም፡፡ በየደረጃዉ የራሱ ስልጣን እና ኃላፊነት ያለዉ የአስተዳደር እርከን አለ፡፡

- ‹‹ጎጎቲ ኦገት›› ሀላባ ዉስጥ ከሚደረጉ የኦገት አይነቶች አንዱ ሲሆን ይህ ኦገት ሀላባን ከአጎራባች ብሔረሰቦች ጋር የሚያስተሳስር የኦገት አይነት ነዉ፡፡ በዚህ ጠቅላላ ሸንጎ ላይ ከሀላባ አጎራባች ህዝቦች ጋር የድንበር ጉዳዮችንና የድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን፣ የጋራ ሀብትን በሚመለከትና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ከጋራ ስምምነት የሚደረስበት ነዉ፡፡

- ከሀላባ ብሔረሰብ ባህላዊ የግጭት አፈታት ስርዓት (ኦገት) ተግባራት ዉስጥ አንዱ ‹‹ጉምጉማ›› ነዉ፡፡ ጉምጉማ ማለት የኦገቴዉ ቆርቶዎች ጥፋተኛዉ ከተለየ በኋላ የቅጣት ዉሳኔ ላይ ከሸንጎዉ ተሳታፊዎች መካከል አስተያየት የሚቀበሉበት ስርዓት ነዉ፡፡

- በአሁኑ ወቅት ኦገቴ ዘመናዊዉን የህግ ስርዓት በበጎ ጎን የሚያግዝ ስሆን ጉዳዮችን ከፍርድ ቤት በመዉሰድ በሴራዉ መሰረት እየፈታም ይገኛል።

- ከዘመናዊዉ የህግ ስርዓት ጋር አብሮ ስለማይሄድ ተፈጻሚነታቸዉ ከቀሩ ባህላዊ የቅጣት አይነቶች መካከል አንዱ ያዩ (ማህበረሰባዊ ማግለል) ነዉ፡፡ ምንም እንኳን ዓላማዉ ጥፋተኛዉን ለሴራዉ ተገዢ እንዲሆን ማድረግ ቢሆንም ከሰብዓዊ መብት አንጻር ግን ገደብ የሚጣልበት ሆኗል፡፡

(በPDF የተያያዘውን ፋይል ያንብቡ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ኦገት.pdf
የአፋር ባህላዊ እርቅ (1).pdf
267.3 KB
#2

#እኔም_የዕርቅ_ሀሳብ_አለኝ !

የአፋር ህዝብ ባህላዊ የዕርቅ ሥርዓት ፦

አዘጋጅ፦ ሩት ኃይሌ

- የአፋር ማህበረሰብ እንቅስቃሴው በዳጉ የተደገፈ ነው። ይህ ፈጣንና እውነተኛ የመረጃ ልውውጥ መንገድ በማህበረሰቡ የሚፈጠርን ችግር ወይም ግጭት በቶሎ ወደ ሽማግሌዎች እንዲደርስ ያስችላል፡፡

- በአፋር ባህላዊ እርቅ ውስጥ የፍትህ ማስከበርን ብቻ ሳይሆን የምንመለከተው ቀድመው ወደ ነበሩበት መልካሙ ግንኙነት እንዲመለሱ የሚረዳ የእርቅ ሥርአት መሆኑን ነው።

- በአፋር ማህበረሰብ የተለያዩ ጎሳዎች ቢኖሩም ነገር ግን የባህላዊዉ የዕርቅ ትግበራና ቅጣቶች ወይም የካሳ ክፍያዎች እንዲሁም ወደ ሽማግሌዎች ቀርበው የሚታዩት ግጭቶች ተመሳሳይነት ያላቸው ናቸው። ስያሜውም ከአንዱ ዞን ወደ ሌላ ዞን ስንሄድ የተለየ ነው።

በዚህ ጹሑፍ የተዳሰሱት የእርቅ ሥርዓቶች፦

#ቢሉ፡- ከፍተኛ ግጭት ወይም ነፍስ ማጥፋት የሚሸመገልበት ባህላዊ የእርቅ ስርአት ነው፡፡

#ኢረና፡- በዚህ ሽምግልና በሰው ልጅ በየእለት እንቅስቃሴ የሚገጥመውን ጨምሮ ስርቆትም በዚህ ይዳኛል።

#መብሎ፡- ከፍተኛ ግጭት ወይም ነፍስ ማጥፋት የሚሸመገልበት ባህላዊ የእርቅ ስርአት ነው፡፡ በዚህ የእርቅ ስርአት የሰው አብሱማ ማለትም ለሌላ የታጨችን ሴት ማግባት ከነፍስ ግድያ እኩል ነው የሚታየው የካሳ ክፍያውም ተመሳሳይ ነው፡፡

#ኢዶሊና፡- ይህ የእርቅ ሥርዓት ከኢረና ጋር ትግበራውም የቅጣቱም አይነቶች እንዲሁም ግጭቶቹ ተመሳሳይ ናቸው፡፡

- የባህላዊ የእርቅ መንገዳችን ከፍርድ እና ከካሰ ይልቅ ሰዎች ላይ ያተኮረ እና ግጭት ውስጥ የገቡት ሰዎች ቀድሞ ወደነበራቸው ሰላማዊ ግንኙነት እንዲመለሱ የሚሰራ የእርቅ መንገድ ነው። በተጓዳኝም ካሳ ክፍያን በመፈጸም ፍትህን ከሰላሙ ጎን ለጎን የሚሰራ ነው፡፡

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የአፋር ባህላዊ እርቅ (1).pdf
ሙከጀላ በኤደን ገስላሴ.pdf
665.6 KB
#3

#እኔም_የዕርቅ_ሀሳብ_አለኝ

ሙከጀላ ባሕላዊ የዕርቅ ስርዓት በድሬዳዋ ማህበረሠብ

አዘጋጅ፦ ኤደን ገ/ስላሴ

በድሬዳዋ ሙከጀላ የሚባል የቀደመ ባሕል አለ፡፡ ሙከጀላ በማህበረሰቡ መካከል ለሚፈጠረ ማንኛውም ግጭትም ሆነ አለመግባባት በዛፍ ጥላ ሆኖ የሚመከርበት ቀደምት ባህል ነው፡፡

የዕርቁ ሂደት የሚካሔድበትን ቀንና ቦታ የሚመርጡት ማኅበረሰቡ የመረጣቸው፤ ትልቅ ቦታ በሚሰጣቸውና በሚከበሩ ትልልቅ አባቶች
ነው፡፡ የዕርቅ ሥርዓቱም የሚካሄደው በአካባቢው በሚገኘው ሙከጀላ በተባለ የዛፍ ጥላ ስር ነው፡፡

በባህሉ መሠረት ሽማግሌዎች ቀን እና ቦታ በቆረጡበት በሠአቱ ይገኛሉ፡፡ ይህም ሠዓትን የማክበር ልምድ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ የማህበረሰቡ ልምድ እና ባህል ነው፡፡

የተፈፀመው ጥፋት ተመጣጣኝ ነው ተብሎ ከታመነ ይቅር ለፈጣሪ ተባብለው እንዲያልፉት ቢደረግም በዚህ ሂደት ውስጥ ግን ጥፋቱ ከባድ ሆኖ ከተገኘ በመጀመሪያ በዳይ እግር ስር ወድቆ ይቅርታ ይጠይቃል፡፡

ከዚህ በኋላ አላጠፋም ፣ እታረማለው፣ ካሣዬንም እከፍላለው በማለት በአባቶች ፊት መሃላ ይፈፅማል፡፡ ተከሳሽም የሚከፍለው ካሣ መጠን በታዛቢዎች ፊት ለተበዳይ በግዜውና በሠዓቱ አንዲሰጥ ይወሰናል።

ባህላዊ የዕርቅ ሥርዓት ፍትህ እንዲገኝ ትልቅ አስተዋፅኦ የሚያደርገው እውነት ላይ የተመሠረተ በመሆኑ ነው፡፡ ዘርን፣ ሀይማኖትን፣ ፆታን፣ ሀብትን እና ሌሎች ልዩነቶችን ሳያደርግ ሚዛናዊ የሆነ ዳኝነት ስለሚሰጥ የባህላዊ ዕርቅ ሥርዓት ፍትህን ያስገኛል፡፡

ሙከጀላ በፊት ላይ ከፍተኛ ተቀባይነት የነበረው ቢሆንም አሁን ላይ ግን ይህ ስርዓት ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ወደ መረሳት ላይ ደርሷል፡፡ ይህ ባህል አለ እንኳን ቢባል በጣም በተወሰኑ ቦታዎች ላይ ነው፡፡

📁 ሙሉ ጹሑፉን ከላይ ተያይዟል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሙከጀላ በኤደን ገስላሴ.pdf
ኔሞ የሽናሻ_ታምሩ ዳኘው.pdf
305.2 KB
#4

#እኔም_የዕርቅ_ሀሳብ_አለኝ

''ኔሞ'' የሽናሻ ብሔረሰብ ባህላዊ የዳኝነት ስርዓት

አዘጋጅ: ታምሩ ዳኘው

" ኔሞ " ሽናሾች የሚመሩበት፣ የሚተዳደሩበት፣ እና ፍትህ የሚያገኙበት የህይወታቸው አንድ አካል ነው። የሺናሻ ብሄረሰብ በውስጡ ከ16 በላይ ንዑሳን ጎሳዎች ሲኖሩት እነዚህ ጎሳዎች ለኔሞ ስርዓት እንዲያመች ሆነው በሶስት ይከፈላሉ።

እነዚህም ጎሳዎች በብሄረሰቡ ባህል መሰረት “ሦስት ጉልቻ” ተብለው ይጠራሉ። ሦስቱ ጎሳዎች ዶዎ፣ ኢኖሮ፣ እና ኢንዲዎ ይባላሉ። ከእነዚህ ሶስቱ ጉልቻዎች አንዱ እንኳን ቢጎድል የኔሞ ስርዓትአይከወንም።

የቦሮ-ሽናሻ ብሄረሰብ ባህላዊ የፍርድ አሰጣጥ ሂደቶች አራት ደረጃዎች አሉት። እነዚህም፦

#ቡራ፦ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ የሚሰጥበት “ቡራ”በመባል ይታወቃል:: ቡራ አንድ ሽማግሌ ብቻውን ሆኖ የሚፈርድበት የቤተሰብ ባህላዊ ችሎት ነው።

#ኔማ፦ ሁለተኛ ደረጃ ፍርድ የሚሰጥበት የዳኝነት ክፍል”ኔማ” ይሰኛል። በዚህኛው ደረጃ ሦስት ሽማግሌዎች ግራናቀኝ አይተው ፍርድ ወይም ፍትህ ይሰጣሉ ተብሎ ይታመናል።

#ፄራ፦ ሶስተኛው የዳኝነት ክፍል ወይም ችሎት “ፄራ” ይባላል::ይህ ባህላዊ ችሎት የሚመራው በአንድ ባህላዊ ሹም ዳኛ ነው። በዚህ ክፍል ኔማ ችሎት መፍታት ያልቻለው ጉዳይ በጥልቀት ይታያል።

#ፋላ፦ ይህ በሺናሻ የመጨረሻ ወይም ከፍተኛ የዳኝነት አካል ነው፡፡

የሽናሾች ባህላዊ የኔሞ ስርዓት ዘመናዊውን ዳኝነት እጅጉን የማገዝ አቅም አለው። በአመክንዮአዊነቱ (ምክንያታዊነቱ) ዘመናዊ አስተሳሰብንና ፍትህን በሚዛናዊነት አስተናግዶህብረተሰቡ በሰላም ተሳስቦ መኖር እንዲችል አስተዋፅኦውወደር የሌለው በመሆኑ ትልቅ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ባህላዊ እሴት ነው።

📁 ሙሉ ጹሑፉን ከላይ ተያይዟል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ኔሞ የሽናሻ_ታምሩ ዳኘው.pdf
ዘወልድ.pdf
403.7 KB
#5

#እኔም_የዕርቅ_ሀሳብ_አለኝ

#ዘወልድ (የራያ ቆቦ ማህበረሰብ ባህላዊ የእርቅ ስርዓት)

አዘጋጅ፦ ዮሐንስ ቢሰጥ

እንደ አሁኑ ዘመናዊ የፍትህ ስርዓት ባልሰፈነበት ጊዜ በራያ አካባቢ የሚኖሩ ማህበረሰቦች የአካባቢያቸውን ባህል መሰረት በማድረግ ህግ አውጥተው ይተዳደሩና በመረጧቸው ሽማግሌዎች ይዳኙ ነበር ፡፡

- የዘወልድ ሽማግሌዎች የዕርቅ ሥነ-ስርዓት ከጠፋው የሰው ልጅ ህይወት ተጨማሪ የአካልና የህይወት እንዲሁም የንብረት ጉዳት እንዳይደርስ የመከላከል ስራ ይሰራሉ፡፡

- የሽምግልና ሂደቱን የሚመሩት አባቶች የሚመረጡት በአካባቢው ማሕበረሰብ ሲሆን መስፈርቱም አርቆ አሳቢነት፣ ታማኝና ሐቀኛ የሆኑ፣ የችግር ቋጠሮ የመፍታት እይታቸው ላቅ ያለ አባቶችን በመመልመል ይሰይማል፡፡

- ከዕርቅ ሽማግሌዎች አፈንግጦ የሚወጣ ተበዳይ የአካባቢውን ማህበረሰብ በመሰብሰብ ‹‹እንበደዲ›› በማለት ይወስናሉ፡፡ እንበደዲ ማለትም ይህን ግለሰብ /ተበዳይ/ ከማንኛውም የማህበራዊ ህይወት ማግለል ማለት ነው፡፡

- ከወንድ ሽማግሌዎች ባልተናነሰ ሁኔታ በአካባቢው መጠሪያ የዱበርቲዎች ወይንም የሴቶች ሚና የሟች ቤተሰብ የበቀልና የቁጭት ስሜት እንዳያሳዩ ልብ የሚያራራ የምልጃና የልመና ዜማ ለሟች ቤተሰቦች ያቀርባሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በዕርቁ ዕለት ምግቡን በማቀራረብና ሟችና ገዳይ አብረው እንዲበሉ በማድረግ ይቅር ባይነትን ያስተምራሉ።

(ሙሉውን ከላይ በPDF ያንብቡ)

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia