TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ለመደባ አያገለግሉም የተባሉት ውጤቶች አልተሰረዙም!

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ም/ዳይሬክተር አቶ መሳይ ደምሴ ለተጠየቋቸው ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያ፦

TIKVAH-ETH ከአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት አዳምጦ ቃል በቃል ያሰፈረው!

የውጤት ግሽበት ምን ማለት ነው??

"ያልተጠበቀ ውጤት እስካሁን ድረስ በሀገሪቱ የፈተና አሰጣጥ በተለይም የ12ኛ ክፍል ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ሲሰጥ የተመዘገቡ ውጤቶች አሉ የ10 ዓመት ሊሆን ይችላል ወይም ከዚያ በላይ ነገር ግን ባልተጠበቀ መልኩ መቶ እና ሁለት መቶ፣ ሶስት መቶ በሁለት ወይም በሶስት የትምህርት አይነት ወይም በአራት የትምህርት አይነት መቶዎች አይመዘገብም። ዘንድሮ ግን በርካታ ውጤት ከ90 በላይ የተመዘገቡት በተለይ በመጨረሻዎቹ ሁለት ቀናትና ይሄ ያልተጠበቀ ነው። 6002 የሚሆኑ ተማሪዎች አጠቃላይ መቶ ሙሉ በሙሉ ያስመዘገቡት ውጤት ከዚህ በፊት ከተለመደው ባለን ሪከርድ የለም።"

ውሳኔው በራሳቸው ሰርተው ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ችግር አይፈጥርም?

" ችግር አይፈጥርም፤ 7 የትምህርት አይነቶች ናቸው የተሰጡት የመጀመሪያዎቹ ሰኔ 6-7 የተፈተኑት ፈተናዎች እንግሊዘኛ ለሁሉም፣ ለተፈጥሮ ሳይንስና ለማህበራዊ ሳይንስ፣ ሂሳብ ለተፈጥሮ ሳይንስ እና ማህበራዊ ሳይንስ፤ አፕቲትዩድ ለሁሉም ለማህበራዊ ሳይንስ ጆግራፊ፣ ለተፈጥሮ ሳይንስ ፊዚክስ ተፈትነዋል። የጋሸበ ውጤት አለ የሚል ግምት ሲፈጠር የሰኞና የማክሰኞ፣ የመጀመሪያዎቹ ፈተናዎችም በኮሚቴ ታይቷል። በአንፃራዊነት የተማሪዎች ውጤት ተቀራራቢ ነው የነዚያኛዎቹ ግን የጋሸበ ነው ያልተጠበቀ ነው።"

የጋሸበ ውጤት የታየባቸው አካባቢዎች?

"የቴክኒክ ኮሚቴው ያጠናው አጠቃላይ በሀገሪቱ ነው። በጣም በተወሰኑ ክልሎች በ4 ክልሎች በደቡብ፣ በአማራ፣ በቤኒሻንጉል አንድ ዞን፣ ኦሮሚያ የተወሰኑ ዞኖች የተወሰኑ ቁጥር፣ በርከት የሚለው በአማራ ክልል ሆኖ የጋሸበ ውጤት የተመዘገበበት ሁኔታ አለ። ነገር ግን በአንፃራዊነት ነው ሲታይ ግን በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የተሰጠው ፈተና ሰኞ እና ማክሰኞ ግሽበት ያሳያል።"

ለምደባ የማያገለግሉት የትምህርት አይነቶች ዕጣ ፋንታቸው ምንድነው?

"ህብረተሰቡንም #የሚያወዛግበው እና ግልፅ ያልሆነላቸው ይሄ ነው። እጣ ፈንታቸው... በልጆቹ ውጤት ሰርተፊኬት ላይ ይመዘገባል። ከዚህ በፊትም ቢሆን መንግስት ባለው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፤ የሳይንስና ከፍተኛ ሚኒስቴር በሚያወጣው መቁረጫ ነጥብ መሰረት ያስገባል። ሲያስገባ የሚወስደው መስፈርት አለ መስፈርቱ እሱ በወሰነው ነው። በዚህ አራቱ ትምህርት ይወሰድ ብለን ወስነናል። መንግስት ነው የወሰነው። የዩኒቨርሲቲ የማቀበል አቅም ...እነዚህ ዩኒቨርሲቲዎች ለመግባት መንግስት ኢንቨስት ለማድረግ አስተምራለሁ፣ በቀጣይ የሃገሪቱን እጣ ፈንታ የሚወስኑ አካላት ናቸው ብሎ የወሰደው compulsory ሶስቱ የትምህርት አይነቶች ናቸው ሂሳብ፣ እንግሊዘኛ እና አፕቲትዩድ ወሳኝ ናቸው እንደገና በፈተና አሰጣጥም የተረጋጋ በውጤትም በተማሪዎች ነካከል የጎላ ልዩነት ስለሌለ ተፅኖ ስለማይፈጥር ነገር ግን ሰኞና ማክሰኞ የተፈተኑት ለመደባ አያገለግሉም የተባሉት ውጤታቸው አልተሰረዙም ህብረተሰቡ ጋር ግን እንደተሰረዘ ተደርጎ ይወራል አልተሰረዙም! በልጆቹ ሰርተፊኬት ላይ ይቀመጣል። ከተቀመጠ በኃላ ለስኮላርሺፕ ይጠቀሙበታል፣ ለግል ዩኒቨርስቲ ተቋማት ይጠቀሙበታል። ሙቁረጫ ነጥብ 4ቱ የተወሰዱት በግልፅ ህብረተሰቡ እንዲያውቀውና እንዲረዳው የምንፈልገው ለመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች #ብቻ ነው፣ ለሌላ ይጠቀሙበታል።"

መቁረጫ ነጥብና ምደባው እንዴት ይከናወናል?

"የመቁረጫ ነጥቡን የሚወስናው የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ነው፤ ከምን ተነስቶ? ከአራቱ ትምህርት ውጤቶች ትምህርት ተነስቶ። ህብረተሰቡ ማወቅ ያለበት ከ400 ታርሟል። ከ400 ከፍተኛ ውጤት ያመጣው በግሌ በማውቀው ወደ 336 ያመጣው ከ400 ከፍተኛው ውጤት ነው 6 መቶ ምናምን የነበረው ሰው። በግምት እኛ ባለን መረጃ አምና እስከ 150,000 ተማሪዎችን ተቀብሏል ዩኒቨርሲቲዎች አሁንም ከዚያ ባነሰ አይቀበልም ከዚያ በተሻለ ሊቀበል ይችላል። ለጊዜው ግን እኔ የማውቀውና የምረዳውም የአምናውን እንኳን ብንወስድ 150,000 ተማሪ የመቀበል አቅም ይኖራቸዋል ዩኒቨርሲቲዎች፣ ከላይ ተነስቶ ወደታች ይሄዳል።"

ማነው ኃላፊነቱን የሚወስደው?

"ሃላፊነቱን የሚወስድ አካል ይኖራል። ይህንንም አጣርቶ የሚያቀርበው አሁን በሃገር አቀፍ ደረጃ የተቋቋመው ኮሚቴ ካጣራ በኃላ ነው። ተጠያቂ የሚሆነው። ኮሚቴው ተዋቅሮ አልቋል ወደስራም ተገብቷል። ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ነው። በየደረጃው ያለ አካል ከላይ እስከታች ኤጀንሲውም ጋር ችግር ካለ፣ ትምህርት ሚኒስቴርም ችግር ካለ፣ ችግር አለ ተብሎ ተዳሶ እርምጃ ይወሰዳል። ወደፊት ለህብረተሰቡ ግልፅ ይሆናል።"

#TIKVAH_ETHIOPIA

TIKVAH-ETH ከአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት አዳምጦ ቃል በቃል ያሰፈረው!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የተጠነቀቀ ይህን የከፋ ጊዜ ይሻገራል!

ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የሩቅ ሀገር በሽታ ነው ሲባል እንዳልነበር ዓለምን አዳርሶ ዛሬ ሀገራችንን እያመሰ ነው

በአዲስ አበባ አሁንም መደበኛ ህይወት የሚመራባቸው አካባቢዎች እንዳሉ ተመልክተናል። ይህ እጅግ ከፍተኛ ዋጋ የሚያስከፍል ነው

በአ/አ የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ፍጥነት እየተሰራጨ ቢገኝም አሁንም ከክልሎች ጋር 'የህዝብ ትራንስፖርት' አልቆመም ይህ ሁኔታ መላው የሀገሪቱን ህዝብ አደጋ ላይ እየጣለ ነው

የክልል ከተሞች ላይ የሚታየው መዘንጋት ደግሞ ችግሩን የከፋ ሊያደርገው ይችላል። ጊዜው ሳይረፍድ መፍትሄ ቢፈልግ መልካም ነው

የክልል ነዋሪዎች ጋር ቫይረሱ በስፋት ያለው አዲስ አበባ #ብቻ ነው እኛ ጋር አይደርስም በሚል የተሳሳተ አመለካከት ካለ አሁን መታረም አለበት።

የውጭ ሀገር ነው ሲባል የነበረው በሽታ ዛሬ ሀገራችን ፣ ሰፈራችን ደርሷል፤ #ካልተጠነቀቅን የእያንዳንዳችንን ቤት ማንኳኳቱ አይቀርም።

የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መከላከያ መንገዶች እጅግ በጣም ቀላል ሆነው ሳለ ለምን የማይገባ ዋጋ እንከፍላለን ?

• የእጆቻችንን ንፅህና እንጠብቅ! /መታጠብ/

• ቤት ውስጥ እንቀመጥ! /መቀመጥ/

• የስራችን ሁኔታ ከቤት የሚያስወጣና አስገዳጅ ጉዳዮች ኖረውን ከቤት ከወጣን የአፍንጫና አፍ መሸፈኛ እናድርግ! /መሸፈን/

• በሁሉም ቦታ አካላዊ ርቀት እንጠብቅ! /መራራቅ/

የኢትዮጵያ መንግስት የቫይረሱን ከፍተኛ ስርጭት ከግምት ውስጥ ሊያስገባና በህዝብ ትራስፖርቶች ላይ ያለውን ሁኔት ሳይውል ሳያድር መፍትሄ ሊፈልግለት ይገባል። ካልሆነ በሀገር ደረጃ የሚከፈለው ዋጋ ከፍተኛ ነው!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የ12ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተፈታኞችን በሚመለከት ፦

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሐረጓ ማሞ ከ12ኛ እና ከ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ጋር በተያያዘ ተከታዩን ብለውናል ፦

- የ12ኛ እና የ8ኛ ክፍል ፈተና በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲሰጥ በቅድሚያ ትምህርት ቤቶች ኮቪድ-19 መከላከልን መርህ ባደረገ መልኩ ዝግጅት ሙሉ በሙሉ ማጠናቀቅ ይጠበቅባቸዋል።

- ከፈተናው አስቀድሞ የትምህርት ቤቶችን ዝግጁነት የማረጋገጥ ስራ በትምህርት ሚኒስቴር ይሰራል።

- ይህ ተግባራዊ እንዲሆን ሁሉም ትምህርት ቤቶች ፣ የጤና ተቋማት፣ ወላጆች፣ አጠቃላይ ማህበረሰቡ ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

- የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የ11ኛ ክፍል ትምህርት ያጠናቀቀቁ እና የ12ኛ ክፍልን የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርት የተከታተሉ መሆን አለባቸው።

- የ8ኛ ክፍል ተፈታኛ ተማሪዎች የ7ኛ ክፍል ትምህርት ያጠናቀቁ እና የ8ኛ ክፍልን የአንደኛ ሴሚስተር ትምህርት የተከታተሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

- ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው በሙሉ አቅም እንዲመለሱ የስነ ልቦና ድጋፍ ይደረግላቸዋል።

- የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና እና ምዝገባ በኦንላይን ይካሄዳል። ተማሪዎች የ45 ቀን የክለሳ እና የቴክኖሎጂ መለማመጃ ጊዜም ይኖራቸዋል።

- በነገራችን ላይ ትምህርት ቤቶች የሚከፈቱት ፣ ፈተናዎችም የሚሰጡት ትምህርት ቤቶች አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ ማሟላት ሲችሉ #ብቻ ነው

- ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ቤቶች እንዲከፈቱ ያስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሸራረፉ እንዲተገበሩ ለሁሉም ባለድርሻ አካላት ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
159_በመንደር_የንግድ_ቁጥጥር_የአሠራር_ሥርዓት_መመሪያ_ቁጥር_159_2016.pdf
#AddisAbaba #ንግድ

የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ማህበረሰብ ያለወከባ በተረጋጋ መንፈስ የንግድ ተግባሩን ለማከናወን እንዲያስችል ዕድል ይፈጥርለታል የተባለ አዲስ መመሪያ ስራ ላይ መዋሉን ለማወቅ ተችሏል።

አዲሱ መመሪያ  " በመንደር ንግድ ቁጥጥር አሰራር ስርዓት መመሪያ 159/2016 " እንደሚባል ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

መመሪያው በየትኛው አስተዳደር እርከን የትኛው አይነት እርምጃ እንደሚወሰድ በግልጽ ያስቀመጠ ሲሆን ይህም ሲታይ የነበረውን ግልጽ እና ፍትሃዊ ያልሆነ አሰራር ያስቀራል ተብሏል።

በአዲሱ የመንደር ንግድ መመሪያ መሰረት የወረዳ የንግድ ቁጥጥር ባለሙያ አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወስድ ህጉ የሚፈቅድለት በተመደበበት መንደር ላይ ፦
ያለ ንግድ ፍቃድ
ባልታደሰ ፍቃድ
በታገደ አልያም በተሰረዘ ንግድ ፈቃድ የሚነግድ የንግድ ድርጅት ላይ #ብቻ_ነው። ይህን ሲያደርግም ለቅርብ ኃላፊ ማሳወቅ አለበት።

ከዚህ ወጪ ያሉት ጥፋቶች #በሙሉ እርምጃ ሳይወስድ ለቅርብ ኃላፊው በፅሁፍ በማሳወቅ ለውሳኔ ወደ ንግድ ቢሮ መላክ ይጠበቅበታል ፤ የተወሰነውን ውሳኔ የማስፈፀም ኃላፊነትም አለበት።

መመሪያው ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/87886

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia