TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#HPR

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ነገ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኝ መረጃ ያመለክታል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#HPR

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡ ጥያቄዎችና የማሻሻያ ሞሽን ምላሽ እየሰጡ ይገኛሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#HPR

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ባካሔደው 5ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ ስብስባ ቤት ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሆኑ የውጭ ዜጎች በመድን እና አነስተኛ የፋይናንስ ሥራ ላይ እንዲሳተፉ የሚፈቅደውን አዋጅ አጸደቀ። ምክር ቤቱ የተሻሻሉትን የመድን እና የአነስተኛ የፋይናንስ ሥራ አዋጆች በሙሉ ድምፅ ያጸደቀው ከገቢ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቀረበለትን ሪፖርት እና የውሳኔ ሐሳብ ከመረመረ በኋላ ነው።

Via ኢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethioia
#NewsAlert

በዛሬው ዕለት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቀጣይ የሚካሄደውን ሀገራዊ ምርጫ አስመልክቶ የተቀመጡ ሦስት አንቀፆች ህገመንግስታዊ ትርጓሜ እንዲሰጣቸው በ25 ተቃውሞ በአብላጫ ድምጽ አፅድቋል።

ምክር ቤቱ የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በህመንግስቱ አንቀፅ 83 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ምርጫውን መራዘም በተመለከተ ትርጉም የሚያስፈልጋቸውን አንቀፆች በአንድ ወር ወስጥ እንዲተረጉም ነው የወሰነው፡፡

የህግ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምርጫን በተመለከተ የተቀመጡ ሶስት አንቀጾች ላይ የህገ መንግስት ትርጓሜ እንዲሰጥ የውሳኔ ሀሳብ ማቅረቡን አስታውቀዋል።

የውሳኔ ሀሳቡ የህገ መንግስቱ አንቀፅ 54/1 አንቀፅ 58/3 እና አንቀፅ 93 ከህገ መንግስት አላማ እና ግቦች እንዲሁም መሰረታዊ መርሆች ጋር ለማስተሳሰር ትርጉም እንዲሰጥባቸው የሚል ህገ መንግስታዊ የመፍትሄ ሀሳብ ነው ያቀረበው።

#HPR #EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Update

የአገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ ላይ ግብዓት ማሰባሰብ ተጀምሯል።

በህ/ተ / ም/ቤት የህግ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ላይ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቶ የተለያዩ ግብዓቶችን አሰባስቧል፡፡

በይፋዊ የውይይት መድረኩ ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የሰብኣዊ መብት ኮሚሽን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤትና የተለያዩ የሲቪክ ማህበራት የስራ ኃላፊዎች ተሳትፈውበታል፡፡

በውይይቱ መግቢያ የፍትህ ሚንስቴር ሚንስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ማቋቋሚያ አዋጁን አስመልክተው አጭር ገለጻ ያቀረቡ ሲሆን፤ የማቋቋሚያ አዋጁን አስፈላጊነት፣ እስካሁን ያለፈባቸውን ሂደቶች እንዲሁም የኮሚሽኑ ተግባርና ኃላፊነት ላይ ማብራሪያ አቅርበዋል፡፡

ለሀገራዊ መግባባት የሚጠቅሙ አጀንዳዎች መለየት፣ የሚሳተፉ አካላትን መለየት፣ የምክክር መድረኮችን ማሳለጥ፣ ከምክክር መድረኮቹ የተገኙ ምክረ ሀሳቦችንና የአተገባበር ስልታቸውን የሚጠቁም ሰነድ ማዘጋጀት እንዲሁም ተግባራዊነታቸውን መከታተል ከሚቋቋመው ኮሚሽን የሚጠበቁ ዋና ዋና ተግባራት ስለመሆናቸው ጠቁመዋል፡፡

ከየተቋማቱ የመጡት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ለሚቋቋመው ኮሚሽን ይጠቅማል ያሉትን መልካም ተሞክሮዎቻቸውን በማጋራት ሊገጥም ይችላል ያሉትን ስጋት ጠቁመዋል፡፡

በሚቋቋመው ኮሚሽን ተግባርና ኃላፊነት እንዲሁም የኮሚሽነሮች አሰያየም ላይ ተደጋጋሚ አስተያየቶች የቀረቡ ሲሆን፤ በረቂቅ አዋጁ አንቀጽ 9/10 ስር ኮሚሽኑ ዝርዝር ሪፖርት በማዘጋጀት ለመንግስት ያቀርባል የሚለው ሀሳብ ኮሚሽኑን በመንግስት ተጽእኖ ስር ሊከተው ይችላል የሚሉና ተመሳሳይነት ያላቸው የገለልተኝነት ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን በዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ #HPR

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ተሳተፉ " ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን " ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ6ኛ ዙር አንደኛ አመት የስራ ዘመኑ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለማቋቋም የቀረበውም ረቂቅ አዋጅ ለህግ ፣ ፍትህ እና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቶ ነበር። ህብረተሰቡ መሳተፉን ማረጋገጥ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የመጀመሪያ ዙር የህዝብ አስተያየት መሰብሰቢያ መድረክ ተዘጋጅቶ ከህዝቡና ከተለያዩ ተቋማት የተወከሉ ተሳታፊዎች…
#ETHIOPIA

" የሚቋቋመው ኮሚሽን እውነተኛ ችግር ፈቺ ሊሆን ይገባል " - የውይይቱ ተሳታፊዎች

የአገራዊ የምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ሁለተኛው ዙር ይፋዊ የህዝብ ውይይት ዛሬ ቅዳሜ ተካሂዷል።

የሚቋቋመው ኮሚሽን እውነተኛ ችግር ፈቺ ሊሆን ይገባል ተብሏል።

በውይይቱ የፍትህ ሚኒስቴር ሚንስትር ጌዲዮዎን ጢሞቲዮስ (ዶ.ር) የእጩ ኮማሽነሮችን ሹመትን በተመለከተ በጠቅላይ ሚንስትሩ አቅራነት በህ /ም/ቤት የሚጸድቅ ሲሆን ኮሚሽነሮቹ መሉ ጊዜያቸውን ስራ ላይ የሚያውሉ እንደሆነ አስረድተዋል።

አገራዊ የምክክር መድረኩ ዋና አላማ አገራዊ መግባባትን ለመፍጠር እሰከሆነ ድረስ በርዕሱ ላይ ማሻሻያ ሊደረግበት አንደሚችል ተናግረዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች የሚቋቋመው ኮሚሽን የህዝብን አንድነት ለማስቀጠልና አገሪቱ ከገባችበት ውስብስብ ችግር ማውጣት የሚያስችል መሆን አለበት ብለዋል።

ኮሚሽኑ ነጻና ገለልተኛ አንዲሆን በጀቱ ከገንዘብ ሚኒስቴር መውጣት እንዳለበት እና እጩ ኮሚሽነሮች በጠቅላይ ሚንስትር ይቀርባሉ የሚሉ ሀሳቦች ከረቂቅ አዋጁ መውጣት አንዳለባቸው የውይይቱ ተሳታፊዎች አስተያየት ሰጥተዋል።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች ከፖለቲካ፣ ከሀይማኖት እና ከብሄር ወገንተኝነት የፀዱ፣ ችሎታቸው እና ብቃታቸው የተረጋገጠ፣ እንዲሁም አገርና ህዝብን ለማሻገር ቁርጠኛ የሆኑ ህዝብ ያመነባቸው ሊሆኑ እንደሚገባ አንስተዋል።

አገር በቀል እውቀቶች እና እሴቶች በረቂቅ አዋጁ መካተት እንዳለበት የውይይቱ ተሳታፊዎች ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል የረቂቅ አዋጁን ርዕስ አገራዊ የምክክር መድረክ ከማለት ይልቅ ‹‹ብሄራዊ የመግበባት መድረክ›› መባል አንዳለበት ሀሳባቸውን ገልጸዋል፤ ረቂቅ አዋጁ ቋንቋን ታሳቢ ማድረግ እንዳለበት ጠቁመዋል።

#HPR

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA የፀደቀው የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምን ማሻሻያዎች ተደረገበት ? የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚ አዋጅ በዛሬው ዕለት በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል። የኮሚሽኑን መሪዎች በመሰየሙ ሂደት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሙሉ በሙሉ እጃቸው እንዳይገባ ሆኖ ነው የኮሚሽኑ የማቋቋሚያ አዋጅ የፀደቀው። አገራዊ መግባባትን ለማምጣት ተከታታይ ምክክሮችን በማዘጋጀት እንዲሰራ ስልጣን የተሰጠውን ኮሚሽን…
" የአገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች በህዝብ ይመረጣሉ " - የህግ ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ

የአገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች በህዝብ እንደሚመረጡና ሹመታቸውም በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት እንደሚጸድቅ የህግ ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል፡፡

መግለጫውን የሰጡት የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወ/ሮ እፀገነት መንግስቱ ናቸው።

በጋዜጣዊ መግለጫው ምን ምን ነጥቦች ተነሱ ?

• የኮሚሽነሮች ጥቆማ መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ያካተተ ነው። ከተጠቆሙት 14 እጩዎች መካከል 11 ተመልምለው በአፈ ጉባኤው አቅራቢነት በም/ቤቱ ይሾማሉ።

• ኮሚሽነሮቹ በም/ቤቱ ከተሰየሙበት እለት ጀምሮ ለ3 ዓመታት የሚቆይ የስራ ጊዜ ይኖራቸዋል። እንደ አስፈላጊነቱ ቆይታቸው ሊራዘም ይችላል።

• በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ስለ #ድርድር የሚገልጽ ምንም አይነት ይዘት አልተካተተም፤ የአዋጁ ዋና አላማ እስካሁን መግባባት ላይ ያልተደረሰባቸውና የኢትዮጵያን ህልውና የሚፈታተኑ የተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ያካተተ ውይይት በማድረግ ችግሮችን መፍታት ነው።

• የሚቋቋመው ኮሚሽን ከምክክር መድረኮቹ የሚያገኘውን ምክረ ሀሳብ በመቀመር ተግባራዊ እንዲደረጉ ይሰራል። ም/ቤቱን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነት ወስደው እንደሚያስፈጽሙና ለስኬታማነቱም ጠንካራ የክትትልና ቁጥጥር ስርዓት ይዘረጋል።

#HPR

@tikvahethiopia
#Update

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አማካሪ ኮሚቴ ሁለት አጀንዳዎችን በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

አጀንዳዎቹ ፦
• የማሕበረሰብ ጤና አቀፍ መድህን ረቂቅ አዋጅ
• የ2014 በጀት አመት ተጨማሪ በጀት ረቂቅ አዋጅ ናቸው።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ በማሕበረሰብ ጤና አቀፍ መድህን ረቂቅ አዋጅ ላይ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፣ ረቂቅ አዋጁ መታከም የማይችለው የሕብረሰተብ ክፍል ፍትሃዊ ፣ ተደራሽ እና ጥራት ያለው የጤና ሽፋን በመስጠት እንዲታከም ለማድረግ ያለመ መሆኑን አብራርተዋል።

በሌላ በኩል በ2014 በጀት አመት ተጨማሪ በጀት ረቂቅ አዋጅ አስፈላጊነት ላይም ወ/ሮ ሎሚ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ፣ ረቂቅ አዋጁ የተቋረጡ እና በጅምር ላይ ያሉ ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ለማስቀጠል እንዲሁም በኮሮና እና በጦርነቱ ምክንያት የወጡ ወጪዎችን ለመሸፈን እንደሚውል ጠቅሰው ለዚህም በሚኒስትሮች ምክር ቤት ታይቶ 122 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት እንደቀረበ ነው የገለጹት።

#HPR

@tikvahethiopia
#HPR

በዛሬው ዕለት የሕዝብ ተወካዮች ምክርት ባካሄደው ሶስተኛ ልዩ ስብሰባ የቀረበለትን የ120 ቢሊየን ብር ተጨማሪ በጀት አጽድቋል።

የተጨማሪ በጀት ውሳኔው በዘጠኝ ተቃውሞ በሰባት ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ ነው የፀደቀው።

በምክር ቤቱ ከጸደቀው በጀት ውስጥ 90 ቢሊየኑ ለአገር መከላከያ ሰራዊት ስንቅና ትጥቅ እንደሚውል ተነግሯል።

ለዕለት ደራሽ ዕርዳታ 8 ቢሊየን ብር፣ ለመጠባበቂያ በጀት 5 ቢሊዮን ብር፣ ለካፒታል ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ 7 ቢሊዮን ብር እና ለታክስ ገቢ ጉድለት ማካካሻ 9 ቢሊዮን ብር ፀድቋል።

ተጨማሪ በጀቱ የተቋረጡ እና በጅምር ላይ ያሉ ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ለማስቀጠል እንዲሁም በጦርነቱና በኮቪድ 19 ምክንያት በቂ ያለተሰበሰበውን ታክስ ጉድልት ለመሙላት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

ቀደም ሲል ለ2014 በጀት አመት 561 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር የፌደራል መንግስቱ በጀት ሆኖ በምክር ቤቱ መፅደቁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia