TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbaba 🛬 #DireDawa

በዛሬው ዕለት ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ በመጓዝ ላይ የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET248 ድሬዳዋ አውሮፕላን ማረፍያ ለማረፍ በዝግጅት ላይ ሳለ በአውሮፕላኑ ውስጥ #ጢስ መታየቱን አየር መንገዱ አሳውቋል።

አውሮፕላኑ በድሬዳዋ አውሮፕላን ማረፍያ በሰላም እንዳረፈም ገልጿል።

መንገደኞችን በተለመደው መልኩ ከአውሮፕላኑ ማውረድ መቻሉን ገልጾ አየር ጢሱ የተነሳበትን ምክንያት በማጣራት ላይ እንደሚገኝ ጠቁሟል።

ለተፈጠረው ክስተት መንገደኞቹን ይቅርታ ጠይቋል።

ከዚህ ቀደም (ከወራት በፊት) ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረ አውሮፕላን ውስጥ ጭስ መታየቱን ፤ ነገር ግን አውሮፕላኑ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፍያ በተመደበለት የመንገደኞች ማስተናገጃ በር ያለ ምንም እክል መቆሙ መንገዶኞቹም ከአውሮፕላን ላይ ደህንነታቸው እንደተጠበቀ መወርዳቸው መገለጹ የሚዘነጋ አይደለም።

በወቅቱም ጢሱ ከእሳት ወይም ከሌላ ነገር ጋር የተያያዘ ሳይሆን አዉሮፕላን ዉስጥ ያለዉ ዘይት ተቃጥሎ የተፈጠረ መሆኑን ይህም አልፎ አልፎ የሚያጋጥም ችግር እንደሆነ አስረድቶ ነበር።

ዛሬ ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ በመጓዝ ላይ በነበረውና ድሬዳዋ አውሮፕላን ማረፍያ ለማረፍ በዝግጅት ላይ በነበረው አውሮፕላኑ ውስጥ የታየው #ጢስ ምክንያት ምን እንደሆነ #እያጣራ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሳውቋል።

@tikvahethiopia