TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አሳዛኝ ዜና‼️

ሰባ ገደማ #ኢትዮጵያውያን በቀይ ባህር #የጀልባ_መገልበጥ አደጋ #ሞቱ:: ቀይ ባሕርን አቋርጠው ወደ ሳውዲ አረቢያ እና የመን በጀልባ በመጓዝ ላይ የነበሩ 70 ገደማ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የመገልበጥ አደጋ ደርሶባቸው ሞቱ። ከሟቾቹ ውስጥ ስድሳዎቹ ከትግራይ ክልል አፅቢ ወንበርታ ወረዳ የተነሱ ነበሩ ተብሏል።

ሰባ ገደማ ወጣቶች ይዛ ስትጓዝ የነበረችው ጀልባ የመገልበጥ አደጋ የደረሰባት ቅዳሜ መጋቢት 28 ለሊት መሆኑን ከአካባቢው የተገኙ መረጃዎች አመልክተዋል።

ከጀልባዋ ተሳፋሪዎች መካከል 60ዎቹ ከትግራይ ክልል አፅቢ ወንበርታ ወረዳ የተጓዙ መሆናቸው ከተሰማ በኋላ በወረዳዋ በከባድ የሐዘን እና ድንጋጤ ድባብ እንደምትገኝ የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

በተገለበጠችው ጀልባ ላይ የነበሩት ቀሪዎቹ ወጣቶች ኢትዮጵያውያን እንደነበሩ ቢነገርም ትክክለኛ ቁጥራቸውን እና ከየት አካባቢ እንደመጡ በተመለከተ እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

በአፅቢ ወንበርታ ወረዳ አብዛኞቹ የሟች ወጣቶች ቤተሰቦች የሞት መርዶውን በአደጋው ማግስት እሁድ እና ትናንት እንደተረዱ ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬለ አስረድተዋል። የወረዳው የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ከ40 በላይ የሟች ቤተሰቦች መርዶው እንደደረሳቸው ገልጿል። የትግራይ ክልል የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ትናንት ምሽት ባወጣው የሐዘን መግለጫ የአርባዎቹን ወጣቶች መሞት አረጋግጧል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia