TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፖሊስ በቂ ዝግጅት አድርጓል~ሀዋሳ‼️

በሃዋሳ ከተማ ነገ ለሚካሄደው የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ #ይፋጠንልን ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ በሰላም እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ማድረጉን የሃዋሳ ከተማ ፖሊስ አስታወቀ። 

የከተማው ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር #መስፍን_ዴቢሶ ለኢዜአ እንደገለጹት ነገ በሃዋሳ የሚካሄደውን ሰልፍ ተከትሎ #ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ ዝግጅት ተደርጓል።

የከተማው ፖሊስ ከዞን፣ ከክልሉ ልዩ ሃይልና ከፌደራል ፖሊስ ጋር በመቀናጀት ሰልፉ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች በቂ ጥበቃ ያደርጋልም ብለዋል፡፡

ፖሊስ አዛዡ እንዳሉት ከሪፈራል አደባባይ ጠዋት አንድ ሰዓት የሚጀመረው ሰላማዊ ሰልፍ መዳረሻው ከቀኑ ስድስት ሰዓት ሃዋሳ አለም አቀፍ ስታዲየም ነው፡፡

ሰልፉ ወደ ብሉናይል የሚያወጣውን አስፓልት ይዞ ተስፋዬ ግዛው ህንጻ አደባባይ ሲደርስ ወደ ሃዋሳ አለም አቀፍ ስታዲየም እንደሚገባና ማጠቃለያውን እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡

በዚህ ምክንያት መንገዶቹ ለተሸከርካሪ ዝግ ይሆናሉ ያሉት ኮማንደር መስፍን፤ በበቂ የፀጥታ ሃይል ጥበቃ እንደሚደረግም ገልጸዋል፡፡

የከተማው ነዋሪ በሰልፉ ምክንያት ስጋት ውስጥ እንዳይገባ በየክፍለ ከተማው #ውይይት መደረጉን ገልጸው ህዝቡም ለሰልፉ ሰላማዊነት የበኩሉን እንዲወጣ ጠይቀዋል፡፡

የሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴ የሚዲያ ተጠሪ አቶ ሳሙኤል በላይነህ በበኩሉ የሲዳማ ብሄር በክልል የመደራጀት ህገ-መንግስታዊ ጥያቄውን ተከትሎ ህዝበ ውሳኔው በመዘግየቱ የተዘጋጀ ሰልፍ ነው” ብሏል።

ዓላማውም “ከዞን ምክር ቤት ጀምሮ በክልሉ ምክር ቤት ጸድቆ ለህዝበ ውሳኔ ለምርጫ ቦርድ የተላከው ሪፈረንደም ጥያቄ ዘግይቷል ይፋጠንልን” የሚል መሆኑን ተናግሯል።

ጥያቄው ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ተከትሎ የቀረበ ቢሆንም ምላሹ በመዘግየቱ በዞኑ ካሉ ወረዳዎችና ከሃዋሳ ከተማ የተውጣጡ ነዋሪዎች መንግስትን በሰላማዊ መንገድ የሚጠይቁበት እንደሆነም ተናግሯል፡፡

“ሰልፉ በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ ከከተማው ፖሊስና ከሃዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ጋር በቅንጅት እየሰራን ነው” ብሏል፡፡

በሰላማዊ ሰልፉ የመንግስት አካላት፣ የተለያዩ ተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎችና የሰልፉ ደጋፊዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሃዋሳ #ሃምሌ19

በሐዋሳ ከተማ በዛሬው ዕለት የተከበረው ዓመታዊው የገብርኤል የንግሥ በዓል ሰላም መጠናቀቁን የከተማው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር #መስፍን_ዴቢሶ ገልፀዋል። 

@tsegabwolde @tikvahethiopia